ዘፍጥረት 27:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብ ይገዙልህ፤ አለቆችም ይስገዱልህ፤ ለወንድምህ ጌታ ሁን፤ የአባትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን፤ የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችም ተደፍተው እጅ ይንሡህ፤ የወንድሞችህ ጌታ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ተደፍተው እጅ ይንሡህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚባርኩህ የተባረኩ ይሁኑ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ፥ ለወንድሞችህ ጌታ ሁን፥ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፥ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችም ያገልግሉህ፤ በወንድሞችህ ሁሉ ላይ አለቃ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚመርቁህም የተመረቁ ይሁኑ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለወንድሞችህ ጌት ሁን የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን የሚባርክህም ቡሩም ይሁን። |
ይስሐቅም መለሰ ዔሳውንም አለው፥ “እነሆ ጌታህ አደረግሁት፤ ወንድሞቹንም ሁሉ ለእርሱ ተገዦች አደረግኋቸው፤ እህሉን፥ ወይኑንና ዘይቱንም አበዛሁለት፤ ለአንተ ግን፥ ልጄ ሆይ፥ ምን ላድርግልህ?”
በሰይፍህም ትኖራለህ፤ ለወንድምህም ትገዛለህ፤ ነገር ግን ቀንበሩን ከአንገትህ ልትጥል ብትወድድ ከእርሱ ጋር ተስማማ።”
አባቱም ገሠጸው፤ እንዲህም አለው፥ “ይህ ያለምኸው ሕልም ምንድን ነው? በውኑ እኔና እናትህ፥ ወንድሞችህም መጥተን በምድር ላይ እንሰግድልህ ይሆን?”
እነሆ፥ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበርና፥ እነሆ፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶዎች በዙርያ ከብበው እነሆ፥ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”
ሰሎሞንም ከወንዙ ጀምሮ እስከ ግብፅ ምድር ዳርቻ እስከ ፍልስጥኤማውያን ሀገር ድረስ በመንግሥታት ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር፤ ግብርም ያመጡለት ነበር፤ በዕድሜውም ሙሉ ለሰሎሞን ይገዙ ነበር።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ግብፅና የኢትዮጵያ ንግዶች ደከሙ፤ ቁመተ ረዥሞች የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፤ ለአንተም ይገዙልሃል፤ እጆቻቸውን ታስረው በኋላህ ይከተሉሃል፤ በፊትህም ያልፋሉ፤ ለአንተም እየሰገዱ፦ በእውነት እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም ብለው ይለምኑሃል።
ነገሥታትም አሳዳጊዎች አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፤ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።”
ታዳጊህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሕይወቱን የሚያስጨንቃትን፥ በአሕዛብ የተጠላውን የአለቆችን ባርያ ቀድሱት፤ ነገሥታት ያዩታል፤ አለቆችም ስለ እግዚአብሔር ብለው ተነሥተው ይሰግዱለታል፤ የእስራኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መርጨሃለሁና።”
የአስጨናቂዎችሽም ልጆች እየተንቀጠቀጡ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእስራኤል ቅዱስ የእግዚአብሔር ከተማ፥ ጽዮን ተብለሽም ትጠሪያለሽ።
ለአለቆች ሰላምን ለእርሱም ሕይወትን አመጣለሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆናል፤ በዳዊት ዙፋን መንግሥቱ ትጸናለች፤ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዐት ይህን ያደርጋል።
አርፎአል፥ እንደ አንበሳና እንደ አንበሳ ደቦል ተጋድሞአል፤ ማን ያስነሣዋል? የሚመርቁህ ሁሉ የተመረቁ ይሁኑ፤ የሚረግሙህም ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ።”