በእጃቸው ሥራ ሁሉ ሊያስቈጡኝ ትተውኛልና፥ ለሌሎችም አማልክት አጥነዋልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።
ኤርምያስ 42:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ቍጣዬና መቅሠፍቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፥ እንዲሁ ወደ ግብፅ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ ይፈስስባችኋል፤ እናንተም ለጥላቻና ለጥፋት ለስድብና ለርግማን ትሆናላችሁ፤ ይችንም ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩአትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ‘ቍጣዬና መዓቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ሁሉ ላይ እንደ ፈሰሰ፣ እንዲሁ ወደ ግብጽ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ በእናንተ ላይ ይፈስሳል፤ እናንተም የመረገሚያና የድንጋጤ፣ የመረገሚያና የመዘባበቻ ምልክት ትሆናላችሁ፤ ይህንም ስፍራ ዳግመኛ አታዩም።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ተናግሮአልና፦ ቁጣዬና መዓቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ወረደ፥ እንዲሁ ወደ ግብጽ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ ይወርድባችኋል፤ እናንተም ለጥላቻና ለመሣቀቂያ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ትሆናላችሁ፥ ይህንም ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሠራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ወደ ግብጽ እንሄዳለን ብላችሁ ብትወስኑ ከዚህ በፊት በኢየሩሳሌም ሕዝብ ላይ የወረደው ቊጣዬና መዓቴ በእናንተም ላይ ይወርዳል፤ ለሕዝብ ሁሉ አስፈሪ መቀጣጫ ትሆናላችሁ፤ የሚያዩአችሁም ሕዝብ ሁሉ መዘባበቻ ያደርጓችኋል፤ ስማችሁም ለመሳለቂያ ይሆናል፤ ይህችንም ስፍራ ዳግመኛ አታዩአትም።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ቍጣዬና መዓቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፥ እንዲሁ ወደ ግብጽ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ ይፈስስባችኋል፥ እናንተም ለጥላቻና ለመደነቂያ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ትሆናላችሁ፥ ይህንም ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩትም። |
በእጃቸው ሥራ ሁሉ ሊያስቈጡኝ ትተውኛልና፥ ለሌሎችም አማልክት አጥነዋልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።
ስማችሁንም እኔ ለመረጥኋቸው ሕዝቤ ጥጋብ አድርጋችሁ ትተዋላችሁ፤ ጌታ እግዚአብሔርም ያጠፋችኋል፤ ባሪያዎች ግን በሐዲስ ስም ይጠራሉ።
በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ፥ ለጥላቻና ለርግማን ይሆኑ ዘንድ በምድር መንግሥታት ሁሉ እንዲበተኑ አደርጋለሁ።
እነሆ ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ፤ ባሪያዬንም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፤ በዚችም ምድርና በሚቀመጡባትም ሰዎች ላይ፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ለጥፋትና ለፉጨት ለዘለዓለምም ዕፍረት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም አሳድዳቸዋለሁ፤ ባሳደድሁባቸውም አሕዛብ ሁሉ ዘንድ ለርግማንና ለጥፋት፥ ለማፍዋጫም፥ ለመሰደቢያም እንዲሆኑ በምድር መንግሥታት ሁሉ ዘንድ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
ከእነርሱም የተነሣ በባቢሎን ያሉ የይሁዳ ምርኮኞች ሁሉ፦ የባቢሎን ንጉሥ በእሳት እንደ ጠበሳቸው እንደ ሴዴቅያስና እንደ አክዓብ እግዚአብሔር ያድርግህ የምትባል ርግማንን ያነሣሉ፤
የከለዳውያን ተዋጊዎች ለመዋጋት መጥተዋል፤ ነገር ግን በቍጣዬና በመዓቴ በገደልኋቸው ሰዎች ሬሳዎች እሞላታለሁ፥ ስለ ክፋታቸው ሁሉ ፊቴን ከዚህች ከተማ እመልሳለሁ።
ወደ ግብፅም ይገቡ ዘንድ፥ በዚያም ይቀመጡ ዘንድ ፊታቸውን ያቀኑትን የይሁዳን ቅሬታ እወስዳለሁ፤ ሁሉም ይጠፋሉ፤ በግብፅም ምድር ይወድቃሉ፤ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፤ ከታናሹም ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በሰይፍና በራብ ይሞታሉ፤ ለጥላቻና ለጥፋት፥ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ይሆናሉ።
እግዚአብሔርም ከእንግዲህ ወዲህ የሥራችሁን ክፋትና ያደረጋችሁትን ርኵሰት ይታገሥ ዘንድ አልቻለም፤ ስለዚህ ምድራችሁ ባድማ፥ በረሃና መረገሚያ ሆናለች፤ እስከ ዛሬም የሚኖርባት የለም።
ስለዚህ መዓቴና መቅሠፍቴ ወረደ፤ በይሁዳም ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ነደደ፤ ዛሬም እንደ ሆነው ጠፍና ባድማ ሆኑ።
ሰውነታችሁንም ታጠፉ ዘንድ፥ በምድርም አሕዛብ ሁሉ መካከል መረገሚያና መሰደቢያ ትሆኑ ዘንድ፥ ለመቀመጥ በገባችሁባት በግብፅ ምድር ለሌሎች አማልክት በማጠናችሁ በእጃችሁ ሥራ ለምን ታስቈጡኛላችሁ?
