Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከጌታ አስፈሪነት ከግርማው ሽሽ፤ ወደ ዐለቶች ሂድ፤ በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከእግዚአብሔር አስፈሪነትና ከግርማው ሽሽ፤ ወደ ዐለቶች ሂድ፤ በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከእግዚአብሔር ቊጣና ከአስፈሪ ግርማው ለማምለጥ በአለት ስንጣቂ ዋሻና በመሬት ጒድጓድ ውስጥ ተሸሸጉ!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አሁ​ንም ምድ​ርን ያነ​ዋ​ው​ጣት ዘንድ በተ​ነሣ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ፍ​ራ​ትና ከግ​ር​ማው ክብር የተ​ነሣ ወደ ድን​ጋይ ዋሻ ግቡ፤ በመ​ሬት ውስ​ጥም ተሸ​ሸጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ከእግዚአብሔር ማስደንገጥና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻ ግባ፥ በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 2:10
22 Referencias Cruzadas  

የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል በመንግሥታቸውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ ሌለ፥ አንተን መፍራት ይገባልና አንተን የማይፈራ ማን ነው?


ከጌታ ፊት ከኃይሉም ክብር ርቀው በዘለዓለም ጥፋት ይቀጣሉ።


በዚያን ጊዜ ተራራዎችን ‘በላያችን ውደቁ፤’ ኮረብቶችንም ‘ሰውሩን፤’ ማለት ይጀምራሉ፤


ማንን መፍራት እንደሚገባችሁ አሳያችኋለሁ፤ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ለመጣል ሥልጣን ያለውን ፍሩ። አዎን እላችኋለሁ እርሱን ፍሩ።


የእስራኤል ኃጢአት የሆኑት የአዌን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ እሾኽና አሜከላ በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላል፤ እነርሱም ተራሮችን፦ “ሸፍኑን!” ኮረብቶችንም፦ “ውደቁብን!” ይሉአቸዋል።


ጌታ ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቁጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን መቋቋም አይችሉም።


ይህ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ ሕዝብ ነው፤ ሁሉም በዋሻ ውስጥ ተጠምደዋል፤ በግዞት ቤትም ተሸሽገዋል፤ ተበዝብዘዋል የሚያድንም የለም፥ ተማርከዋል፤ “መልሷቸው” የሚል ማንም የለም።


በምትጎበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?


የቁጣህን ጽናት ማን ያውቃል? የቁጣህንስ ግርማ ማን ያውቃል?


የእግዚአብሔር መዓት አስደንግጦኛልና፥ በክብሩም ፊት ምንም ለማድረግ አልቻልሁም።”


በአፈር ውስጥ በአንድነት ሰውራቸው፥ በተሸሸገም ስፍራ ፊታቸውን ሸፍን።


ለሰው ልጆች ኃይልህን የመንግሥትህንም ግርማ ክብር ያስታውቁ ዘንድ


ዋናተኛም ሲዋኝ እጁን እንደሚዘረጋ፥ እንዲሁ በመካከሉ እጁን ይዘረጋል፤ ነገር ግን ትዕቢቱን ከእጁ ተንኮል ጋር ያዋርዳል።


“ጌታ እንዲህ ይላል፦ እንዲሁ የይሁዳን ትዕቢት ታላቁንም የኢየሩሳሌምን ትዕቢት አጠፋለሁ።


አንቺ ደግሞ ትሰክሪአለሽ፥ ትደበቂያለሽ፤ አንቺ ደግሞ ከጠላት የተነሣ መጠጊያን ትፈልጊአለሽ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios