Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ነህምያ 9:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 “ነገር ግን እነርሱ በአንተ ላይ ዐምፀው ለቃልህ አንታዘዝም አሉ፤ ሕግህንም ላለመስማት ፊታቸውን መለሱ፤ በማስጠንቀቅ ወደ አንተ እንዲመለሱ ያስተማሩአቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ በየጊዜውም በአንተ ላይ ክፉ የስድብ ቃል ተናገሩ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 “ነገር ግን እንቢተኞች ሆኑ፤ ዐመፁብህም፤ ሕግህንም አሽቀንጥረው ጣሉ፤ ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩት ነቢያትህን ገደሉ፤ አስጸያፊ የስድብ ቃልም ተናገሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 “ነገር ግን እንቢተኞች ነበሩ፥ ዐመፁብህም፥ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፥ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፥ እጅግም አስቆጡህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 “ነገር ግን ተመ​ል​ሰው ዐመ​ፁ​ብህ፤ ሕግ​ህ​ንም ወደ ኋላ​ቸው ጣሉት፤ ወደ አን​ተም ይመ​ለሱ ዘንድ የመ​ሰ​ከ​ሩ​ባ​ቸ​ውን ነቢ​ያ​ት​ህን ገደሉ፤ እጅ​ግም አስ​ቈ​ጡህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ነገር ግን እንቢተኞች ነበሩ፥ ዐመፁብህም፥ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፥ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፥ እጅግም አስቈጡህ።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 9:26
35 Referencias Cruzadas  

ይልቁንም ከአንተ በፊት መሪዎች ከነበሩ ሰዎች የከፋ ኃጢአት ሠራህ፤ እኔንም ትተህ ጣዖቶችና ከብረት የተቀረጹ ምስሎችን ለማምለክ በመሥራትህ ቊጣዬን አነሣሥተሃል፤


በጥጃ አምሳል ለራሳቸው ጣዖትን ሠርተው፥ ‘ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣን አምላክ ይህ ነው!’ አሉ፤ በአንተ ላይም ከፍተኛ የስድብን ቃል እንኳ ተናገሩ፤


ከነቢያት መካከል አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን አለ? እነርሱ የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ እናንተም አሁን ይህን ጻድቁን አሳልፋችሁ በመስጠት ገደላችሁት።


ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ!” ሲል መለሰ።


ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ታስገድል በነበረችበትም ጊዜ አብድዩ አንድ መቶ የሚሆኑትን የእግዚአብሔርን ነቢያት ከሁለት ከፍሎ ኀምሳ፥ ኀምሳውን በዋሻዎች ከሸሸጋቸው በኋላ እህልና ውሃ በማቅረብ ይመግባቸው ነበር።


ገበሬዎቹ ግን አገልጋዮቹን ይዘው አንዱን ደበደቡት፤ አንዱን ገደሉት፤ ሌላውን ደግሞ በድንጋይ ወገሩት።


“ነገር ግን ልጆቻቸው በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ለሚፈጽመው ሁሉ ሕይወት የሚያስገኝለትን ሕጌን አፈረሱ፤ ሕጎቼንም አልጠበቁም፤ ሰንበትንም አረከሱ፤ በዚያም በበረሓ ሳሉ የቊጣዬን ኀይል በእነርሱ ላይ በማውረድ ሁሉንም ላጠፋቸው አስቤ ነበር።


ስሕተትህን መታረም ትጠላለህ፤ ቃሎቼንም ትንቃለህ።


አንተም ለብዙ ዓመቶች ታገሥካቸው፤ ያስተምሩአቸውም ዘንድ ነቢያትን በመንፈስህ አስነሣህላቸው፤ ነገር ግን እነርሱ አላዳመጡም፤ ስለዚህም ለጐረቤት ሕዝቦች ድል እንዲነሡአቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው።


እስራኤላውያን ግን በእግዚአብሔር መልእክተኞች ላይ ተሳለቁ፤ በነቢያቱም በማፌዝ፥ የእግዚአብሔርን ቃል አቃለሉ፤ ከዚህም የተነሣ፥ የእግዚአብሔር ቊጣ በሕዝቡ ላይ ወረደ፤ ከታላቅ ቊጣውም ለማምለጥ አልቻሉም።


“የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ይህን ሁሉ አሳፋሪ ነገር አደረገ፤ ይኸውም ቀድሞ ከነዓናውያን ይፈጽሙት ከነበረው ሁሉ የከፋ ነው፤ በሠራቸውም ጣዖቶች የይሁዳን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ፤


ደግሞስ ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ስታስገድል በነበረችበት ጊዜ አንድ መቶ የሚሆኑትን ነቢያት ከሁለት በመክፈል ኀምሳ ኀምሳውን በዋሻዎች ውስጥ ሸሽጌ እህልና ውሃ በማቅረብ ስመግባቸው መኖሬን አልሰማህምን?


