ዘፍጥረት 41:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋም ጊዜ መንፈሱ ታወከችበት፤ የግብፅ ሕልም ተርጓሚዎችንና ጠቢባንን ሁሉ ልኮ አስጠራቸው፤ ፈርዖንም ሕልሙን ነገራቸው፤ ነገር ግን ከእነርሱ ለፈርዖን ሕልሙን የሚተረጕምለት አልተገኘም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በነጋታውም ፈርዖን መንፈሱ ታወከበት፤ ስለዚህ በግብጽ አገር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች በሙሉ አስጠርቶ ሕልሞቹን ነገራቸው፤ ይሁን እንጂ ሕልሞቹን ሊተረጕምለት የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነጋታውም ፈርዖን መንፈሱ ታወከበት፤ ስለዚህ በግብጽ አገር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች በሙሉ አስጠርቶ ሕልሞቹን ነገራቸው፥ ይሁን እንጂ ሕልሞቹን ሊተረጉምለት የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠዋት ከመኝታው ሲነሣ መንፈሱ ታወከ፤ ስለዚህ በግብጽ ምድር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች ሁሉ አስጠርቶ ሕልሙን ነገራቸው፤ ነገር ግን የሕልሞቹን ትርጒም ለመግለጥ የቻለ አንድ እንኳ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ነቃ እነሆም ሕልም ነበረ። በነጋም ጊዜ ነፍሱ ታወከችበት ወደ ሕልም ተርጕሚዎች ሁሉ ወድ ግብፅ ጠቢባንም ሁሉ ልኮ ወደ እርሱ ጠራቸው ፈርዖንም ሕልሙን ነገራቸው ነገር ግን ከእነርሱ ለፈርዖን የሚተረጕም አልተገኘም። |
እነርሱም፥ “ሕልምን አልመን የሚተረጕምልን አጣን” አሉት። ዮሴፍም አላቸው፥ “ሕልምን የሚተረጕም እግዚአብሔር የሰጠው አይደለምን? እስቲ ንገሩኝ፤ ሕልማችሁ ምንድን ነው?”
ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፥ “ሕልምን አየሁ፤ የሚተረጕምልኝም አጣሁ፤ ሕልምን እንደ ሰማህ፥ እንደ ተረጐምህም ስለ አንተ ሰማሁ።”
እነዚያ የሰለቱትና በነፋስ የተመቱት እሸቶች እነዚያን ያማሩትንና የጐመሩትን ሰባቱን እሸቶች ዋጡአቸው። ለሕልም ተርጓሚዎችም ሕልሜን ነገርሁ፤ የተረጐመልኝም የለም።”
እነዚያም የሰለቱና ነፋስ የመታቸው እሸቶች ሰባቱን ያማሩና የጐመሩ እሸቶች ዋጡአቸው። ፈርዖንም ነቃ፤ እነሆም ሕልም ነበር።
የግብፅም ጠንቋዮች በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ የፈርዖን ልብ ጸና፤ አልሰማቸውምም።
ጠንቋዮችም ቍስል ስለ ነበረባቸው በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፤ ቍስል ጠንቋዮችንና ግብፃውያንን ሁሉ ይዞአቸው ነበርና።
የግብፅም መንፈስ በውስጣቸው ትደነግጣለች፤ ምክራቸውን አጠፋለሁ፤ እነርሱም አማልክቶቻቸውንና ጣዖቶቻቸውን፥ ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎቻቸውንም ይጠይቃሉ።
ስለዚህ፥ እነሆ፥ ይህ ሕዝብ በድጋሚ እንዲፈልስ አደርጋለሁ፤ አፈልሳቸዋለሁም፤ የጥበበኞችንም ጥበብ አጠፋለሁ፤ የአስተዋዮችንም ማስተዋል እሰውራለሁ።”
እነርሱም፥ “ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ጠይቁ” ባሉአችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአምላኩ መጠየቅ አይገባውምን? ወይስ ለሕያዋን ሲሉ ሙታንን ይጠይቃሉን?
“ወደ መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቋዮች አትሂዱ፤ እንዳትረክሱባቸውም አትፈልጉአቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
“እነርሱን ተከትሎ ያመነዝር ዘንድ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን የሚከተል ሰው ቢኖር፥ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይች አጠፋዋለሁ።
እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፣ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፣ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፣ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፣ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።
ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና” እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
የኤፌቆሮስን ትምህርት ከተማሩ ፈላስፋዎች መካከልና ረዋቅያውያን ከሚባሉት ወገን የሆኑ ሌሎች ፈላስፎችም የተከራከሩት ነበሩ፤ እኩሌቶችም፥ “ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይፈልጋል?” ይሉ ነበር፤ ሌሎችም፥ “ስለ ኢየሱስ ከሙታን ስለ መነሣቱም ሰብኮላቸዋልና የአዲስ አምላክ ትምህርትን ያስተምራል” አሉ።
ፍልስጥኤማውያንም ካህናትንና ምዋርተኞችን ጠንቋዮችንም ጠርተው፥ “በእግዚአብሔር ታቦት ላይ ምን እናድርግ? ወደ ስፍራዋስ በምን እንስደዳት? አስታውቁን” አሉ።