La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሴቲ​ቱን፥ “ይህን ለምን አደ​ረ​ግሽ?” አላት። ሴቲ​ቱም አለች፥ “እባብ አሳ​ተ​ኝና በላሁ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር አምላክ ሴቲቱን፣ “ይህ ያደረግሽው ምንድን ነው?” አላት። እርሷም፣ “እባብ አሳሳተኝና በላሁ” አለች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ እግዚአብሔርም ሴቲቱን፦ “ይህ ያደረግሽው ምንድነው?” አላት። ሴቲቱም፥ “እባብ አሳተኝና በላሁ” አለች።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን “ይህ ያደረግሽው ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቃት። እርስዋም “እባብ አታለለኝና በላሁ” አለች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፦ ይህ ያደረግሽው ምንድር ነው? አላት። ሴቲቱም አለች፦ እባብ አሳተኝና በላሁ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 3:13
15 Referencias Cruzadas  

ፈር​ዖ​ንም አብ​ራ​ምን ጠርቶ አለው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብኝ ምን​ድን ነው? እር​ስዋ ሚስ​ትህ እንደ ሆነች ለምን አል​ገ​ለ​ጥ​ህ​ል​ኝም?


ዮሴ​ፍም፥ “ይህ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ነገር ምን​ድን ነው? እንደ እኔ ያለ ሰው ምሥ​ጢ​ርን እን​ዲ​ያ​ውቅ አታ​ው​ቁ​ምን?” አላ​ቸው።


ኢዮ​አ​ብም ወደ ንጉሥ ገብቶ፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ነገር ምን​ድን ነው? እነሆ፥ አበ​ኔር መጥ​ቶ​ልህ ነበር፤ በደ​ኅና እን​ዲ​ሄድ ስለ​ምን አሰ​ና​በ​ት​ኸው?


እር​ሱም፥ “እኔ ደግሞ እን​ዳ​ንተ ነቢይ ነኝ፤ መል​አ​ክም፦ እን​ጀራ ይበላ ዘንድ ውኃም ይጠጣ ዘንድ ከአ​ንተ ጋር ወደ ቤትህ መል​ሰው ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ተና​ገ​ረኝ” አለው። ዋሽ​ቶም ተና​ገ​ረው።


ሴት ልጅም ብት​ወ​ልድ እንደ ግዳ​ጅዋ ወራት ሁለት ሳም​ንት ያህል የረ​ከ​ሰች ናት፤ ከደ​ም​ዋም እስ​ክ​ት​ነጻ ድረስ ስድሳ ስድ​ስት ቀን ትቈይ።


እነ​ዚ​ያም ሰዎች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ኰበ​ለለ እርሱ ስለ ነገ​ራ​ቸው ዐው​ቀ​ዋ​ልና እጅግ ፈር​ተው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ምን​ድን ነው?” አሉት።


ጲላ​ጦ​ስም መልሶ፥ “እኔ አይ​ሁ​ዳዊ ነኝን? ለእኔ አሳ​ል​ፈው የሰ​ጡህ ወገ​ኖ​ች​ህና ሊቃነ ካህ​ናት አይ​ደ​ሉ​ምን? Aረ ምን አድ​ር​ገ​ሃል?” አለው።


ኀጢ​አት በዚ​ያች ትእ​ዛዝ ምክ​ን​ያት አሳ​ተ​ችኝ፤ በእ​ር​ሷም ገደ​ለ​ችኝ።


ነገር ግን እባብ ሔዋ​ንን በተ​ን​ኰሉ እን​ዳ​ሳ​ታት፥ አሳ​ባ​ችሁ ከክ​ር​ስ​ቶስ የዋ​ህ​ነ​ትና ንጽ​ሕና ምና​ል​ባት እን​ዳ​ይ​ለ​ወጥ ብዬ እፈ​ራ​ለሁ።


የተታለለም አዳም አይደለም፤ ሴቲቱ ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፤


ሳሙ​ኤ​ልም፥ “ያደ​ረ​ግ​ኸው ምን​ድን ነው?” አለ። ሳኦ​ልም፥ “ሕዝቡ ከእኔ ተለ​ይ​ተው እንደ ተበ​ታ​ተኑ፥ አን​ተም በነ​ገ​ር​ኸኝ መሠ​ረት በቀ​ጠ​ሮው ቀን እን​ዳ​ል​መ​ጣህ፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወደ ማኪ​ማስ እንደ ተሰ​በ​ሰቡ አየሁ፤


ሳኦ​ልም፦“ሕዝቡ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠ​ዉ​አ​ቸው ዘንድ ከበ​ጎ​ችና ከላ​ሞች መን​ጋ​ዎች መል​ካም መል​ካ​ሙን አድ​ነ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን አመ​ጣን፤ የቀ​ሩ​ት​ንም ፈጽሜ አጠ​ፋሁ” አለው።