ኢሳይያስ 42:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 እነሆ፥ ተመለከትሁ፤ ሕዝቡ የተበዘበዘና የተዘረፈ ነው፤ ወጥመድ በሁሉም ቦታ በዋሻዎችና እነርሱን በሸሸጉባቸው ቤቶች ተጠምዶአል፤ ብዝበዛ ሆነዋል፤ የሚያድንም የለም፤ ምርኮም ሆነዋል፤ የሚያስጥላቸውም የለም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ይህ ሕዝብ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ፣ በጕድጓድ ውስጥ የተጠመደበት፣ በወህኒ ቤት የተዘጋበት ነው፤ ተበዝብዘዋል፣ የሚያድናቸውም የለም፤ ተማርከዋል፣ “መልሷቸው” የሚልም የለም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ይህ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ ሕዝብ ነው፤ ሁሉም በዋሻ ውስጥ ተጠምደዋል፤ በግዞት ቤትም ተሸሽገዋል፤ ተበዝብዘዋል የሚያድንም የለም፥ ተማርከዋል፤ “መልሷቸው” የሚል ማንም የለም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ሕዝቡ ግን ተዘርፈውና ተበዝብዘው በዋሻ ውስጥ ተዘግቶባቸዋል፤ በወህኒ ቤትም ተሸሽገዋል። ተዘረፉ፤ ተበዘበዙ፤ ማንም በመታደግ ሊያድናቸው አልቻለም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ይህ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ ሕዝብ ነው፥ ሁላቸው በዋሻ ውስጥ ተጠምደዋል በግዞት ቤትም ተሸሽገዋል፥ ብዝበዛ ሆነዋል የሚያድንም የለም፥ ምርኮም ሆነዋል፥ ማንም፦ መልሱ አይልም። Ver Capítulo |