Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 19:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አባቶች ለልጆቻቸው ቤትንና ሀብትን ያወርሳሉ፤ ሚስት ግን በእግዚአብሔር ከባልዋ ጋር አንድ ትሆናለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ቤትና ሀብት ከወላጆች ይወረሳሉ፤ አስተዋይ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ቤትና ባለጠግነት ከአባቶች ዘንድ ይወረሳሉ፥ አስተዋይ ሚስት ግን ከጌታ ዘንድ ናት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አንድ ሰው ቤትና ሀብት ከወላጆቹ ሊወርስ ይችላል፤ አስተዋይ ሚስትን የሚሰጥ ግን እግዚአብሔር ብቻ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 19:14
12 Referencias Cruzadas  

ደግ ሚስትን ያገኘ ሞገስን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ደስታን ተቀበለ። ደግ ሴትን የፈታ ደስታን አጣ፥ አመንዝራዪቱንም የሚያኖር አላዋቂና ኀጢአተኛ ነው።


ደግ ሰው ለልጅ ልጅ ያወርሳል፥ የኀጢአተኞች ብልጽግና ግን ለጻድቃን ይደልባል።


በመንገድህ ሁሉ ጥበብን ዕወቃት፥ እርስዋም መንገድህን ታቃናልሃለች።


በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፤ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


እነሆ ወደ እና​ንተ ልመጣ ስዘ​ጋጅ ይህ ሦስ​ተ​ኛዬ ነው፤ ነገር ግን አል​ተ​ፋ​ጠ​ን​ሁም ገን​ዘ​ባ​ች​ሁን ያይ​ደለ፥ እና​ን​ተን እሻ​ለ​ሁና፤ ልጆች ለወ​ላ​ጆ​ቻ​ቸው ያይ​ደለ ወላ​ጆች ለል​ጆ​ቻ​ቸው ሊያ​ከ​ማቹ ይገ​ባ​ልና፤


ለል​ጆቹ ከብ​ቱን በሚ​ያ​ወ​ር​ስ​በት ቀን ከተ​ጠ​ላ​ችው ሚስት በተ​ወ​ለ​ደው በበ​ኵሩ ፊት ከተ​ወ​ደ​ደ​ችው ሚስት የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ልጅ በኵር ያደ​ር​ገው ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያ​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል እንደ ክፍ​ላ​ቸው በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው ርስት አድ​ርጎ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው፤ ምድ​ሪ​ቱም ከጦ​ር​ነት ዐረ​ፈች።


ከአ​ባቴ ቤት፥ ከተ​ወ​ለ​ድ​ሁ​ባት ምድር ያወ​ጣኝ፦ ‘ይህ​ች​ንም ምድር ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ’ ብሎ የነ​ገ​ረ​ኝና የማ​ለ​ልኝ የሰ​ማ​ይና የም​ድር አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እርሱ መል​አ​ኩን በፊ​ትህ ይሰ​ድ​ዳል፤ ከዚ​ያም ለልጄ ሚስ​ትን ትወ​ስ​ዳ​ለህ።


እር​ስ​ዋም ፦ ‘አንተ ጠጣ፤ ደግ​ሞም ለግ​መ​ሎ​ችህ እቀ​ዳ​ለሁ’ የም​ት​ለኝ ድን​ግል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጌ​ታዬ ልጅ ለባ​ሪ​ያዉ ለይ​ስ​ሐቅ ያዘ​ጋ​ጃት ሚስት እር​ስዋ ትሁን። በዚ​ህም ለጌ​ታዬ ምሕ​ረ​ትን እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ አው​ቃ​ለሁ።”


የሰ​ው​ዬ​ውም ስም ናባል፥ የሚ​ስ​ቱም ስም አቤ​ግያ ነበረ፤ ሴቲ​ቱም ደግና ብልህ፥ መል​ክ​ዋም እጅግ የተ​ዋበ ነበረ፤ ሰው​ዬው ግን ጨካ​ኝና ንፉግ ነበረ፤ ግብ​ሩም ክፉ ነበረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios