1 ሳሙኤል 21:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ተነሣ በዚያም ቀን ከሳኦል ፊት ሸሸ፤ ወደ ጌትም ንጉሥ ወደ አንኩስ መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያች ዕለት ዳዊት ከሳኦል ሸሽቶ ወደ ጋት ንጉሥ ወደ አንኩስ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያች ዕለት ዳዊት ከሳኦል ሸሽቶ ወደ ጋት ንጉሥ ወደ አኪሽ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ከሳኦል በመሸሽ አኪሽ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ጋት ንጉሥ ሄደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ተነሣ በዚያም ቀን ሳኦልን ፈርቶ ሸሸ፥ ወደ ጌትም ንጉሥ ወደ አንኩስ ሄደ። |
ይቅር በለኝ፥ አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ ነፍሴ አንተን ታምናለችና፤ ኀጢአት እስክታልፍ ድረስ በክንፎችህ ጥላ እታመናለሁ።
ንጉሡም ኢዮአቄም፥ ሠራዊቱ ሁሉ፥ አለቆቹም ሁሉ ቃሉን በሰሙ ጊዜ ንጉሡ ሊገድለው ፈለገ፤ ኡርያም ይህን በሰማ ጊዜ ፈርቶ ሸሸ፤ ወደ ግብፅም ገባ።
ዳዊትም ሮጦ በፍልስጥኤማዊው ላይ ቆመ፤ ሰይፉንም ይዞ ከሰገባው መዘዘው፤ ገደለውም፤ ራሱንም ቈረጠው። ፍልስጥኤማውያንም ዋናቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ሸሹ።