Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዳንኤል 4:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ከሕዝብ መካከል ተባረህ መኖሪያህ ከዱር አራዊት ጋር ይሆናል፤ ሰባት ዓመት እስኪያልፍ እንደ በሬ ሣር ትበላለህ፤ ይህም የሚሆነው ልዑል እግዚአብሔር በምድር መንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና መንግሥትንም ሁሉ ለወደደው ሰው እንደሚሰጥ እስክትገነዘብ ድረስ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ከሕዝብ መካከል ትሰደዳለህ፤ ከዱር አራዊት ጋራም ትኖራለህ፤ እንደ ከብት ሣር ትበላለህ፤ ልዑሉ በሰዎች መንግሥት ሁሉ ላይ ሙሉ ሥልጣን እንዳለውና እነዚህንም መንግሥታት ለወደደው እንደሚሰጥ እስክታውቅ ድረስ ሰባት ዓመት ያልፋል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ልዑሉም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለሚወድደውም እንዲሰጠው እስክታውቅ ድረስ ከሰዎች ተለይተህ ትሰደዳለህ፥ መኖሪያህም ከምድር አራዊት ጋር ይሆናል፥ እንደ በሬም ሣር ትበላ ዘንድ ትገደዳለህ፥ ሰባት ዘመናትም ያልፉብሃል አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 4:32
22 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርም የምናሴን ጸሎት ሰማ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመልሶ እንደገና እንዲገዛ ፈቀደለት፤ በዚህም ምናሴ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ መሆኑን ተገነዘበ።


“አምላክ ሆይ! አንተ ሁሉን ነገር ማድረግ እንደምትችል ዐውቃለሁ፤ የአንተንም ዕቅድ ማሰናከል የሚችል የለም።


የፈለገውን ቢወስድ ማንም አይከለክለውም፤ ‘ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?’ ብሎ ሊጠይቀው የሚደፍርም የለም።


አምላካችን በሰማይ ነው፤ እርሱ የፈቀደውን ሁሉ ያደርጋል።


በሰማይና በምድር፥ በጥልቅ ባሕሮችም የወደደውን ሁሉ ያደርጋል።


ንጉሡም “እንግዲያውስ ነገውኑ ጸልይልኝ” አለ። ሙሴም እንዲህ አለ፤ “እንዳልከው አደርጋለሁ፤ አንተም እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ሌላ አምላክ እንደሌለ በዚያን ጊዜ ታውቃለህ።


ነገር ግን እምቢ ብትል፥ በዓለም ላይ እኔን የመሰለ ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቅ ዘንድ አንተን ራስህን፥ መኳንንትህንና ሕዝብህን በመቅሠፍቴ ኀይል አሁኑኑ እቀጣለሁ።


ሙሴም ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “ከከተማው እንደ ወጣሁ እጄን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነጐድጓዱም ይቆማል፤ በረዶም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም፤ በዚህ ዐይነት አንተም ምድር የእግዚአብሔር እንደ ሆነች ታውቃለህ።


እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! አንተ ብቻ አምላክ መሆንህን የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ያውቁ ዘንድ አሁን ከአሦራውያን እጅ በመታደግ አድነን።”


በእግዚአብሔር ፊት ሕዝቦች እንደ አንድ የውሃ ጠብታ ናቸው፤ በሚዛንም ላይ እንዳለ ዐቧራ ናቸው፤ ደሴቶችም በእርሱ ዘንድ እንደ ትቢያ የቀለሉ ናቸው።


በእግዚአብሔር ዘንድ ሕዝቦች ሁሉ እንዳሉ የሚቈጠሩ አይደሉም። እነርሱ በእርሱ ዘንድ እንደ ኢምንት የሚቈጠሩና ዋጋ የሌላቸው ናቸው።


በጨለማና በድብቅ ቦታ የተከማቸውን ሀብት እሰጥሃለሁ። በዚህም በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንኩ ታውቃለህ።


‘በታላቁ ኀይሌና ብርታቴ ዓለምንና የሰውን ዘር እንዲሁም በምድር ላይ የሚኖሩ እንስሶችን ሁሉ ፈጠርኩ፤ ምድርንም የሚገዛ ማን እንደሚሆን እወስናለሁ።


እርሱ ጊዜያትንና ወራትን ያፈራርቃል፤ ነገሥታትን ወደ ዙፋን ያወጣል፤ ከዙፋንም ያወርዳል፤ ጥበብን ለጠቢባን፥ ዕውቀትንም ለአስተዋዮች የሚሰጥ እርሱ ነው።


ንግግሩን ገና ሳይጨርስ እንዲህ የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ፤ “ንጉሥ ናቡከደነፆር ሆይ! የተላለፈብህን ውሳኔ ስማ! እነሆ፥ መንግሥትህ ከአንተ ተወስዳለች፤


ከሕዝብ መካከል ተባረረ፤ አእምሮውም ተለውጦ እንደ እንስሳ ሆነ፤ እንደ በሬም ሣር እየበላ ከሜዳ አህዮች ጋር ሆኖ ለመኖር ተገደደ፤ መጠለያ አጥቶ ሰውነቱ በሰማይ ጠል ረሰረሰ፤ ይህም የሆነው ልዑል እግዚአብሔር በመንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና መንግሥትን ሁሉ ለፈለገው መስጠት እንደሚችል እስከሚረዳበት ጊዜ ድረስ ነበር።


በዚህም ምክንያት በምድር ላይ የሚኖር ሕዝብ ሁሉ የእግዚአብሔር ኀይል ምን ያኽል ታላቅ እንደ ሆነ ይገነዘባል፤ እናንተም አምላካችሁ እግዚአብሔርን ለዘለዓለም ታከብራላችሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos