Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 41:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በነጋታውም ፈርዖን መንፈሱ ታወከበት፤ ስለዚህ በግብጽ አገር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች በሙሉ አስጠርቶ ሕልሞቹን ነገራቸው፥ ይሁን እንጂ ሕልሞቹን ሊተረጉምለት የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በነጋታውም ፈርዖን መንፈሱ ታወከበት፤ ስለዚህ በግብጽ አገር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች በሙሉ አስጠርቶ ሕልሞቹን ነገራቸው፤ ይሁን እንጂ ሕልሞቹን ሊተረጕምለት የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ጠዋት ከመኝታው ሲነሣ መንፈሱ ታወከ፤ ስለዚህ በግብጽ ምድር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች ሁሉ አስጠርቶ ሕልሙን ነገራቸው፤ ነገር ግን የሕልሞቹን ትርጒም ለመግለጥ የቻለ አንድ እንኳ አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በነ​ጋም ጊዜ መን​ፈሱ ታወ​ከ​ች​በት፤ የግ​ብፅ ሕልም ተር​ጓ​ሚ​ዎ​ች​ንና ጠቢ​ባ​ንን ሁሉ ልኮ አስ​ጠ​ራ​ቸው፤ ፈር​ዖ​ንም ሕል​ሙን ነገ​ራ​ቸው፤ ነገር ግን ከእ​ነ​ርሱ ለፈ​ር​ዖን ሕል​ሙን የሚ​ተ​ረ​ጕ​ም​ለት አል​ተ​ገ​ኘም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ፈርዖንም ነቃ እነሆም ሕልም ነበረ። በነጋም ጊዜ ነፍሱ ታወከችበት ወደ ሕልም ተርጕሚዎች ሁሉ ወድ ግብፅ ጠቢባንም ሁሉ ልኮ ወደ እርሱ ጠራቸው ፈርዖንም ሕልሙን ነገራቸው ነገር ግን ከእነርሱ ለፈርዖን የሚተረጕም አልተገኘም።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 41:8
39 Referencias Cruzadas  

በማግስቱ ጧት ዮሴፍ ወደ እነርሱ ሲገባ ተክዘው አገኛቸው።


እነርሱም “ሁለታችንም ሕልም አየን፤ ነገር ግን የሚተረጉምልን ሰው አጣን” ሲሉ መለሱለት። ዮሴፍም፥ “ሁልጊዜስ ቢሆን የሕልም ትርጓሜ ከእግዚአብሔር የሚገኝ አይደለምን? እስቲ ያያችሁትን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።


ፈርዖንም ዮሴፍን፥ “ሕልም አይቼ ነበር፤ ሕልሜን ሊተረጉምልኝ የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም፤ አንተ ግን ሕልም ሲነገርህ የመተርጐም ችሎታ እንዳለህ ሰማሁ” አለው።


የቀጨጩት የእሸት ዛላዎችም ሰባቱን ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጧቸው፤ ይህንኑም ለአስማተኞች ነገርሁ፤ ነገር ግን ማንም ሊፈታው አልቻለም።”


የቀጨጩት የእሸት ዛላዎች፥ ፍሬያቸው የተንዠረገገውን ሰባቱን ያማሩ ዛላዎች ዋጡአቸው። በዚህ ጊዜ ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ፤ ነገሩ ሕልም ነበር።


ጌታ ለሚፈሩት ወዳጃቸው ነው፥ ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል።


ፈርዖንም ጠቢባንንና አስማተኞችን ጠራ፤ የግብጽም አስማተኞች ደግሞ በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ።


የግብጽም አስማተኞች በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ፤ የፈርዖንም ልብ ጸና፥ ጌታም እንደ ተናገረ አልሰማቸውም።


እንቁራሪቶቹን ከአንተ ከቤቶችህም ከአገልጋዮችህም ከሕዝብህም ያርቃል፤ በዓባይ ወንዝ ብቻ ይቀራሉ።”


ብጉንጅ በጠንቋዮቹና በግብጻውያን ሁሉ ላይ ነበር፤ ጠንቋዮቹም ብጉንጅ ስለ ነበረባቸው በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፤


የግብጽም መንፈስ በውስጥዋ ባዶ ይሆናል፥ ዕቅዳቸውንም መና አስቀራለሁ፤ እነርሱም ጣዖቶቻቸውን፥ የሙታን መናፍስትን፥ መናፍስት ጠሪዎቻቸውንና የጠንቋዮቻቸውን ምክር ይጠይቃሉ።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ ድንቅ ነገርን በዚህ ሕዝብ መካከል፥ አስደማሚ ነገርን ተአምራትንም እንደገና አደርጋለሁ፤ የጥበበኞችም ጥበብ ትጠፋለች፥ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።


ሰዎች፤ የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሹኩትን ሟርተኞችንና መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ ቢሏችሁ፤ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕያዋን ምትክ ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ?


“ወደ ሙታን መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቋዮች አትሂዱ፤ በእነርሱም እንዳትረክሱ አትፈልጉአቸው፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።


“የሙታን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም በሚከተል፥ በሥራቸውም በሚያመነዝር፥ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቊራለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።


እኔ ሰምቻለሁ፥ አንጀቴ ራደብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መበስበስ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በውስጤም ተንቀጠቀጥሁ፥ በአስጨነቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፥ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።


ኢየሱስም በይሁዳ ቤተልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፥


ከኤፊቆሮስ ወገንና ኢስጦኢኮችም ከተባሉት ፈላስፎች አንዳንዶቹ ከእርሱ ጋር ተገናኙ። አንዳንዶቹም “ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይወዳል?” አሉ፤ ሌሎችም የኢየሱስንና የትንሣኤውን ወንጌል ስለ ሰበከላቸው “አዲሶችን አማልክት የሚያወራ ይመስላል፤” አሉ።


ሙሴም የግብጾችን ጥበብ ሁሉ ተማረ፤ በቃሉና በሥራውም የበረታ ሆነ።


“የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የአስተዋዮችንም ማስተዋል እጥላለሁ፤” ተብሎ ተጽፎአልና።


ፍልስጥኤማውያን ካህናትንና ጠንቋዮችን ጠርተው፥ “የጌታን ታቦት ምን እናድርገው? ወደ ስፍራው እንዴት መመለስ እንደሚገባን ንገሩን” አሏቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos