ዘሌዋውያን 22:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 ማናቸውም ሰው ስእለቱን ለመፈጸም ወይም በፈቃዱ ለማቅረብ የደኅንነትን መሥዋዕት፥ ወይም በሬን፥ ወይም በግን፥ ለእግዚአብሔር ቢያቀርብ፥ ይሰምርለት ዘንድ ፍጹም ይሁን፤ ነውርም አይሁንበት። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 ማንኛውም ሰው ስእለት ለመፈጸም ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ለማበርከት ከላም ወይም ከበግ ወይም ከፍየል መንጋ ለእግዚአብሔር የኅብረት መሥዋዕት ሲያቀርብ፣ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ፍጹም የሆነውንና እንከን የሌለበትን ያቅርብ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ማናቸውም ሰው ከበሬ ወይም ከበግ መንጋ ስእለቱን ለመፈጸም ወይም በፈቃዱ ለማቅረብ የአንድነትን መሥዋዕት ለጌታ ቢያቀርብ፥ እንዲሠምርለት ፍጹም የሆነ ይሁን፥ በእርሱም ነውር የሆነ ነገር አይኑርበት። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ማንም ሰው ስእለት ተፈጽሞለት ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጎ የአንድነት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ቢያቀርብ፥ ተቀባይነት ማግኘት እንዲችል፥ እንስሳው ምንም ነውር የሌለበት ይሁን። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ማናቸውም ሰው ስእለቱን ለመፈጸም ወይም በፈቃዱ ለማቅረብ የደኅንነትን መሥዋዕት፥ ወይም በሬን ወይም በግን፥ ለእግዚአብሔር ቢያቀርብ፥ ይሠምርለት ዘንድ ፍጹም ይሁን፥ ነውርም አይሁንበት። Ver Capítulo |