እስራኤላውያን ባዓልና ዐስታሮት የተባሉትን ባዕዳን አማልክት እንዲሁም የሶርያን፥ የሲዶናን፥ የሞአብን፥ የዐሞንንና የፍልስጥኤምን አማልክት በማምለክ እንደገና እግዚአብሔርን በደሉ፤ እርሱንም ማምለክ ተዉ፤


እነርሱም ወደ ሕግህ እንዲመለሱ አስጠነቀቅኻቸው፤ በትዕቢታቸው ግን ትእዛዞችህን ናቁ፤ ቢፈጽሙአቸው ሕይወት በሚሰጡት ሕጎችህ ላይ ኃጢአት ሠሩ። በልበ ደንዳናነት ፊታቸውን አዞሩ፤ በእልኸኛነታቸውም እምቢተኞች ሆኑ።


ከቶ የምትታረሙ ስላልሆናችሁ፥ እኔ እናንተን መቅጣቴ ከንቱ ነው፤ እንደ ተቈጣ አንበሳ ሆናችሁ ነቢያቶቻችሁን በሰይፍ ገደላችሁ።


በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል በላቸው፦ ‘የቀድሞ አባቶቻችሁ ከእኔ ተለይተው የሐሰት አማልክትን በማምለክ አገለገሉ፤ እኔን ተዉኝ፤ ሕጌንም አልፈጸሙም።


ነገር ግን ወደዚህች ምድር መጥተው ከወረሱአት በኋላ ለቃልህ መታዘዝንና በአስተማርካቸው ሕግ ጸንተው መኖርን እምቢ አሉ፤ ያዘዝካቸውንም ነገር ሁሉ አልፈጸሙም፤ ከዚህም የተነሣ ይህን ሁሉ ጥፋት አመጣህባቸው።


“እናንተ ከስደት የተረፋችሁ የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ወደ እግዚአብሔር በላካችሁኝ ጊዜ እርሱ የሚያዘውን ሁሉ ንገረንና እንፈጽማለን ብላችሁ የማትፈጽሙትን ቃል በመግባታችሁ አደገኛ ስህተት ሠርታችኋል፤ አሁንም እግዚአብሔር ወደ ግብጽ አትሂዱ ብሎ ስለ ከለከለ እኔም ዛሬ ይህ ትእዛዝ እርግጠኛ መሆኑን በመግለጥ አስጠነቅቃችኋለሁ።


“አምላክ ሆይ! እኛ ኃጢአትና ዐመፅ ሠርተናል፤ አንተም ይቅር አላልከንም።


ከከብቶች፥ ከበጎችና ከፍየሎች መንጋ በሚገኝ ወተትና ዕርጎ፥ ከባሳን በሚገኙ ምርጥ ጠቦቶች፥ አውራ በጎች፥ ኰርማዎችና ፍየሎች ጮማ ሥጋ ከምርጥ ስንዴ ዳቦ ጋር መገባቸው። እናንተም ሕዝቦቹ ከቀይ ወይን ዘለላ ጭማቂ የወይን ጠጅ ጠጣችሁ።


“እስራኤላውያንም ወፈሩ፤ ዐመፁም። በጣም በልተው ወፈሩ፤ ሰቡ፤ የፈጠራቸውንም አምላክ ተዉ፤ መጠጊያ አዳኛቸውን አቃለሉ።


እግዚአብሔርም በአገልጋዮቹ በነቢያት አማካይነት እንዲህ ሲል ተናገረ፦


የምታስገኘውን ሰብልና ሌሎችን መልካም ነገሮች ሁሉ አግኝተው እንዲደሰቱ ለም ወደ ሆነች ምድር አገባኋቸው፤ እነርሱ ግን ምድሬን አበላሹ፤ የሰጠኋቸውን አገር አረከሱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios