Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 19:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሎጥ​ንም ጠር​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “በሌ​ሊት ወደ አንተ የገ​ቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እና​ው​ቃ​ቸው ዘንድ ወደ እኛ አው​ጣ​ቸው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ሎጥንም ጠርተው፣ “በዚህች ምሽት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች የት አሉ? ሩካቤ ሥጋ እንድንፈጽምባቸው ወደ ውጭ አውጣልን” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፦ “በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ሎጥንም ጠርተው “ከአንተ ጋር ለማደር ወደዚህ የገቡት ሰዎች የት አሉ? ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ለማድረግ ስለምንፈልግ ወደ እኛ አውጣቸው!” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፤ በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናችው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 19:5
23 Referencias Cruzadas  

ሎጥም ወደ እነ​ርሱ ወደ ደጅ ፊት ለፊት ወጣ፤ መዝ​ጊ​ያ​ው​ንም በስ​ተ​ኋ​ላው ዘጋው፤


በም​ድ​ርም ሁሉ ዐመፅ ነበረ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሳ​ደ​ዳ​ቸው የአ​ሕ​ዛ​ብን ርኵ​ሰት ሁሉ ያደ​ርጉ ነበር።


ከአ​ባ​ቱም ከአሳ ዘመን የቀ​ረ​ውን ርኩስ ሥራ ከም​ድር አጠፋ።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘርን ባያ​ስ​ቀ​ር​ልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆ​ንን፥ እንደ ገሞ​ራም በመ​ሰ​ልን ነበር።


ዛሬም ክብ​ራ​ቸው ተዋ​ር​ዷ​ልና፥ ፊታ​ቸ​ውም አፍ​ሯ​ልና ኀጢ​አ​ታ​ቸው እንደ ሰዶ​ምና እንደ ገሞራ ኀጢ​አት ተቃ​ወ​መ​ቻ​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ተገ​ልጣ ታወ​ቀች።


ለጕ​ስ​ቍ​ል​ናሽ ከብ​ዙ​ዎች እረ​ኞች ጋር ኖርሽ የአ​መ​ን​ዝ​ራም ሴት ፊት ነበ​ረ​ብሽ፥ በሁ​ሉም ዘንድ ያለ ኀፍ​ረት ሄድሽ። ስለ​ዚህ የመ​ከ​ርና የበ​ልግ ዝናም ተከ​ለ​ከለ።


ርኩስ ነገ​ርን ስለ ሠሩ አፍ​ረ​ዋ​ልን? ምንም አላ​ፈ​ሩም፤ ውር​ደ​ት​ንም አላ​ወ​ቁም፤ ስለ​ዚ​ህም ከሚ​ወ​ድቁ ጋር ይወ​ድ​ቃሉ፤ በጐ​በ​ኘ​ኋ​ቸው ጊዜ ይዋ​ረ​ዳሉ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እነሆ የእ​ኅ​ትሽ የሰ​ዶም ኀጢ​አት ይህ ነበረ፤ ትዕ​ቢት፥ እን​ጀ​ራን መጥ​ገብ፥ መዝ​ለ​ልና ሥራን መፍ​ታት፥ ይህ ሁሉ በእ​ር​ስ​ዋና በል​ጆ​ችዋ ነበር፤ የች​ግ​ረ​ኛ​ው​ንና የድ​ሀ​ው​ንም እጅ አላ​ጸ​ና​ችም።


ኰር​ተው ነበር፤ በፊ​ቴም ርኵስ ነገር አደ​ረጉ፤ ስለ​ዚህ እንደ አየሁ አስ​ወ​ገ​ድ​ኋ​ቸው።


ሰማ​ር​ያም የኀ​ጢ​አ​ት​ሽን እኩ​ሌታ አል​ሠ​ራ​ችም፤ አንቺ ግን ከእ​ኅ​ቶ​ችሽ ይልቅ ኀጢ​አ​ትን አበ​ዛሽ፤ በሠ​ራ​ሽ​ውም ኀጢ​አት ሁሉ አጸ​ደ​ቅ​ሻ​ቸው።


ከሴ​ትም ጋር እን​ደ​ም​ት​ተኛ ከወ​ንድ ጋር አት​ተኛ፤ ጸያፍ ነገር ነውና።


ማና​ቸ​ውም ሰው ከሴት ጋር እን​ደ​ሚ​ተኛ ከወ​ንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድ​ር​ገ​ዋል፤ ፈጽ​መው ይገ​ደሉ፤ በደ​ለ​ኞች ናቸው።


ዐመ​ፀ​ኞች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት እን​ደ​ማ​ይ​ወ​ርሱ አታ​ው​ቁ​ምን? አያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ፤ ሴሰ​ኞች፥ ወይም ጣዖ​ትን የሚ​ያ​መ​ልኩ፥ ወይም አመ​ን​ዝ​ራ​ዎች፥ ወይም ቀላ​ጮች፥ ወይም በወ​ንድ ላይ ዝሙ​ትን የሚ​ሠሩ፥ የሚ​ሠ​ሩ​ባ​ቸ​ውም ቢሆኑ፤


“ከእ​ስ​ራ​ኤል ሴቶች ልጆች ሴት አመ​ን​ዝራ አት​ገኝ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወን​ዶች ልጆች ወንድ አመ​ን​ዝራ አይ​ገኝ።


ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች እያሳቱና እየሳቱ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።


ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል፤ በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል።


ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዐመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበርና በዐመፀኞች ሴሰኛ ኑሮ የተገፋውን ያን ጻድቅ ካዳነ፥


እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።


ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ደስ ባሰኙ ጊዜ የኃ​ጥ​ኣን ልጆች የሆኑ የከ​ተ​ማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ፤ በሩ​ንም ይደ​በ​ድቡ ነበር፤ ባለ​ቤ​ቱ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ውን ሰው፥ “ወደ ቤትህ የገ​ባ​ውን ሰው እን​ድ​ን​ደ​ር​ስ​በት አው​ጣ​ልን” አሉት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos