ዘሌዋውያን 18:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሴትም ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ፤ ጸያፍ ነገር ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከሴት ጋራ እንደሚደረገው ሁሉ ከወንድ ጋራ አትተኛ፤ ይህ አስጸያፊ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሴትም ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ፤ ጸያፍ ነገር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነገር ስለ ሆነ፥ ግብረ ሰዶም አትፈጽም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሴትም ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ፤ ጸያፍ ነገር ነውና። |
በምድርም ሁሉ ዐመፅ ነበረ፥ ከእስራኤልም ልጆች ፊት እግዚአብሔር ያሳደዳቸው የአሕዛብን ርኵሰት ሁሉ ያደርጉ ነበር።
ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ በደለኞች ናቸው።
ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አያስቱአችሁ፤ ሴሰኞች፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ፥ ወይም አመንዝራዎች፥ ወይም ቀላጮች፥ ወይም በወንድ ላይ ዝሙትን የሚሠሩ፥ የሚሠሩባቸውም ቢሆኑ፤
ስለ ተሳልኸው ስእለት ሁሉ የአመንዝራዪቱን ዋጋና የውሻውን ዋጋ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አታቅርብ፤ ሁለቱም በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያጸይፉ ናቸውና።
እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።
ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ የኃጥኣን ልጆች የሆኑ የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም ይደበድቡ ነበር፤ ባለቤቱንም ሽማግሌውን ሰው፥ “ወደ ቤትህ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን” አሉት።