Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 41:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እነ​ዚ​ያም የሰ​ለ​ቱና ነፋስ የመ​ታ​ቸው እሸ​ቶች ሰባ​ቱን ያማ​ሩና የጐ​መሩ እሸ​ቶች ዋጡ​አ​ቸው። ፈር​ዖ​ንም ነቃ፤ እነ​ሆም ሕልም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የቀጨጩት የእሸት ዛላዎች፣ ፍሬአቸው የተንዠረገገውን ሰባቱን ያማሩ ዛላዎች ዋጧቸው። በዚህ ጊዜ ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ፤ ነገሩ ሕልም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የቀጨጩት የእሸት ዛላዎች፥ ፍሬያቸው የተንዠረገገውን ሰባቱን ያማሩ ዛላዎች ዋጡአቸው። በዚህ ጊዜ ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ፤ ነገሩ ሕልም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ሰባቱም የቀጨጩ የእሸት ዛላዎች፥ ሰባቱን የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጡአቸው፤ ንጉሡም ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ ሕልም ማየቱን ተገነዘበ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የሰለቱትም እሽቶች ስባቱን ያማሩና የዳበሩ እሸቶች ዋጡአቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 41:7
5 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያች ሌሊ​ትም አቤ​ሜ​ሌክ ተኝቶ ሳለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ልም ወደ እርሱ መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰ​ድ​ሃት ሴት ትሞ​ታ​ለህ፤ እር​ስዋ ባለ ባል ናትና።”


ዮሴ​ፍም ሕል​ምን አለመ፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ነገ​ራ​ቸው።


እነ​ሆም፥ ከእ​ነ​ርሱ በኋላ የሰ​ለ​ቱና በነ​ፋስ የተ​መቱ ሰባት እሸ​ቶች ወጡ፤


በነ​ጋም ጊዜ መን​ፈሱ ታወ​ከ​ች​በት፤ የግ​ብፅ ሕልም ተር​ጓ​ሚ​ዎ​ች​ንና ጠቢ​ባ​ንን ሁሉ ልኮ አስ​ጠ​ራ​ቸው፤ ፈር​ዖ​ንም ሕል​ሙን ነገ​ራ​ቸው፤ ነገር ግን ከእ​ነ​ርሱ ለፈ​ር​ዖን ሕል​ሙን የሚ​ተ​ረ​ጕ​ም​ለት አል​ተ​ገ​ኘም።


ሰሎ​ሞ​ንም ነቃ፤ እነ​ሆም፥ ሕልም ነበረ፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሄደ፤ በጽ​ዮ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆመ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አሳ​ረገ፤ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ሁሉ ታላቅ ግብዣ አደ​ረገ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos