ደግሞም እግዚአብሔር አብራምን “ይህችን አገር በውርስ ለአንተ እንድሰጥህ ዑር ከምትባለው ከከለዳውያን ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ” አለው።
ዘኍል 33:53 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእናንተ የሰጠኋት ስለ ሆነ፥ ምድሪቱን ወርሳችሁ በእርስዋ ኑሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድሪቱን ርስት አድርጌ ሰጥቻችኋለሁና ውረሷት፤ ኑሩባትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱንም ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁና ምድሪቱን ትወርሱአታላችሁ ትቀመጡባታላችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያች ምድር የሚኖሩትንም አጥፍታችሁ በውስጥዋ ኑሩ። ምድሪቱን ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱንም ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁና ምድሪቱን ትወርሱአታላችሁ ትቀመጡባታላችሁም። |
ደግሞም እግዚአብሔር አብራምን “ይህችን አገር በውርስ ለአንተ እንድሰጥህ ዑር ከምትባለው ከከለዳውያን ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ” አለው።
ውሳኔውም የተላለፈው በቅዱሳን መላእክት ነው፤ ይህም የሆነው ልዑል እግዚአብሔር በምድር መንግሥታት ላይ ሥልጣን ያለው መሆኑን ሁሉም እንዲያውቅ ነው፤ ሥልጣኑንም ለፈቀደለት ሰው ይሰጠዋል፤ የተናቁትንም በሥልጣን ላይ ያስቀምጣቸዋል።’
ከሕዝብ መካከል ተለይተህ ትሰደዳለህ፤ ኑሮህም ከዱር አራዊት ጋር ይሆናል፤ ሰባት ዓመት እስኪያልፍ እንደ በሬ ሣር ትበላለህ፤ በሰማይ ጠል ትረሰርሳለህ፤ ይህም ሁሉ የሚደርስብህ ልዑል እግዚአብሔር በመንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና መንግሥትንም ሁሉ ለወደደው ሰው እንደሚሰጥ እስከምትረዳ ድረስ ነው።
ከሕዝብ መካከል ተባረህ መኖሪያህ ከዱር አራዊት ጋር ይሆናል፤ ሰባት ዓመት እስኪያልፍ እንደ በሬ ሣር ትበላለህ፤ ይህም የሚሆነው ልዑል እግዚአብሔር በምድር መንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና መንግሥትንም ሁሉ ለወደደው ሰው እንደሚሰጥ እስክትገነዘብ ድረስ ነው።”
“በዚህም ጊዜ የሚከተለውን መመሪያ ሰጠኋቸው፤ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለውን ይህን ምድር ትወርሱ ዘንድ ሰጥቶአችኋል፤ እንግዲህ የጦር ሰዎቻችሁን አስታጥቃችሁ ሌሎቹ የእስራኤል ነገዶች ምድራቸውን እስኪወርሱ ድረስ እነርሱን ለመርዳት ግንባር ቀደም ሆነው እንዲዘምቱ አድርጉ።
ልዑል እግዚአብሔር ለሕዝቡ ርስታቸውን ባከፋፈለ ጊዜ፥ የሰውን ዘር በለያየ ጊዜ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ቊጥር ብዛት፥ ለሕዝቡ ድንበርን ሠራላቸው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ሊሰጣቸው በመሐላ ቃል የገባላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤላውያን ሰጠ። ምድሪቱንም ከወረሱ በኋላ በዚያ ተደላድለው ኖሩ፤
አምላካችሁ እግዚአብሔር እነርሱን በፊታችሁ እንዲሸሹ ያደርጋል፤ እነርሱን ነቃቅሎ ያጠፋል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁም ተስፋ መሠረት ምድራቸውን ትወርሳላችሁ።