“ነገር ግን እነርሱ በአንተ ላይ ዐምፀው ለቃልህ አንታዘዝም አሉ፤ ሕግህንም ላለመስማት ፊታቸውን መለሱ፤ በማስጠንቀቅ ወደ አንተ እንዲመለሱ ያስተማሩአቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ በየጊዜውም በአንተ ላይ ክፉ የስድብ ቃል ተናገሩ፤
ማቴዎስ 23:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ኢየሩሳሌም፥ ኢየሩሳሌም ሆይ! አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ! ወደ አንቺ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግሪ! ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ ሥር እንደምትሰበስብ፥ እኔም የአንቺን ልጆች በአንድነት ልሰበስብ ስንት ጊዜ ፈቀድኩ! እናንተ ግን አልፈለጋችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ነቢያትን የምትገድዪ፣ ወደ አንቺ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግሪ፤ ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ፣ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፤ እናንተ ግን አልፈቀዳችሁም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድዪ ወደ አንቺ የተላኩትንም የምትወግሪ፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን ልሰበስብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ! እናንተ ግን አልፈለጋችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም። |
“ነገር ግን እነርሱ በአንተ ላይ ዐምፀው ለቃልህ አንታዘዝም አሉ፤ ሕግህንም ላለመስማት ፊታቸውን መለሱ፤ በማስጠንቀቅ ወደ አንተ እንዲመለሱ ያስተማሩአቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ በየጊዜውም በአንተ ላይ ክፉ የስድብ ቃል ተናገሩ፤
ለመሆኑ እኔ ለእርሱ ያላደረግኹለት ነገር አለን? ከዚህስ ሌላ ላደርግለት የሚገባ ምን አለ? ታዲያ፥ መልካም ፍሬ ያፈራል ብዬ ስጠብቀው ስለምን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ?
“እኔ በመጣሁ ጊዜ ማንም ሰው አለመኖሩ ለምንድን ነው? በጠራሁም ጊዜ ማንም ሰው መልስ ያልሰጠኝ ለምንድን ነው? እኔ ለመታደግ አልችልምን? ለማዳንስ ኀይል የለኝምን? በተግሣጼ ብቻ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ወደ ምድረ በዳነት እለውጣለሁ፤ ዓሣዎቻቸውም ውሃ ከማጣት የተነሣ ሞተው ይበሰብሳሉ።
አገልጋዮቼ የሆኑትን ነቢያትን ወደ እናንተ ደጋግሜ ልኬአለሁ፤ እነርሱም ከክፉ ሥራችሁ ተመልሳችሁ ቅን የሆነውን ነገር እንድትሠሩ ነግረዋችኋል፤ ለባዕዳን አማልክት እንዳትሰግዱና የእነርሱም አገልጋዮች እንዳትሆኑ አስጠንቅቀዋችኋል፤ ለእናንተና ለቀድሞ አባቶቻችሁ በሰጠኋችሁ ምድር መኖር ትችሉ ዘንድ ይህን ሁሉ አዘዝኳችሁ፤ እናንተ ግን እኔን ለማዳመጥም ሆነ ለምነግራችሁ ቃል ትኲረት ልትሰጡት አልፈለጋችሁም።
ከዚህ በኋላ ልዑሉን ይረሕምኤልን ከዐዝርኤል ልጅ ሠራያና ከዐብድኤል ልጅ ከሸሌምያ ጋር ሆኖ እኔንና ባሮክን እንዲይዝ አዘዘው፤ እኛ ግን እግዚአብሔር ሰወረን።
እናንተ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ይህ ሁሉ መከራ ማስጠንቀቂያ ይሁናችሁ፤ አለበለዚያ ከፊቴ አስወግዳችኋለሁ፤ ከተማችሁን ወደ ምድረ በዳ ለውጬ ማንም እንዳይኖርባት አደርጋለሁ።”
ነገር ግን ሕዝቤን እስራኤልን ይበልጥ ወደ እኔ እንዲቀርቡ በጠራኋቸው መጠን፥ እነርሱ ይበልጥ ከእኔ እየራቁ ሄዱ። በዓል ተብሎ ለሚጠራው ጣዖት መሥዋዕት ከማቅረብና ለምስሎቹም ዕጣን ከማጠን አልተቈጠቡም።
“ከእኔ ርቀው ስለ ሄዱ ወዮላቸው! በእኔም ላይ ስለ ዐመፁ ጥፋት ይምጣባቸው፤ እኔ ልታደጋቸው ፈልጌ ነበር፤ እነርሱ ግን በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ።
እንደ ቀድሞ አባቶቻችሁ አትሁኑ፤ እነርሱን የቀድሞ ነቢያት ‘ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ’ ብለው አስጠንቅቀዋቸው ነበር፤ አባቶቻችሁ ግን ቃሌን አላደመጡም፤ ትእዛዜንም አልጠበቁም።
በመንግሥተ ሰማይ የምታገኙት ዋጋ ትልቅ ስለ ሆነ ደስ ይበላችሁ፤ ሐሴትም አድርጉ። ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያት እንዲሁ ስደትና መከራ አድርሰውባቸዋል።”
አይሁድ ጌታ ኢየሱስንና ነቢያትን የገደሉ እኛንም አሳደው ከአገር ያስወጡ ናቸው፤ እነርሱ እግዚአብሔርን የሚያሳዝኑና ሰዎችን ሁሉ የሚጠሉ ናቸው፤
እግዚአብሔር ላደረግሽው በጎ ነገር ዋጋሽን ይክፈልሽ! የእርሱን ጥበቃ ተማምነሽ የመጣሽው የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ዋጋሽን የተትረፈረፈ ያድርገው!”