በዚያም ብዙ ቀን ተቀመጠ። የፍልስጥኤም ንጉሥ አቤሜሌክም በመስኮት ሆኖ በተመለከተ ጊዜ ይስሐቅን ከሚስቱ ከርብቃ ጋር ሲጫወት አየው።
መክብብ 9:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሕይወትህ፥ አንተም ከፀሓይ በታች በምትደክምበት ድካም ይህ ዕድል ፈንታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀሓይ በታች በሰጠህ፥ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ፥ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ከፀሓይ በታች በሰጠህ በዚህ ትርጕም የለሽ የሕይወት ዘመን ሁሉ፣ ከንቱ በሆኑትም ቀኖችህ ሁሉ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋራ ደስ ይበልህ፤ በሕይወትህና ከፀሓይ በታች በምትደክምበት ነገር ሁሉ ይህ ዕድል ፈንታህ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕይወትህ፥ አንተም ከፀሐይ በታች በምትደክምበት ድካም ይህ እድል ፈንታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀሐይ በታች በሰጠህ፥ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ፥ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዓለም እግዚአብሔር በሰጠህ ከንቱ በሆነ ኑሮህ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ፤ ስለ መከራህና ስለ ድካምህ ሁሉ ዋጋ ሆኖ የተሰጠህ ዕድል ፈንታ ይኸው ብቻ ስለ ሆነ ከንቱ ዘመንህን፥ እያንዳንዱን ቀን ተደሰትበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሕይወትህ፥ አንተም ከፀሐይ በታች በምትደክምበት ድካም ይህ እድል ፈንታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀሐይ በታች በሰጠህ፥ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ፥ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ። |
በዚያም ብዙ ቀን ተቀመጠ። የፍልስጥኤም ንጉሥ አቤሜሌክም በመስኮት ሆኖ በተመለከተ ጊዜ ይስሐቅን ከሚስቱ ከርብቃ ጋር ሲጫወት አየው።
አቤቱ አምላኬ፥ ብዙ ተአምራትህን አደረግህ፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፤ አወራሁ፥ ተናገርሁ፥ ከቍጥርም በዛ።
ደግ ሚስትን ያገኘ ሞገስን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ደስታን ተቀበለ። ደግ ሴትን የፈታ ደስታን አጣ፥ አመንዝራዪቱንም የሚያኖር አላዋቂና ኀጢአተኛ ነው።
ዐይኖቼ ከፈለጉት ሁሉ አላጣሁም፥ ልቤንም ከደስታ ሁሉ አልከለከልሁትም፤ ልቤ በድካሜ ሁሉ ደስ ይለው ነበርና፤ ከድካሜም ሁሉ ይህ ዕድል ፋንታዬ ሆነ።
ለሰው ከመብላትና ከመጠጣት በድካሙም ለሰውነቱ መልካም ነገር ከሚያሳያት በቀር በጎ ነገር የለም፤ ይህ ደግሞ ከእግዚአብሔር እጅ እንደ ተሰጠ አየሁ።
ያም ዕድል ፋንታው ነውና ሰው በሥራው ደስ ከሚለው በቀር ሌላ መልካም ነገር እንደሌለው አየሁ፤ ከእርሱ በኋላስ የሚሆነውን ያይ ዘንድ የሚያመጣው ማን ነው?
እነሆ፥ እኔ ያየሁት መልካምና የተዋበ ነገር፦ ሰው እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከፀሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው፤ ይህ ዕድል ፈንታው ነውና።
ሰው በከንቱ ወራቱ ቍጥርና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማን ነው? ወይስ ለሰው ከፀሓይ በታች ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ማን ይነግረዋል?
እግዚአብሔር የሕይወትን መንፈስ አንድ አድርጎ ጠብቆልን የለምን? እርሱም የሚፈልገው ምንድር ነው? ዘር አይደለምን? ስለዚህ መንፈሳችሁን ጠብቁ፥ ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል።