መዝሙር 18:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአፍንጫው የቊጣ ጢስ ወጣ፤ ከአፉም የሚባላ የእሳት ነበልባልና የሚያቃጥል ፍም ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፤ ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤ ከውስጡም ፍሙ ጋለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድርም ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም፥ የተራሮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ ተናጉም እግዚአብሔርም ተቈጥቶአልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ሥርዐት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዐይኖችንም ያበራል። |
ከአሸባሪ ድምፅ የሚሸሽ በተቈፈረ ጒድጓድ ውስጥ ይወድቃል፤ ከጒድጓድ ዘሎ ለማምለጥ የሚሞክርም በወጥመድ ይያዛል፤ ከሰማይ ብርቱ ዝናብ ይዘንባል፤ የምድር መሠረቶችም ይናወጣሉ።
የእሳትም ምንጭ ከዙፋኑ ፊት ይፈልቅ ነበር፤ በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ አገልጋዮች ነበሩት፤ እልፍ አእላፋትም በፊቱ ቆመው ነበር፤ ችሎት ተጀመረ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ።
“ሰዶምንና ገሞራን እንደ ደመሰስኩ ከእናንተም ብዙዎችን ደመሰስኩ፤ እናንተም የተረፋችሁት በእሳት ከተቀጣጠለ በኋላ ተነጥቆ እንደ ወጣ እንጨት ነው፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።
እስራኤላውያን ስለ ደረሰባቸው ችግር ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ማጒረምረም ጀመሩ፤ እግዚአብሔርም የማጒረምረም ጩኸታቸውን ሰምቶ እጅግ በመቈጣት የሚባላ እሳት ላከባቸው፤ ያም እሳት ከሰፈሩ አንዱን ክፍል አወደመ።
እግዚአብሔር ለእንደዚህ ያለው ሰው ይቅርታ አያደርግም፤ ይልቁንም የእግዚአብሔር ቊጣና ቅናት በእርሱ ላይ እንደ እሳት ይነዳል፤ እግዚአብሔርም እንደዚህ ያለውን ሰው ፈጽሞ እስኪደመስሰው ድረስ በዚህ መጽሐፍ የተጻፉት መቅሠፍቶች ሁሉ ይወርዱበታል።