La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕንባቆም 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፣ የሚናገረኝንም፥ ስለ ክርክሬም የምመልሰውን አውቅ ዘንድ እመለከታለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፤ በምሽጉ ቅጥር ላይ ወጥቼ እቈያለሁ፤ ምን እንደሚለኝ፣ ለክርክሩም የምሰጠውን መልስ ለማወቅ እጠባበቃለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፤ ምን እንደሚለኝና በአቤቱታዬም ምን መልስ እንደምሰጥ ለማየት እጠባበቃለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በጥበቃ ቦታዬ እቆማለሁ በግንቡ ጫፍ ላይም ቦታዬን እይዛለሁ፤ እግዚአብሔር ምን እንደሚለኝ ለጥያቄዬም ምን መልስ እንደሚሰጥ እጠባበቃለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፥ የሚናገረኝንም፥ ስለ ክርክሬም የምመልሰውን አውቅ ዘንድ እመለከታለሁ።

Ver Capítulo



ዕንባቆም 2:1
23 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም በሁ​ለት በር መካ​ከል ተቀ​ምጦ ነበር፤ ዘበ​ኛ​ውም በቅ​ጥሩ ላይ ወዳ​ለው ወደ በሩ ሰገ​ነት ወጣ፤ ዐይ​ኑ​ንም አቅ​ንቶ ብቻ​ውን የሚ​ሮጥ ሰው አየ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በአ​ም​ላ​ካ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ቅን ያል​ሆ​ነን ነገር በስ​ውር አደ​ረጉ፤ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ከዘ​በ​ኞች ግንብ ጀምሮ እስከ ተመ​ሸ​ገች ከተማ ድረስ በከ​ፍ​ታ​ዎች ላይ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠሩ።


ሰላ​ይም ያያ​ቸው ዘንድ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ግንብ ላይ ቆመ፤ ሲመ​ጡም የእ​ነ​ኢ​ዩን አቧራ አየ። “እነ​ሆም፥ አቧራ አያ​ለሁ” አለ። ኢዮ​ራ​ምም፥ “ይገ​ና​ኛ​ቸው ዘንድ አንድ ፈረ​ሰኛ ይሂድ፤ እር​ሱም፦ ሰላም ነውን? ይበ​ላ​ቸው” አለ።


የሚ​ያ​ደ​ም​ጠ​ኝን ማን በሰ​ጠኝ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እጅ አል​ፈ​ራሁ እንደ ሆነ፥ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ር​ድ​ብኝ የክስ ጽሑፍ ምነው በኖ​ረኝ!


ከባለ ዕዳዬ የም​ቀ​በ​ለው ሳይ​ኖር ቀድ​ጀው እመ​ለ​ሳ​ለሁ።


በማ​ለዳ ቃሌን ስማኝ፥ በማ​ለዳ በፊ​ትህ እቆ​ማ​ለሁ፥ እገ​ለ​ጥ​ል​ሃ​ለ​ሁም።


አቤቱ፥ ከአ​ማ​ል​ክት የሚ​መ​ስ​ልህ የለም፥ እንደ ሥራ​ህም ያለ የለም።


የፈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው አሕ​ዛብ ሁሉ ይምጡ፥ አቤቱ፥ በፊ​ት​ህም ይስ​ገዱ፥ ስም​ህ​ንም ያክ​ብሩ፤


ማዕ​ዱን አዘ​ጋጁ፤ ብሉ፤ ጠጡ፤ እና​ንተ አለ​ቆች ሆይ፥ ተነሡ፤ ጋሻ​ው​ንም አዘ​ጋጁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ​ኛ​ልና፥ “ፈጥ​ነህ ሂድ፤ ጕበ​ኛ​ንም አቁም፤ የሚ​ያ​የ​ው​ንም ይና​ገር፤ የሚ​ሰ​ማ​ው​ንም ያውራ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጕበኛ ኦር​ያስ ተጠራ፤ እር​ሱም፥ “እነሆ እኔ አለሁ፤ መላ መዓ​ል​ቱ​ንና መላ ሌሊ​ቱን በማማ ላይ ቆሜ አለሁ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ሽን በቅ​ጥ​ርሽ ላይ ቀንና ሌሊት አቁ​ሜ​አ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ስቡ ከቶ ዝም አይ​ሉም፤


አቤቱ! ከአ​ንተ ጋር በተ​ም​ዋ​ገ​ትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአ​ንተ ጋር ስለ ፍርድ ልና​ገር። የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች መን​ገድ ስለ ምን ይቀ​ናል? በደ​ል​ንስ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላ​ቸ​ዋል?


እኔም፥ “የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ አድ​ምጡ” ብዬ ጠባ​ቂ​ዎ​ችን ሾም​ሁ​ባ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን፥ “አና​ዳ​ም​ጥም” አሉ።


“የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጕበኛ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ የአ​ፌን ቃል ስማ፤ በቃ​ሌም ገሥ​ጻ​ቸው።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጕበኛ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ከአፌ ቃሌን ስማ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቃ​ቸው።


እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ፥ አምላኬም ይሰማኛል።


ክር​ስ​ቶስ በእኔ አድሮ እን​ደ​ሚ​ና​ገር ማስ​ረጃ ትሻ​ላ​ች​ሁና፤ እር​ሱም ሁሉ የሚ​ቻ​ለው ነው እንጂ፥ በእ​ና​ንተ ዘንድ የሚ​ሳ​ነው የለም።


በስ​ሙም ለአ​ሕ​ዛብ ወን​ጌ​ልን አስ​ተ​ምር ዘንድ፥ በእ​ጄም የልጁ ክብር ይታ​ወቅ ዘንድ ልጁን ገለ​ጠ​ልኝ፤ ያን​ጊ​ዜም ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ሰው ጋር አል​ተ​ማ​ከ​ር​ሁም።