Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 4:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እኛ የምንጠብቀው የማይታየውን ነገር እንጂ የሚታየውን አይደለም፤ የሚታየው ነገር ጊዜያዊ ነው፤ የማይታየው ግን ዘለዓለማዊ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ስለዚህ ዐይናችን የሚያተኵረው በሚታየው ነገር ላይ ሳይሆን በማይታየው ላይ ነው፤ የሚታየው ጊዜያዊ ነውና፤ የማይታየው ግን ዘላለማዊ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ስለዚህ የሚታየውን ሳይሆን የማይታየውን እንመልከት፥ ምክንያቱም የሚታየው ጊዜያዊ ነው፤ የማይታየው ግን ዘላለማዊ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የማ​ይ​ታ​የ​ውን እንጂ የሚ​ታ​የ​ውን ተስፋ አና​ደ​ር​ግም፤ የሚ​ታ​የው ኀላፊ ነውና፥ የማ​ይ​ታ​የው ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር ነው።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 4:18
12 Referencias Cruzadas  

እኛ የምንኖረውም ጌታን በማመን እንጂ እርሱን በማየት አይደለም።


እምነት ማለት በተስፋ የሚጠበቀውን ነገር “አዎን በእውነት ይሆናል” ብሎ መቀበል ነው፤ በዐይን የማይታየውንም ነገር እንደሚታይ አድርጎ መቊጠር ነው።


ይህም ክርስቶስ የሰጠን ተስፋ የዘለዓለም ሕይወት ነው።


እነዚህ ሁሉ በእምነት እንዳሉ ሞቱ፤ እግዚአብሔር ሊሰጣቸው ቃል የገባላቸውንም ነገር አላገኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይተው ልክ እንዳገኙት አድርገው በደስታ ተቀበሉት። በምድር ላይ እንግዶችና መጻተኞች መሆናቸውንም ተገነዘቡ።


ስለዚህ እነዚህ ወደ ዘለዓለም ቅጣት ሲሄዱ፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘለዓለም ሕይወት ይሄዳሉ።”


ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን፥ በጸጋውም የዘለዓለም መጽናናትን፥ መልካም ተስፋንም የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን


ነገር ግን ክርስቶስ በመምጣት ላይ ላሉት መልካም ነገሮች የካህናት አለቃ ሆኖ ተገልጦአል፤ እርሱ የገባባት ድንኳን ትልቅና ፍጹም ናት፤ ይህች ድንኳን በሰው እጅ ያልተሠራችና ከዚህ ፍጥረት ያልሆነች ናት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios