ኤርምያስ 7:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ሕዝብ ለእኔ ለአምላኩ የማይታዘዝና ከቅጣቱም ሥነ ሥርዓትን መማር የማይፈልግ ሆኖአል፤ በዚህ ምክንያት እውነት ጨርሳ ጠፍታለች፤ ስለ እርስዋ በአንደበቱ የሚያነሣ እንኳ የለም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ይህ ሕዝብ አምላኩን እግዚአብሔርን ያልታዘዘ፣ ምክሩን ያልተቀበለ ወገን ነው፤ እውነት ጠፍቷል፤ ከአንደበታቸውም ሸሽቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም፦ “የአምላኩን የጌታን ድምፅ ያልሰማ፥ ተግሣጽንም ያልተቀበለ ሕዝብ ይህ ነው፤ እውነት ጠፍቶአል ከአፋቸውም ታጥቶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም፦ የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቃል ያልሰማ፥ ተግሣጽንም ያልተቀበለ ሕዝብ ይህ ነው፤ እውነት ጠፍቶአል፤ ከአፋቸውም ተቈርጦአል ትላቸዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም፦ የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቃል ያልሰማ፥ ተግሣጽንም ያልተቀበለ ሕዝብ ይህ ነው፥ እውነት ጠፍቶአል ከአፋቸውም ተቈርጦአል ትላቸዋለህ። |
እኔ ያዘዝኳቸውን ለመፈጸም እምቢ ይሉ እንደ ነበሩት እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ኃጢአት ይሠራሉ፤ ባዕዳን አማልክትን ያመልካሉ፤ እስራኤልና ይሁዳ በአንድነት ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል።
የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! “እስቲ በኢየሩሳሌም መንገዶች ሁሉ እየተዘዋወራችሁ እዩ! ትክክለኛ ፍርድ የሚሰጥና እውነትን የሚሻ አንድ ሰው እንኳ ማግኘት ትችሉ እንደ ሆነ፥ እስቲ በየአደባባዩ ፈልጉ! ይህ ቢሆን እኔ ለኢየሩሳሌም ምሕረት አደርግላታለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።
እናንተ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ይህ ሁሉ መከራ ማስጠንቀቂያ ይሁናችሁ፤ አለበለዚያ ከፊቴ አስወግዳችኋለሁ፤ ከተማችሁን ወደ ምድረ በዳ ለውጬ ማንም እንዳይኖርባት አደርጋለሁ።”
በዚህች ምድር በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ እግዚአብሔር የሚያቀርበው ወቀሳ አለው፤ ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እርሱ የሚልህን ሁሉ ስማ፦ “በምድሪቱ ላይ ታማኝነትና ፍቅር እግዚአብሔርንም ማወቅ ጠፍቶአል።
እኔም ይህን ሁሉ በማድረጌ ‘ሕዝቤ ያከብረኛል፤ ተግሣጼንም ይቀበላል፤ የደረሰበትንም ተግሣጽ ሁሉ አይረሳም’ ብዬ ነበር፤ ሕዝቤ ግን እየባሰበት ሄደ፤ በክፉ ሥራውም ረከሰ።”