ሚልክያስ 2:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳዳችን ወንድማችንን ስለ ምን አታለልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለንምን? የፈጠረንስ አንድ አምላክ አይደለምን? ታዲያ እርስ በርሳችን ታማኝነት በማጕደል የአባቶቻችንን ኪዳን ለምን እናረክሳለን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሁላችን አባት አንድ አይደለምን? የፈጠረንስ አንድ አምላክ አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማርከስ ሁላችንም ለምን ወንድማችንን እናታልላለን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሁላችንም አንድ አባት ያለን አይደለምን፤ የፈጠረንስ አንድ አምላክ አይደለምን? ታዲያ ለምን የቀድሞ አባቶቻችንን ቃል ኪዳን በማፍረስ እርስ በርሳችን እምነተቢሶች እንሆናለን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳዳችን ወንድማችንን ስለ ምን አታለልን? |
በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ እንደ ንስር ክንፍም እንደ ተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።
አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ፥ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ።
ሙሴም ገባ፤ ለሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቃሎች ሁሉ፥ ሥርዐቱንም ሁሉ ነገረ፤ ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ድምፅ፥ “እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እንሰማለን፤ እናደርጋለንም” ብለው መለሱ።
የቃል ኪዳኑንም መጽሐፍ ወስዶ ለሕዝቡ አነበበላቸው፤ እነርሱም፥ “እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እንሰማለን፤ እናደርጋለንም” አሉ።
አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዝአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ተቤዥችሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ።
የፈጠረህ ከማኅፀንም የሠራህ የሚረዳህም እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፥ “ባሪያዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም ወዳጄ እስራኤል ሆይ፥ አትፍራ።
ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፥ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ፤ አንድ ብቻውን በሆነ ጊዜ ጠራሁት፤ ባረክሁትም፤ ወደድሁትም፤ አበዛሁትም።
አንተ አባታችን ነህ፤ አብርሃም ግን አላወቀንም፤ እስራኤልም አልተገነዘበንም፤ ነገር ግን አንተ አባታችን አድነን፤ ስምህም ለዘለዓለም በእኛ ላይ ነው።
ስምህንም የሚጠራ፥ አንተንም የሚያስብ የለም፤ ፊትህንም ከእኛ መልሰሃል፤ ለኀጢአታችንም አሳልፈህ ሰጥተኸናል።
እያለቀሱ ሄዱ፤ እኔም በማጽናናት አመጣቸዋለሁ፤ በወንዝ ዳር በቅን መንገድ አስሄዳቸዋለሁ፤ በእርሱም አይሰናከሉም፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ ኤፍሬምም በኵሬ ነውና።”
“የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ምድር በአሉ በባድማ ስፍራዎች የተቀመጡ፦ አብርሃም ብቻውን ሳለ ምድሪቱን ወረሰ፤ እኛም ብዙዎች ነን፤ ምድሪቱም ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች ይላሉ። ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦
እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፣ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተም፦ ስምህን ያቃለልን በምንድር ነው? ብላችኋል።
እግዚአብሔር የወደደውን መቅደስ ይሁዳ አርክሶአልና፥ የእንግዳውንም አምላክ ልጅ ሚስት አድርጎ አግብቶአልና ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኵሰት ተሠርቶአል።
እናንተ ግን ከመንገዱ ፈቀቅ ብላችኋል፣ በሕግም ብዙ ሰዎችን አሰናክላችኋል፣ የሌዊንም ቃል ኪዳን አስነውራችኋል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ደቀ ዛሙርታቸውንም ከሄሮድስ ወገን ጋር ላኩበት፤ እነርሱም “መምህር ሆይ! እውነተኛ እንደ ሆንህ በእውነትም የእግዚአብሔርን መንገድ እንድታስተምር እናውቃለን፤ ለማንምም አታደላም፤ የሰውን ፊት አትመለከትምና፤
በልባችሁም ‘አብርሃም አባት አለን’ እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል።
እንግዲህ ለንስሓ የሚያበቃችሁን ሥራ ሥሩ፤ አብርሃም አባታችን አለን በማለት የምታመልጡ አይምሰላችሁ፤ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆችን ማስነሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁ።
እነርሱም መልሰው፥ “የእኛስ አባታችን አብርሃም ነው” አሉት፤ ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የአብርሃም ልጆች ብትሆኑስ የአብርሃምን ሥራ በሠራችሁ ነበር።
እናንተ ግን የአባታችሁን ሥራ ትሠራላችሁ።” እነርሱም፥ “እኛ ከዝሙት አልተወለድንም፤ ነገር ግን አንድ አባት አለን፤ እርሱም እግዚአብሔር ነው” አሉት።
እርሱም ሕይወትንና እስትንፋስን፥ ሌላውንም ነገር ሁሉ ለሁሉ ይሰጣልና እንደ ችግረኛ የሰው እጅ አያገለግለውም።
እርሱም በምድር ሁሉ ላይ ይኖሩ ዘንድ ሰዎችን ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ ይኖሩባትም ዘንድ ዘመንንና ቦታን ወስኖ ሠራላቸው።
እርሱም እንዲህ አለ፥ “ወንድሞቻችንና አባቶቻችን ሆይ፥ ስሙ፤ የክብር አምላክ ለአባታችን ለአብርሃም በሁለት ወንዞች መካከል ሳለ ወደ ካራንም ሳይመጣ ተገለጠለት።
በማግሥቱም ከመካከላቸው ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አገኘ፤ ሊያስታርቃቸውም ወድዶ፦ ‘እናንተማ ወንድማማቾች ናችሁ፤ እርስ በርሳችሁ ለምን ትጣላላችሁ?’ አላቸው።
ለእኛስ ሁሉ ከእርሱ የሆነ፥ እኛም ለእርሱ የሆን አንድ እግዚአብሔር አብ አለን፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ፥ እኛም በእርሱ የሆን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም አለን።
አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።
በሥጋ የወለዱን አባቶቻችን የሚቀጡን፥ እኛም የምንፈራቸው ከሆነ፥ እንግዲያ ይልቁን ለመንፈስ አባታችን ልንታዘዝና ልንገዛ በሕይወትም ልንኖር እንዴት ይገባን ይሆን?