La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 31:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴም ለሕ​ዝቡ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ራ​ቸው፥ “ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ሰዎ​ችን አስ​ታ​ጥቁ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምድ​ያ​ምን ይበ​ቀሉ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከም​ድ​ያም ጋር ይሰ​ለፉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፤ “ምድያማውያንን ለመውጋት እንዲሄዱና ስለ እግዚአብሔርም እንዲበቀሏቸው ከሰዎቻችሁ ጥቂቶቹን ለጦርነት አዘጋጁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሙሴም ሕዝቡን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ “ከእናንተ መካከል ሰዎች ለጦርነት የተዘጋጁ ይሁኑ፤ ስለ ጌታ በቀል ምድያምን እንዲበቀሉ በምድያም ላይ ይዝመቱ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ “ምድያማውያን በእግዚአብሔር ላይ ስለ ፈጸሙት በደል አደጋ ጥላችሁ ትበቀሉአቸው ዘንድ ለጦርነት ተዘጋጁ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሙሴም ሕዝቡን፦ ከእናንተ መካከል ሰዎች ለጦርነት ይሰለፉ፤ ስለ እግዚአብሔር በቀል ምድያምን ይበቀሉ ዘንድ በምድያም ላይ ይሂዱ፤

Ver Capítulo



ዘኍል 31:3
12 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢዩን፥ “በፊቴ ቅን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ በል​ቤም ያለ​ውን ሁሉ በአ​ክ​አብ ቤት ላይ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ልጆ​ችህ እስከ አራት ትው​ልድ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ላይ ይቀ​መ​ጣሉ” አለው።


የባ​ሪ​ያ​ዎቼን የነ​ቢ​ያ​ትን ደም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ባሪ​ያ​ዎች ሁሉ ደም ከኤ​ል​ዛ​ቤል እጅና ከአ​ክ​ዓብ ቤት ሁሉ እጅ እበ​ቀል ዘንድ የጌ​ታ​ህን የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ታጠ​ፋ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ሰ​ወ​ረች እጅ ዐማ​ሌ​ቅን እስከ ልጅ ልጅ ይዋ​ጋ​ልና።


ያ ቀን ጠላ​ቶ​ቹን የሚ​በ​ቀ​ል​በት የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የበ​ቀል ቀን ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ በልቶ ይጠ​ግ​ባል፤ በደ​ማ​ቸ​ውም ይሰ​ክ​ራል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት በሰ​ሜን ምድር በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ ነውና።


የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በቀል፥ የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንም በቀል፥ በጽ​ዮን ይነ​ግሩ ዘንድ ሸሽ​ተው ከባ​ቢ​ሎን ሀገር ያመ​ለ​ጡት ሰዎች ድምፅ ተሰ​ም​ቶ​አል።


የቃል ኪዳ​ኔ​ንም በቀል ይበ​ቀ​ል​ባ​ችሁ ዘንድ ሰይፍ አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ ከተ​ማ​ች​ሁም ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ፤ ቸነ​ፈ​ር​ንም እሰ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ። በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም እጅ ተላ​ል​ፋ​ችሁ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤


“የካ​ህኑ የአ​ሮን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ በቅ​ን​ዓቴ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቀን​ቶ​አ​ልና ቍጣ​ዬን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መለሰ፤ እኔም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በቅ​ን​ዓቴ አላ​ጠ​ፋ​ሁም።


ለአ​ም​ላኩ ቀን​ቶ​አ​ልና፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አስ​ተ​ስ​ር​ዮ​አ​ልና፥ ለእ​ርሱ ከእ​ር​ሱም በኋላ ለዘሩ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የክ​ህ​ነት ቃል ኪዳን ይሆ​ን​ለ​ታል።”


ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ሁሉ ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦር​ነት ስደዱ፤”


በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ መሳ​ፍ​ንት ስለ መሩ ሕዝ​ቡም ስለ ፈቀዱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ አለ፥ “ሜሮ​ዝን ርገሙ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርዳታ አል​መ​ጡ​ምና፥ በኀ​ያ​ላን መካ​ከል ወደ እርሱ ርዳታ አል​መ​ጡ​ምና፥ በቤ​ቶ​ችዋ ያሉ​ትን ሰዎች ፈጽ​ማ​ችሁ ርገሙ።”