La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 2:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሁ​ንም ምድ​ርን ያነ​ዋ​ው​ጣት ዘንድ በተ​ነሣ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ፍ​ራ​ትና ከግ​ር​ማው ክብር የተ​ነሣ ወደ ድን​ጋይ ዋሻ ግቡ፤ በመ​ሬት ውስ​ጥም ተሸ​ሸጉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከእግዚአብሔር አስፈሪነትና ከግርማው ሽሽ፤ ወደ ዐለቶች ሂድ፤ በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከጌታ አስፈሪነት ከግርማው ሽሽ፤ ወደ ዐለቶች ሂድ፤ በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከእግዚአብሔር ቊጣና ከአስፈሪ ግርማው ለማምለጥ በአለት ስንጣቂ ዋሻና በመሬት ጒድጓድ ውስጥ ተሸሸጉ!

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከእግዚአብሔር ማስደንገጥና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻ ግባ፥ በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 2:10
22 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግርማ አስ​ደ​ን​ግ​ጦ​ኛ​ልና፤ በእ​ር​ሱም ከመ​ያዝ በም​ክ​ን​ያት ማም​ለጥ አል​ቻ​ል​ሁም።


በአ​ፈር ውስጥ በአ​ን​ድ​ነት ሰው​ራ​ቸው፤ ፊታ​ቸ​ው​ንም በኀ​ፍ​ረት ሙላ።


በመ​ን​ገ​ድህ ሁሉ ይጠ​ብ​ቁህ ዘንድ መላ​እ​ክ​ቱን ስለ አንተ ያዝ​ዛ​ቸ​ዋ​ልና፤


በተ​ጐ​በ​ኛ​ች​ሁ​በት ቀን፥ ምን ታደ​ርጉ ይሆን? መከራ ከሩቅ ይመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ልና፥ ለረ​ድ​ኤ​ትስ ወደ ማን ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ?


እርሱ ክፉ እንደ አደ​ረ​ገና እንደ አጠፋ በእ​ርሱ ላይ እጁን ያነ​ሣል፤ በእ​ር​ሱም ላይ እጁን ያነ​ሣው ስድ​ብን ይሽ​ራል።


እነሆ፥ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ ሕዝቡ የተ​በ​ዘ​በ​ዘና የተ​ዘ​ረፈ ነው፤ ወጥ​መድ በሁ​ሉም ቦታ በዋ​ሻ​ዎ​ችና እነ​ር​ሱን በሸ​ሸ​ጉ​ባ​ቸው ቤቶች ተጠ​ም​ዶ​አል፤ ብዝ​በዛ ሆነ​ዋል፤ የሚ​ያ​ድ​ንም የለም፤ ምር​ኮም ሆነ​ዋል፤ የሚ​ያ​ስ​ጥ​ላ​ቸ​ውም የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እው​ነ​ተኛ አም​ላክ ነው፤ እር​ሱም ሕያው አም​ላ​ክና የዘ​ለ​ዓ​ለም ንጉሥ ነው፤ ከቍ​ጣው የተ​ነሣ ምድር ትን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣ​ለች፤ አሕ​ዛ​ብም መዓ​ቱን አይ​ች​ሉም።


የአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ሆይ! በአ​ሕ​ዛብ ጥበ​በ​ኞች ሁሉ መካ​ከል፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ​ሌለ፥ ለአ​ንተ ክብር ይገ​ባ​ልና አን​ተን የማ​ይ​ፈራ ማን ነው?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እን​ዲሁ የይ​ሁ​ዳን ትዕ​ቢት፥ ታላ​ቁ​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ትዕ​ቢት አበ​ላ​ሻ​ለሁ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ኀጢ​አት የሆ​ኑት የአ​ዎን የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ይፈ​ር​ሳሉ፤ እሾ​ህና አሜ​ከ​ላም በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ላይ ይበ​ቅ​ላሉ፤ ተራ​ሮ​ች​ንም፥ “ክደ​ኑን፤ ኮረ​ብ​ቶ​ች​ንም፦ ውደ​ቁ​ብን” ይሉ​አ​ቸ​ዋል።


አንቺም ትሰክሪአለሽ ወራዳም ትሆኛለሽ፣ አንቺ ደግሞ ከጠላት የተነሣ መጠጊያን ትፈልጊአለሽ።


ነገር ግን፤ የም​ት​ፈ​ሩ​ትን አሳ​ያ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተስ ከገ​ደለ በኋላ ወደ ገሃ​ነም ሊጥል ሥል​ጣን ያለ​ውን ፍሩት፤ አዎ፥ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እር​ሱን ፍሩ።


ያን​ጊ​ዜም ተራ​ሮ​ችን ‘በላ​ያ​ችን ውደቁ፤ ኮረ​ብ​ቶ​ች​ንም ሰው​ሩን’ ይሉ​አ​ቸ​ዋል።


በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊደነቅ ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኀይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።