Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 45:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ግብ​ፅና የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንግ​ዶች ደከሙ፤ ቁመተ ረዥ​ሞች የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም ይገ​ዙ​ል​ሃል፤ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ታስ​ረው በኋ​ላህ ይከ​ተ​ሉ​ሃል፤ በፊ​ት​ህም ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም እየ​ሰ​ገዱ፦ በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤ ከእ​ር​ሱም ሌላ አም​ላክ የለም ብለው ይለ​ም​ኑ​ሃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የግብጽ ሀብትና የኢትዮጵያ ንግድ፣ ቁመተ ረዣዥሞቹ የሳባ ሰዎች፣ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ የአንተ ይሆናሉ፤ ከኋላ ይከተሉሃል፤ በሰንሰለትም ታስረው ወደ አንተ በመምጣት፣ በፊትህ እየሰገዱ፣ ‘በእውነት እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ነው፤ ከርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም’ ብለው ይለምኑሃል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ጌታ እንዲህ ይላል፦ የግብጽ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፤ ለአንተም ይሆናሉ እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል፤ በፊትህም ያልፋሉ፥ ለአንተም እየሰገዱ፦ በእውነት እግዚአብሔር በአንተ አለ፥ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም ብለው ይለምኑሃል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የግብጽ ሀብትና የኢትዮጵያ ሸቀጥ ለእናንተ ተላልፎ ይሰጣል፤ ቁመታቸው ረጃጅም የሆነ የሳባ ሰዎችም በሰንሰለት ታስረው በመምጣት ይከተሉአችኋል፤ እጅ ነሥተውም፦ ‘እግዚአብሔር የሚገኘው በእናንተ ዘንድ ብቻ ነው፤ በሌላ አይደለም፤ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም’ ይላሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የግብፅ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፥ ለአንተም ይሆናሉ እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል፥ በፊትህም ያልፋሉ፥ ለአንተም እየሰገዱ፦ በእውነት እግዚአብሔር በአንተ አለ፥ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም ብለው ይለምኑሃል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 45:14
41 Referencias Cruzadas  

አሕ​ዛብ ይገ​ዙ​ልህ፤ አለ​ቆ​ችም ይስ​ገ​ዱ​ልህ፤ ለወ​ን​ድ​ምህ ጌታ ሁን፤ የአ​ባ​ት​ህም ልጆች ይስ​ገ​ዱ​ልህ፤ የሚ​ረ​ግ​ምህ እርሱ ርጉም ይሁን፤ የሚ​ባ​ር​ክ​ህም ቡሩክ ይሁን።”


ደግ​ሞም በጌት ላይ ጦር​ነት ሆነ፤ በዚ​ያም በእ​ጁና በእ​ግሩ ስድ​ስት ስድ​ስ​ት​ሁ​ላ​ሁሉ ሃያ አራት ጣቶች የነ​በ​ሩት አንድ ረዥም ሰው ነበረ፤ እርሱ ደግሞ ከራ​ፋ​ይም የተ​ወ​ለደ ነበረ።


ማራ​ኪ​ዎ​ችም መጥ​ተው ወሰ​ዱ​አ​ቸው፥ ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህ​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደሉ፥ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ” አለው።


ታር​ፋ​ለህ፥ የሚ​ዋ​ጋ​ህም የለም፤ ብዙ ሰዎ​ችም ይመ​ጣሉ፤ ልመ​ናም ያቀ​ር​ቡ​ል​ሃል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በጕ​ሮ​ሮ​አ​ቸው ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤ ሁለት አፍ ያለ​ውም ሰይፍ በእጁ ነው፥


ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ግር ብረት፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሰ​ን​ሰ​ለት ያስ​ራ​ቸው ዘንድ፤


እነ​ዚህ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ሁሉ፦ አንተ ውጣ፤ የሚ​ከ​ተ​ሉ​ህም ሕዝብ ሁሉ ከዚ​ያች ምድር ይውጡ እያሉ ወደ እኔ ይወ​ር​ዳሉ፤ ለእ​ኔም ይሰ​ግ​ዳሉ፤ ከዚ​ያም በኋላ እወ​ጣ​ለሁ።” ሙሴም በጽኑ ቍጣ ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ወጣ።


እነሆ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክቡ​ራ​ንን በኀ​ይል ያው​ካ​ቸ​ዋል፤ ታላ​ላ​ቆ​ች​ንም በሐ​ሣር ይቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ከፍ ያሉ​ትም ይዋ​ረ​ዳሉ።


በኢ​ት​ዮ​ጵያ ወን​ዞች ማዶ ላለች፥ ክንፍ ያላ​ቸው መር​ከ​ቦች ላሉ​ባት ምድር ወዮ​ላት!


