La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 22:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አህ​ያም እን​ደ​ሚ​ቀ​በር ይቀ​በ​ራል፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በር ወደ ውጭ ተጐ​ትቶ፥ በው​ራጅ ጨርቅ ተጠ​ቅ​ልሎ ይጣ​ላል።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አህያ እንደሚቀበር ይቀበራል፤ ከኢየሩሳሌም በሮች ውጪ፤ ተጐትቶ ይጣላል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አህያም እንደሚቀበር ይቀበራል፥ ከኢየሩሳሌምም በር ወደ ውጭ ተጐትቶ ይጣላል።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሬሳውም ክብር አጥቶ እየተጐተተ፥ ከኢየሩሳሌም ቅጽር በር ውጪ ተጥሎ የአህያ አቀባበር ይቀበራል።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አህያም እንደሚቀበር ይቀበራል፥ ከኢየሩሳሌምም በር ወደ ውጭ ተጐትቶ ይጣላል።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 22:19
13 Referencias Cruzadas  

ስለ​ዚህ እነሆ፥ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ላይ መከ​ራን አመ​ጣ​ለሁ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ም​ንም አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ፤ አጥር ተጠ​ግቶ እስ​ከ​ሚ​ሸን ወንድ ድረስ አላ​ስ​ቀ​ር​ለ​ትም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ይነ​ግሥ ዘንድ አል​ተ​ወ​ውም፤ ሰው ገለባ እስ​ኪ​ያ​ልቅ ድረስ እን​ደ​ሚ​ያ​ነ​ድድ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ላይ እሳ​ትን አነ​ዳ​ለሁ።


ኢዮ​አ​ቄ​ምም በነ​ገሠ ጊዜ ሃያ አም​ስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ሄል​ድፍ ትባል ነበር፤ እር​ስ​ዋም የሩማ ሰው የፈ​ዳያ ልጅ ነበ​ረች።


ኢዮ​አ​ቄ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በኦ​ዛም የአ​ት​ክ​ልት ቦታ ተቀ​በረ ልጁም ዮአ​ኪን በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


ሊቀ​ብ​ሩ​አ​ትም በሄዱ ጊዜ ከአ​ና​ቷና ከእ​ግ​ርዋ ተረ​ከዝ ከመ​ዳ​ፍ​ዋም በቀር ምንም አላ​ገ​ኙም።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በእ​ርሱ ላይ ወጥቶ ወደ ባቢ​ሎን ይወ​ስ​ደው ዘንድ በሰ​ን​ሰ​ለት አሰ​ረው።


ሰው መቶ ልጆች ቢወ​ልድ፥ ብዙ ዘመ​ንም በሕ​ይ​ወት ቢኖር፥ ዕድ​ሜ​ውም ብዙ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መል​ካ​ምን ባት​ጠ​ግብ፥ መቃ​ብ​ር​ንም ባያ​ገኝ፥ እኔ ስለ እርሱ፥ “ከእ​ርሱ ይልቅ ጭን​ጋፍ ይሻ​ላል” አልሁ።


ሰይ​ፍን ለመ​ግ​ደል፥ ውሾ​ች​ንም ለመ​ጐ​ተት፥ የሰ​ማ​ያ​ት​ንም ወፎች፥ የም​ድ​ር​ንም አራ​ዊት ለመ​ብ​ላ​ትና ለማ​ጥ​ፋት፥ አራ​ቱን ዓይ​ነት ጥፋት አዝ​ዝ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ስለ​ዚ​ህም ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮ​አ​ቄም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዳ​ዊት ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መጥ ልጅ አይ​ኖ​ር​ለ​ትም፥ ሬሳ​ውም በቀን ለት​ኩ​ሳት፥ በሌ​ሊ​ትም ለው​ርጭ ይጣ​ላል።


አንተ ግን ገብ​ተህ ከአፌ የጻ​ፍ​ኸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በጾም ቀን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሕ​ዝቡ ጆሮ በክ​ር​ታሱ አን​ብብ፤ ደግ​ሞም ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው በሚ​ወጡ በይ​ሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አን​ብ​በው።


በወ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ውና በአ​መ​ለ​ኳ​ቸው፥ በተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውና በፈ​ለ​ጓ​ቸው፥ በሰ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም በፀ​ሐ​ይና በጨ​ረቃ፥ በከ​ዋ​ክ​ብ​ትም፥ በሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ፊት ይዘ​ረ​ጓ​ቸ​ዋል፤ አያ​ለ​ቅ​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ቀ​ብ​ሯ​ቸ​ው​ምም፤ በም​ድ​ርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ።


አሕ​ዛ​ብም በዙ​ሪ​ያው ከየ​ሀ​ገሩ ሁሉ ተሰ​በ​ሰ​ቡ​በት፤ መረ​ባ​ቸ​ው​ንም በእ​ርሱ ላይ ዘረጉ፤ በወ​ጥ​መ​ዳ​ቸ​ውም ተያዘ።


አንተ በሜዳ ፊት ላይ ትወ​ድ​ቃ​ለህ፤ እኔ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።