ስለዚህ ቍጣዬን መላሁባቸው፤ ታገሥሁ፤ ፈጽሜም አላጠፋኋቸውም፤ በሜዳ በሕፃናት ላይ በጐልማሶችም ጉባኤ ላይ መዓቴን በአንድነት አፈስስባቸዋለሁ፤ ባል ከሚስቱ ጋር ሽማግሌውም ከጎበዙ ጋር ይያያዛልና።
እንግዲህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰውና በእንስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።”
ዳሌጥ። ቀስቱን እንደ ተቃዋሚ ጠላት ገተረ፤ እንደ ባላጋራም ቀኝ እጁን አጸና፤ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን ለዐይኑ የሚያምረውን ሁሉ ገደለ፤ መዓቱንም እንደ እሳት አፈሰሰ።
ዋው። ማደሪያውን እንደ ወይን ጋረደ፤ በዓሉን ሁሉ አጠፋ፤ እግዚአብሔር በጽዮን ያደረገውን በዓሉንና ሰንበቱን አስረሳ፤ በቍጣውም መዓት ነገሥታቱን፥ አለቆቹንና ካህናቱን አጠፋ።
ካፍ። እግዚአብሔር መዓቱን ፈጽሞአል፤ ጽኑ ቍጣውንም አፍስሶአል፤ እሳትን በጽዮን ውስጥ አቃጠለ፤ መሠረቷንም በላች።
ከአሕዛብም ዘንድ አወጣችኋለሁ፤ ከተበተናችሁባትም ሀገር ሁሉ በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ፥ በፈሰሰችም መዓት እሰበስባችኋለሁ።
ብርም በከውር ውስጥ እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ በውስጥዋ ትቀልጣላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር መዓቴን እንዳፈሰስሁባችሁ ታውቃላችሁ።”
ወደ ከንቱ ነገር ተመለሱ፤ እንደ ጠማማ ቀስትም ሆኑ፤ አለቆቻቸውም ከምላሳቸው ስንፍና የተነሣ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ይህም በግብፅ ምድር ውስጥ መሳለቂያ ይሆንባቸዋል።
የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በአሕዛብ ዘንድ እርግማን እንደ ነበራችሁ፥ እንዲሁ አድናችኋለሁ፥ በረከትም ትሆናላችሁ፣ አትፍሩ፥ እጃችሁንም አበርቱ።
ውኃውን ካጠጣት በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ ራስዋን አርክሳና ባልዋን ቸል ብላው ከሆነ፤ የመርገሙ መራራ ውኃ ወደ ሆድዋ ይገባል፤ ሆድዋንም ይሰነጥቀዋል፤ ጎኗም ይረግፋል፤ ሴቲቱም በሕዝብዋ መካከል ለመርገም ትሆናለች።
እርሱ ደግሞ በቍጣው ጽዋ ሳይቀላቅል ከተዘጋጀው ከእግዚአብሔር ቍጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፤ በቅዱሳንም መላእክትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሰቃያል።