እግዚአብሔርም እነዚያን ከተሞችና ሎጥ የሚኖርባቸውን አውራጃዎችዋን ሁሉ ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን ዐሰበው፤ ሎጥንም ከጥፋት መካከል አወጣው።
ዘዳግም 9:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በራስህ የማልህላቸውን አገልጋዮችህን አብርሃምንና ይስሐቅን፥ ያዕቆብንም አስብ፤ የዚህን ሕዝብ ልበ ደንዳናነት፥ ክፋቱንም፥ ኀጢአቱንም አትመልከት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሪያዎችህን አብርሃምን፣ ይሥሐቅንና ያዕቆብን ዐስብ፤ የዚህን ሕዝብ ልበ ደንዳናነት፣ ክፋትና ኀጢአት አትመልከት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባርያዎችህን አብርሃምን፥ ይስሐቅን፥ ያዕቆብንም አስብ፥ የዚህን ሕዝብ ደንዳንነት ክፋቱንም ኃጢአቱንም አትመልከት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገልጋዮችህን አብርሃምን፥ ይስሐቅንና ያዕቆብን አስብ፤ የዚህን ሕዝብ እልኸኛነት፥ ክፋትና ኃጢአት ሁሉ አትቊጠርበት፤’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎችህን አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም አስብ፤ የዚህን ሕዝብ ደንዳንነት ክፋቱንም ኃጢአቱንም አትመልከት፤ |
እግዚአብሔርም እነዚያን ከተሞችና ሎጥ የሚኖርባቸውን አውራጃዎችዋን ሁሉ ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን ዐሰበው፤ ሎጥንም ከጥፋት መካከል አወጣው።
እግዚአብሔርም ለእናንተ ይሰጣት ዘንድ ለአባቶቻችሁ ወደማለላቸው፥ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር፥ ወደ ከናኔዎናውያን፥ ወደ ኬጢዎናውያንም፥ ወደ አሞሬዎናውያንም፥ ወደ ኤዌዎናውያን፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያንም፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያንም፥ ወደ ፌርዜዎናውያንም ምድር በአገባችሁ ጊዜ ይህችን ሥርዐት በዚህ ወር አድርጉ።
ሂድ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ሰብስብ፤ እንዲህም በላቸው፦ የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተገለጠልኝ፦ መጐብኘትን ጐበኘኋችሁ፤ በግብፅም የሚደረግባችሁን አየሁ፤
ደግሞም፥ “እኔ የአባቶችህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ያይ ዘንድ ፈርቶአልና ፊቱን መለሰ።
ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፤ ይህችንም የተናገርኋትን ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፤ ለዘለዓለምም ይወርሱአታል ብለህ በራስህ የማልህላቸው ባሪያዎችህን አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም ዐስብ።”
ስለ ስምህ ብለህ ተመለስልን፤ የክብርህንም ዙፋን አታጥፋ፤ ከእኛ ጋርም ያደረግኸውን ቃል ኪዳንህን አስብ እንጂ አታፍርስ።
በዚያ ወራት በዚያም ዘመን፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እነዚህን በምድር የተረፉትን ይቅር እላቸዋለሁና የእስራኤል በደል ይፈለጋል፤ አይኖርምም፤ የይሁዳም ኀጢአት ይፈለጋል፥ ምንም አይገኝም።
ያን ጊዜ እኔ ከያዕቆብ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ደግሞም ከይስሐቅ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን፥ ከአብርሃምም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ምድሪቱንም አስባለሁ።
እኔ አምላካቸው እሆን ዘንድ አሕዛብ እያዩ ከግብፅ ምድር ከግዞት ቤት እንዳወጣኋቸው የቀድሞ ቃል ኪዳናቸውን ስለ እነርሱ አስባለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
በእግዚአብሔርም ፊት እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፦ የአማልክት ንጉሥ እግዚአብሔር ሆይ፥ በታላቅ ኀይልህ የተቤዠሃቸውን፥ በጠነከረችውም እጅህና በተዘረጋች ክንድህ ከግብፅ ያወጣሃቸውን ሕዝብህንና ርስትህን አታጥፋ።
ከእርስዋ እኛን ያወጣህባት ምድር ሰዎች፦ እግዚአብሔር ተስፋ ወደ ሰጣቸው ምድር ያገባቸው ዘንድ አልቻለምና፥ ጠልቶአቸውማልና ስለዚህ በምድረ በዳ ሊገድላቸው አወጣቸው እንዳይሉ።
በዚህ ክፉ ሰው በናባል ላይ ጌታዬ ልቡን እንዳይጥል እለምናለሁ፤ እንደ ስሙ እንዲሁ እርሱ ነው፤ ስሙ ናባል ነው፤ ስንፍናም አድሮበታል፤ እኔ ባሪያህ ግን አንተ የላክሃቸውን ብላቴኖችህን አላየሁም።