1 ነገሥት 13:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም ነገር ከገጸ ምድር ለመፍረስና ለመጥፋት በኢዮርብዓም ቤት ላይ ኀጢአት ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ኀጢአት የኢዮርብዓም ቤት እንዲወድቅና ከምድር ገጽም እንዲደመሰስ ምክንያት ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ኃጢአቱ ለሥረወ መንግሥቱ መጥፋትና በሙሉ ለመደምሰሱ ምክንያት ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ኃጢአቱ ለሥረወ መንግሥቱ መጥፋትና በሙሉ ለመደምሰሱ ምክንያት ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስኪፈርስም፥ ከምድርም እስኪጠፋ ድረስ ይህ ነገር ለኢዮርብዓም ቤት ኀጢአት ሆነ። |
ስለዚህ እነሆ፥ በኢዮርብዓም ቤት ላይ መከራን አመጣለሁ፤ ኢዮርብዓምንም አጠፋዋለሁ፤ አጥር ተጠግቶ እስከሚሸን ወንድ ድረስ አላስቀርለትም፤ በእስራኤልም ላይ ይነግሥ ዘንድ አልተወውም፤ ሰው ገለባ እስኪያልቅ ድረስ እንደሚያነድድ በኢዮርብዓም ቤት ላይ እሳትን አነዳለሁ።
እግዚአብሔር እንደ ተናገረ ከኢዮርብዓም ወገን በከተማዪቱ ውስጥ የሞተውን ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳውም የሞተውን የሰማይ ወፎች ይበሉታል።
ሂጂ ለኢዮርብዓም እንዲህ በዪው፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከሕዝብ መካከል ለይቼ ከፍ አድርጌህ ነበር፤ በሕዝቤ በእስራኤል ላይም ንጉሥ አድርጌህ ነበር።
በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በሁለተኛው ዓመት የኢዮርብዓም ልጅ ናባጥ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ በእስራኤልም ላይ ሁለት ዓመት ነገሠ።
አንድ ነቢይም ወደ እስራኤል ንጉሥ መጥቶ፥ “የሶርያ ንጉሥ ወልደ አዴር በሚመጣው ዓመት ይመጣብሃልና፥ በርታ፤ የምታደርገውንም ዕወቅ” አለው።
ነገር ግን እስራኤልን ካሳተው ከናባጥ ልጅ ከኢዮርብዓም ኀጢአት ኢዩ አልራቀም፥ በቤቴልና በዳን የነበሩትን የወርቅ እንቦሶችንም፥ አላስወገደም።
ኢዩ ግን በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ሕግ በፍጹም ልቡ ይሄድ ዘንድ አልተጠነቀቀም፤ እስራኤልንም ካሳተው ከኢዮርብዓም ኀጢአት አልራቀም።
እስራኤልም ከዳዊት ቤት ተለዩ፤ የናባጥንም ልጅ ኢዮርብዓምን አነገሡ፤ ኢዮርብዓምም እግዚአብሔርን ከመከተል እስራኤልን መለሰ፤ ታላቅም ኀጢአት አሠራቸው።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ከገጸ ምድር አስወግድሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ዐመፅን ተናግረሃልና በዚህ ዓመት ትሞታለህ” አለው።
የእስራኤል ኀጢአት የሆኑት የአዎን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ እሾህና አሜከላም በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላሉ፤ ተራሮችንም፥ “ክደኑን፤ ኮረብቶችንም፦ ውደቁብን” ይሉአቸዋል።