ሮሜ 8:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ የዳንነው በዚሁ ተስፋ ነው። ነገር ግን ተስፋ የምናደርገው ነገር የሚታይ ከሆነ ተስፋ መሆኑ ይቀራል፤ የሚታየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ተስፋ ድነናል፤ ተስፋው የሚታይ ከሆነ ግን ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ተስፋ ድነናል፤ ነገር ግን ተስፋው የሚታይ ከሆነ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚታየውን ተስፋ ማድረግ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ እንዴት ተስፋ ያደርጋል? እንዴትስ ይጠብቃል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? |
አብርሃም ዘርህ እጅግ ይበዛል ተብሎ በተነገረው መሠረት የብዙ ሕዝብ አባት እንደሚሆን ያመነውና ተስፋ ያደረገው ምንም ተስፋ በማይጣልበት ነገር ነው።
ወደዚህ አሁን በእምነት ጸንተን ወደምንገኝበት ጸጋ የገባነው በእርሱ ስለ ሆነ በተስፋ የእግዚአብሔር ክብር ተካፋዮች በመሆናችን እንመካለን።
ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት ጸንታችሁ ስትኖሩ ብቻ ነው፤ ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና በዓለም ላይ ላሉት ሰዎች ሁሉ የተሰበከ ነው፤ እኔ ጳውሎስም አገልጋይ የሆንኩት ለዚሁ ወንጌል ነው።
እግዚአብሔርም ለቅዱሳኑ ሊገልጥላቸው የፈቀደው ያለውን የዚህን ምሥጢር የክብር ብልጽግና በእናንተ በአሕዛብ መካከል ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ነው። ይህም ምሥጢር በተስፋ የምንጠባበቀው ክብር የሚገኝበት ክርስቶስ በእናንተ መካከል መሆኑ ነው።
የእውነት ቃል የሆነው ወንጌል በመጀመሪያ ወደ እናንተ በደረሰ ጊዜ በእርሱ ያለውን ተስፋ ሰምታችኋል፤ ስለዚህ እምነታችሁና ፍቅራችሁ የተመሠረተው በሰማይ ተዘጋጅቶ በሚቈያችሁ በዚህ ተስፋ ላይ ነው።
እኛ ግን የብርሃን ሰዎች ስለ ሆንን ራስን በመግዛት በመጠን እንኑር፤ እምነትንና ፍቅርን እንደ ጥሩር እንልበስ፤ የመዳንን ተስፋ እንደ ራስ ቊር እንልበስ፤
እምነት ማለት በተስፋ የሚጠበቀውን ነገር “አዎን በእውነት ይሆናል” ብሎ መቀበል ነው፤ በዐይን የማይታየውንም ነገር እንደሚታይ አድርጎ መቊጠር ነው።
እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ በኢየሱስ አማካይነት እርሱን ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ትተማመናላችሁ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ምክንያት ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ በታላቅ ምሕረቱ በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