በዚያ ዘመን ለሠ​ራ​ዊት ጌታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከተ​ዋ​ረ​ደና ከደ​ከመ ሕዝብ፥ ከዛሬ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ታላቅ ከሆነ ወገን፥ ተስፋ ከሚ​ያ​ደ​ር​ግና ከሚ​ረ​ገጥ፥ በሀ​ገሩ ወንዝ ዳር ከሚ​ኖር ሕዝብ ዘንድ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም በተ​ጠ​ራ​በት በደ​ብረ ጽዮን እጅ መንሻ ይቀ​ር​ባል።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ የታ​ወቀ ይሆ​ናል፤ በዚ​ያም ጊዜ ግብ​ፃ​ው​ያን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያው​ቃሉ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ትም ያቀ​ር​ቡ​ለ​ታል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስእ​ለት ይሳ​ላሉ፤ መባ​ኡ​ንም ያገ​ባሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፅን በታ​ላቅ መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ታ​ታል፤ ይፈ​ው​ሳ​ታ​ልም፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ለ​ሳሉ፤ እር​ሱም ይሰ​ማ​ቸ​ዋል፤ ይፈ​ው​ሳ​ቸ​ው​ማል።


ንግ​ድ​ዋና ዋጋዋ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል፤ ንግ​ድ​ዋም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለሚ​ኖሩ ለመ​ብ​ላ​ትና ለመ​ጠ​ጣት፥ ለመ​ጥ​ገ​ብም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ይሆ​ናል እንጂ ለእ​ነ​ርሱ አይ​ሰ​በ​ሰ​ብም።


እኔ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒ​ትህ ነኝ፤ ግብ​ፅ​ንና ኢት​ዮ​ጵ​ያን ለአ​ንተ ቤዛ አድ​ርጌ፥ ሴዎ​ን​ንም ለአ​ንተ ፋንታ ሰጥ​ቻ​ለሁ።


ራሳ​ች​ሁን አት​ደ​ብቁ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምን? አል​ነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁ​ምን? ከእኔ ሌላ አም​ላክ እንደ ሌለ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ።”


ክብ​ርና ጽድቅ ወደ እርሱ ይመ​ጣሉ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ርቁ ሁሉ ያፍ​ራሉ።


ነገ​ሥ​ታ​ትም አሳ​ዳ​ጊ​ዎች አባ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ እቴ​ጌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ሞግ​ዚ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ ግን​ባ​ራ​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር ዝቅ አድ​ር​ገው ይሰ​ግ​ዱ​ል​ሻል፤ የእ​ግ​ር​ሽ​ንም ትቢያ ይል​ሳሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ፤ እኔ​ንም በመ​ተ​ማ​መን የሚ​ጠ​ባ​በቁ አያ​ፍ​ሩም።”


እንደ ገና​ም​በ​ቀ​ኝና በግራ ተስ​ፋፊ፤ ዘርሽ አሕ​ዛ​ብን ይወ​ር​ሳ​ሉና፥ የፈ​ረ​ሱ​ት​ንም ከተ​ሞች መኖ​ሪያ ታደ​ር​ጊ​ያ​ለ​ሽና።


እነሆ፥ የማ​ያ​ው​ቁህ ሕዝብ ይጠ​ሩ​ሃል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ አክ​ብ​ሮ​ሃ​ልና ስለ አም​ላ​ክህ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የማ​ያ​ው​ቁህ ሕዝብ በአ​ንተ ይማ​ጠ​ናሉ።


ነገ​ሥ​ታት በብ​ር​ሃ​ንሽ፥ አሕ​ዛ​ብም በፀ​ዳ​ልሽ ይሄ​ዳሉ።


ዘራ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በወ​ገ​ኖች መካ​ከል የታ​ወቁ ይሆ​ናሉ፤ ያያ​ቸው ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የባ​ረ​ካ​ቸው ዘር እንደ ሆኑ ያው​ቃል፤


ጌታ ሆይ! አንተ ኀይ​ሌና ረዳቴ፥ በመ​ከ​ራም ቀን መጠ​ጊ​ያዬ ነህ፤ ከም​ድር ዳርቻ አሕ​ዛብ ወደ አንተ መጥ​ተው፥ “በእ​ው​ነት አባ​ቶ​ቻ​ችን ውሸ​ት​ንና ከን​ቱን ነገር ለም​ንም የማ​ይ​ረ​ባ​ቸ​ውን ጣዖ​ትን ሠር​ተ​ዋል” ይላሉ።


የበ​ገ​ና​ውን አው​ታር ድምፅ ይቃ​ኛሉ፤ ከብዙ ሰዎ​ችም ጉባኤ ጋር ሰካ​ራ​ሞቹ ከም​ድረ በዳ መጡ፤ በእ​ጃ​ቸው አን​ባር፥ በራ​ሳ​ቸ​ውም የተ​ዋበ አክ​ሊል አደ​ረጉ።


እነሆ አሦር ጫፉ እንደ ተዋበ፥ ችፍ​ግ​ነቱ ጥላ እንደ ሰጠ፥ ቁመ​ቱም እንደ ረዘመ፥ ራሱም ወደ ደመ​ና​ዎች እንደ ደረሰ እንደ ሊባ​ኖስ ዝግባ ነበረ።


ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን በይ​ሁዳ ልጆች እጅ እሸ​ጣ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ለሩ​ቆቹ ሕዝብ በም​ርኮ ይሸ​ጡ​አ​ች​ኋል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


ስለ ሰለ​ሉ​አ​ትም ምድር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እያ​ወሩ፥ “እኛ ዞረን የሰ​ለ​ል​ናት ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትን ሰዎች የም​ት​በላ ምድር ናት፤ በእ​ር​ስ​ዋም ዘንድ ያየ​ና​ቸው ሰዎች ሁሉ ረጃ​ጅም ሰዎች ናቸው፤


በል​ባ​ቸው የደ​በ​ቁ​ትም ይገ​ለ​ጣል፤ ከዚህ በኋላ ያ የማ​ያ​ም​ነው ተመ​ልሶ ይጸ​ጸ​ታል፤ በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ግ​ዳል፥ በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ዳ​ለም ይና​ገ​ራል።


እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሣውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንደተመለሳችሁ ይናገራሉ።


እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos