Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 21:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጕበኛ ኦር​ያስ ተጠራ፤ እር​ሱም፥ “እነሆ እኔ አለሁ፤ መላ መዓ​ል​ቱ​ንና መላ ሌሊ​ቱን በማማ ላይ ቆሜ አለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ጠባቂው ጮኸ፤ እንዲህም አለ፤ “ጌታ ሆይ፤ በየቀኑ ማማ ላይ ቆሜአለሁ፤ በየሌሊቱም በቦታዬ አለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ያየውም፦ ጌታ ሆይ፥ ቀኑን ሁሉ ዘወትር በማማ ላይ ቆሜአለሁ፥ ሌሊቱንም ሁሉ በመጠበቂያዬ ላይ ተተክያለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ዘብ ጠባቂው “ጌታዬ ሆይ! እኔ በማማዬ ላይ ሆኜ ሌት ከቀን በመጠበቅ ላይ ነኝ” ይላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ያየውም፦ ጌታ ሆይ፥ ቀኑን ሁሉ ዘወትር በማማ ላይ ቆሜአለሁ፥ ሌሊቱንም ሁሉ በመጠበቂያዬ ላይ ተተክያለሁ፥

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 21:8
12 Referencias Cruzadas  

የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ወደ ምድረ በዳው መጠ​በ​ቂያ ግንብ በመጡ ጊዜ ሕዝ​ቡን አዩ፤ እነ​ሆም፥ በም​ድሩ ሁሉ ሬሳ ሞልቶ ነበር፤ ያመ​ለ​ጠም ሰው አል​ነ​በ​ረም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩት ሁሉ፥ በመ​ን​ገ​ዶ​ቹም የሚ​ሄዱ ብፁ​ዓን ናቸው።


ዐመ​ፃን ፈለ​ጓት፥ ሲፈ​ት​ኑም ሲጀ​ም​ሩም አለቁ፤ ሰው በጥ​ልቅ ልብ ውስጥ ይገ​ባል፥


ጩኸ​ታ​ቸው እንደ አን​በሳ ነው፤ እንደ አን​በሳ ደቦ​ሎ​ችም ይቆ​ማሉ፤ ከጕ​ድ​ጓዱ እን​ደ​ሚ​ወጣ አው​ሬም ይነ​ጥ​ቃሉ፤ ይጮ​ሃሉ፤ የሚ​ድ​ንም የለም።


ሁሉም ዕው​ራን እንደ ሆኑ ኑና እዩ፤ ሁሉ ያለ ዕው​ቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ ይጮ​ኹም ዘንድ አይ​ች​ሉም፤ በመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ሕል​ምን ያል​ማሉ፤ ማን​ቀ​ላ​ፋ​ት​ንም ይወ​ድ​ዳሉ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ሽን በቅ​ጥ​ርሽ ላይ ቀንና ሌሊት አቁ​ሜ​አ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ስቡ ከቶ ዝም አይ​ሉም፤


እንደ አን​በሳ መደ​ቡን ለቅ​ቆ​አል፤ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ሰል​ፍና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ የተ​ነሣ ምድ​ራ​ቸው ምድረ በዳ ሆና​ለ​ችና።”


አን​በሳ ከጕ​ድ​ጓዱ ወጥ​ቶ​አል፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው የሚ​ዘ​ርፍ ተነ​ሥ​ቶ​አል፤ ምድ​ር​ሽን ባድማ ያደ​ርግ ዘንድ፥ ከተ​ሞ​ች​ሽ​ንም ሰው እን​ዳ​ይ​ኖ​ር​ባ​ቸው ያፈ​ር​ሳ​ቸው ዘንድ ከስ​ፍ​ራው ወጥ​ቶ​አል።


እነሆ ከእ​ር​ስዋ ዘንድ በቶሎ አባ​ር​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ዳር ወደ ኤታም እንደ አን​በሳ ይወ​ጣል፤ ጐል​ማ​ሶ​ች​ንም በእ​ር​ስዋ ላይ እሾ​ማ​ለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚ​ወ​ስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚ​ቃ​ወም እረኛ ማን ነው?”


እነሆ ከእ​ር​ስዋ ዘንድ በቶሎ አባ​ር​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና እንደ አን​በሳ ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ዳር ወደ ኤታም ምድር ይወ​ጣል፤ ጐል​ማ​ሶ​ቹ​ንም ሁሉ በእ​ር​ስዋ ላይ እሾ​ማ​ለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚ​ወ​ስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚ​ቋ​ቋም እረኛ ማን ነው?


በመጠን ኑሩ፤ ንቁም፤ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos