ፈርዖንም ሎሌዎቹን እንዲህ አላቸው፥ “በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን እንደዚህ ያለ ሰውን እናገኛለን?”
ምሳሌ 22:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገርን የሚረዳ፥ በሥራውም ብልህ የሆነ ሰው፥ ወደ ነገሥታት ይቀርባል፤ በተዋረዱ ሰዎችም ፊት አይቆምም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሙያው ሥልጡን የሆነውን ሰው አይተሃልን? በነገሥታት ዘንድ ባለሟል ይሆናል፤ አልባሌ ሰዎችን አያገለግልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሥራው ብልህ ሰው ትመለከታለህን? በነገሥታት ፊት ያገለግላል፥ በተራ ሰዎችም ፊት ሊያገለግል አይቆምም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሥራው የሠለጠነ ሰው ታያለህን? እንደዚህ ያለ ሰው በተራ ሰው ፊት ሳይሆን በነገሥታት ፊት ለአገልግሎት ይቆማል። |
ፈርዖንም ሎሌዎቹን እንዲህ አላቸው፥ “በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን እንደዚህ ያለ ሰውን እናገኛለን?”
ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ።
በመልካሙ ምድር አባትህንና ወንድሞችህን አኑራቸው፤ ከእነርሱም ውስጥ ዕውቀት ያላቸውን ሰዎች ታውቅ እንደሆነ በእንስሶች ጠባቂዎች ላይ አለቆች አድርጋቸው።”
አሣሄልንም አንሥተው በቤተ ልሔም በአባቱ መቃብር ቀበሩት፤ ኢዮአብና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ፤ ሄዱ፥ በኬብሮንም አነጉ።
ሚስቶችህ የተመሰገኑ ናቸው፤ በፊትህ ሁልጊዜ የሚቆሙ፥ ጥበብህን የሚሰሙ እነዚህ አገልጋዮችህም ምስጉኖች ናቸው።
ኢዮርብዓምም ጽኑዕ ኀያል ሰው ነበረ፤ ሰሎሞንም ጐልማሳው ኢዮርብዓም በሥራ የጸና መሆኑን ባየ ጊዜ በዮሴፍ ነገድ ሥራ ሁሉ ላይ ሾመው።
እነዚህ በነጣዔምና በጋዲራ ከንጉሡ ጋር የሚቀመጡ ሸክላ ሠራተኞች ነበሩ። እነርሱም በመንግሥቱ ጸንተው በዚያ ይኖሩ ነበር።
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።