La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 17:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት በዚ​ያም ዘመን ወደ አሉ ፈራ​ጆች መጥ​ተህ ትጠ​ይ​ቃ​ለህ፤ እነ​ር​ሱም የፍ​ር​ዱን ነገር ይነ​ግ​ሩ​ሃል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ካህናት ወደሆኑት ሌዋውያንና በዚያ ጊዜ ዳኛ ወደ ሆነው ሰው ሄደህ ስለ ጕዳዩ ጠይቃቸው፤ እነርሱም ውሳኔውን ይነግሩሃል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ሌዋውያን ካህናት በዚያም ዘመን ወደ ተሾመው ፈራጅ መጥተህ ትጠይቃለህ፥ እነርሱም የፍርዱን ነገር ይነግሩሃል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከሌዋውያን ወገን ካህናት ለሆኑትና በዚያን ጊዜ ዳኛ ለሆነው ጉዳዩን አቅርብ፤ ጉዳዩንም እነርሱ ይወስኑ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ሌዋውያን ካህናት በዚያም ዘመን ወደ ተሾመው ፈራጅ መጥተህ ትጠይቃለህ፤ እነርሱም የፍርዱን ነገር ይነግሩሃል።

Ver Capítulo



ዘዳግም 17:9
15 Referencias Cruzadas  

ከይ​ሰ​ዓ​ራ​ው​ያን ከና​ን​ያና ልጆቹ ጻፎ​ችና ፈራ​ጆች ይሆኑ ዘንድ በው​ጭው ሥራ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ተሾ​መው ነበር።


ነገ​ርም ቢኖ​ራ​ቸው ወደ እኔ ይመ​ጣሉ፤ በዚ​ህና በዚያ ሰውም መካ​ከል እፈ​ር​ዳ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥር​ዐ​ትና ሕግ አስ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው።


ሌባው ባይ​ገኝ ባለ​ቤቱ ወደ ፈጣሪ ፊት ይቅ​ረብ፤ ባል​ን​ጀ​ራው አደራ በአ​ስ​ቀ​መ​ጠ​በት ገን​ዘ​ብም ላይ እን​ዳ​ል​ተ​ተ​ነ​ኰ​ለና ክፉ እን​ዳ​ላ​ሰበ ይማል።


እነ​ር​ሱም፥ “ሕግ ከካ​ህን፥ ምክ​ርም ከጠ​ቢብ፥ ቃልም ከነ​ቢይ አይ​ጠ​ፋ​ምና ኑ፤ በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ምክ​ርን እን​ም​ከር። ኑ፤ በም​ላስ እን​ም​ታው፤ ቃሉ​ንም ሁሉ አና​ዳ​ምጥ” አሉ።


ክር​ክ​ርም በሆነ ጊዜ ለመ​ፍ​ረድ ይቁሙ፤ እንደ ፍርዴ ይፍ​ረዱ፤ በበ​ዓ​ላቴ ሁሉ ሕጌ​ንና ሥር​ዐ​ቴን ይጠ​ብቁ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ይቀ​ድሱ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ካህናቱን ስለ ሕጉ ጠይቅ፣


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፥ በዚህም ከቆሙት ከእነዚህ ጋር መግባትን እሰጣለሁ።


ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ ባለፉት ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መለየትና ማልቀስ ይገባኛልን? ብለው ይናገሩ ዘንድ ልኮአቸው ነበር።


ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሰ​ጥህ በሀ​ገ​ርህ ደጅ ሁሉ በየ​ነ​ገ​ዶ​ችህ ፈራ​ጆ​ች​ንና መባ​ውን የሚ​ጽ​ፉ​ትን ሹሙ፤ ለሕ​ዝ​ቡም ቅን ፍር​ድን ይፍ​ረዱ።


ስሙ በዚያ ይጠራ ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​ጠው ስፍራ እንደ ነገ​ሩህ ቃል ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ያስ​ተ​ማ​ሩ​ህ​ንም ሕጉን ታደ​ርግ ዘንድ ጠብቅ።


የሌዊ ልጆች ካህ​ና​ትም ይቀ​ር​ባሉ፤ በፊቱ እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግሉ፥ በስ​ሙም እን​ዲ​ባ​ርኩ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መር​ጦ​አ​ቸ​ዋ​ልና፤ በእ​ነ​ር​ሱም ቃል ክር​ክር ሁሉ ጕዳ​ትም ሁሉ ይቆ​ማ​ልና፤


“በሰ​ዎች መካ​ከል ጠብ ቢሆን፥ ወደ ፍር​ድም ቢመጡ፥ ቢፋ​ረ​ዱም ለጻ​ድቁ ይፈ​ረ​ድ​ለት፤ በበ​ደ​ለ​ኛ​ውም ይፈ​ረ​ድ​በት።


ፍር​ድ​ህን ለያ​ዕ​ቆብ፥ ሕግ​ህ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ያስ​ተ​ም​ራሉ፤ በማ​ዕ​ጠ​ን​ትህ ዕጣ​ንን፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ህም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሁል​ጊዜ ያቀ​ር​ባሉ።