ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ከመንጋው ነውር የሌለበትን ወይፈን ውሰድ፤ መቅደሱንም አንጻ።
ዘሌዋውያን 22:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን አይሠምርላችሁምና ነውር ያለበትን ለእግዚአብሔር አታቅርቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንከን ያለበትን ማንኛውንም ነገር አታቅርቡ፤ መሥዋዕታችሁ ተቀባይነት አይኖረውምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን አይሠምርላችሁምና ማናቸውም ነውር ያለበትን አታቅርቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነውር ያለበትን ማናቸውንም እንስሳ ብታቀርቡ ግን እግዚአብሔር አይቀበለውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን አይሠምርላችሁምና ነውር ያለበትን አታቅርቡ። |
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ከመንጋው ነውር የሌለበትን ወይፈን ውሰድ፤ መቅደሱንም አንጻ።
“መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲኖረው በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።
የተቀጠቀጠውን፥ ወይም የተሰበረውን፥ ወይም የተቈረጠውን ወይም የተሰነጋውን ለእግዚአብሔር አታቅርቡ፤ በምድራችሁም እነዚህን አትሠዉ።
ከእነዚህም ከባዕድ ወገን ከሆነ ሰው እጅ ለአምላካችሁ መባ አታቅርቡ፤ ርኵሰትም፥ ነውርም አለባቸውና አይቀበላችሁም።”
“ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ቍርባን የደኅንነት መሥዋዕት ቢሆን፥ ከላሞች መንጋ ተባት ወይም እንስት ቢያቀርብ፥ ነውር የሌለበትን በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ።
“ለእግዚአብሔርም ለደኅንነት መሥዋዕት የሚያቀርበው ቍርባኑ ከበጎች ተባት ወይም እንስት ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ያቀርባል።
ዕውር መሥዋዕትንም ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? አንካሳውንና የታመመውን ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? ያንን ለአለቃህ አቅርብ፣ በውኑ በአንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ፊትህን ይቀበላልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“እግዚአብሔር ያዘዘው የሕጉ ትእዛዝ ይህ ነው፤ መልካሚቱን፥ ነውርም የሌለባትን፥ ቀንበርም ያልተጫነባትን ቀይ ጊደር ያመጡልህ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው።
ለእግዚአብሔርም በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት ፥ ከላሞች አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፤ ነውር የሌለባቸውም ይሁኑላችሁ።
“በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና ነውር ወይም ክፉ ነገር ያለበትን በሬ ወይም በግ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋ።
ነውር የሌለው ሆኖ፥ በዘለዓለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እናመልከው ዘንድ ሕሊናችንን ከሞት ሥራ እንዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን?