ዘኍል 33:52 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም52 በምድሪቱ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ አስወጡአቸው፤ ከድንጋይና ከብረት የተሠሩትን ጣዖቶቻቸውንም ሰባበሩ፤ በኮረብታ ላይ ያሉ መስገጃዎቻቸውንም አፈራርሱ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም52 የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ ከፊታችሁ አሳድዳችሁ አስወጧቸው፤ የተቀረጹ ምስሎቻቸውንና ቀልጠው የተሠሩ ጣዖቶቻቸውን በሙሉ አጥፉ፤ እንዲሁም በኰረብታ ላይ የተሠሩትን መስገጃዎቻቸውን ሁሉ አፈራርሱ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)52 የአገሩን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ ታሳድዳላችሁ፥ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ በኮረብታ ላይ ያሉትን መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)52 በዚያችም ምድር የሚኖሩትን ሁሉ ከፊታችሁ አጥፉአቸው፤ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፤ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፤ በኮረብታ ላይ ያሉትን መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)52 የአገሩን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ ታሳድዳላችሁ፥ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ በኮረብታ ላይ ያሉትን መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ፤ Ver Capítulo |