ኤርምያስ 12:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ቤቴንና ርስቴን ትቼአለሁ፤ የምወዳቸውን ሕዝቤንም ለጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ቤቴን እተዋለሁ፤ ርስቴን እጥላለሁ፤ የምወድዳትን እርሷን፣ አሳልፌ በጠላቶቿ እጅ እሰጣታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ቤቴን ትቼአለሁ ርስቴንም ጥያለሁ፥ ነፍሴም የምትወድዳትን በጠላቶችዋ እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤቴን ትችአለሁ፤ ርስቴንም ጥያለሁ፤ ነፍሴ የምትወድዳትንም በጠላቶችዋ እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤቴን ትቼአለሁ ርስቴንም ጥያለሁ፥ ነፍሴም የምትወድዳትን በጠላቶችዋ እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ። |
አምላክ ሆይ! የያዕቆብ ዘሮች የሆኑ ሕዝብህን እርግፍ አድርገህ ትተሃል፤ ምድሪቱ በምሥራቅ አገር ሰዎች ጥንቈላና በፍልስጥኤማውያን ሟርት ተሞልታለች፤ ሕዝቡም ከአሕዛብ ጋር ተባብረዋል።
እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ እንዲህ እንድላቸው ነገረኝ፦ “እናንተ እኔ የምወዳችሁ ሕዝብ ናችሁ፤ ነገር ግን እንደእነዚህ ያሉ ክፉ ነገሮችን እያደረጋችሁ በዚህ በቤተ መቅደሴ ውስጥ ልትገኙ አይገባም፤ የምታቀርቡልኝም የእንስሶች መሥዋዕት ከጥፋት አይጠብቃችሁም፤ ስለዚህ በቤተ መቅደሴ ውስጥ መደሰታችሁን አቁሙ።
እግዚአብሔር ሆይ! ይሁዳን ፈጽመህ ልትጥላት ነውን? የጽዮንንስ ሕዝብ እንደ ጠላህ መቅረትህ ነውን? ለመፈወስ እስከማንችል ድረስ፥ ይህን ያኽል እንድንጐዳ ማድረግህስ ስለምንድን ነው? ሰላም እናገኛለን ብለን ተስፋ አደረግን፥ ነገር ግን ምንም መልካም ነገር አልገጠመንም፤ ፈውስ እናገኛለን ብለን ተስፋ አደረግን፤ ነገር ግን ሽብር እየበዛ ሄደ።
ቊጣዬ እንደ እሳት እንዲቀጣጠል ስላደረጋችሁ እርሱም ለዘለዓለም ስለሚነድ የሰጠኋችሁን ርስት ሁሉ እንድታጡና በማታውቁት አገር ጠላቶቻችሁን እንድታገለግሉ አደርጋለሁ።”
ትእዛዜን የማትፈጽሙ ከሆነ ግን ይህ ቤተ መቅደስ ፈራርሶ እንደሚወድቅ በራሴ በመማል አረጋግጥላችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፥ “ኤርምያስ ሆይ! ነቢይ ወይም ካህን ወይም ከሕዝቤ አንዱ፥ ‘የእግዚአብሔር ሸክም ምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቅህ፥ ‘የእግዚአብሔር ሸክም እናንተ ናችሁ፤ ስለ ሆነም ከፊቱ ያስወግዳችኋል’ ብለህ ንገራቸው።
ምድራቸው በእኔ በእስራኤል ቅዱስ ዘንድ በበደል የተሞላች ብትሆንም እንኳ እኔ የሠራዊት ጌታ አምላካቸው እስራኤልንና ይሁዳን አልረሳኋቸውም።
ስለዚህ በሴሎ ያደረግኹትን በዚህ በምትታመኑበት በቤተ መቅደሴ አደርጋለሁ፤ ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለእናንተ በሰጠሁት በዚህ ቦታ በሴሎ ያደረግኹትን ደግሜ አደርጋለሁ።
“የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ፥ ጠጒራችሁን ተላጭታችሁ በመጣል እዘኑ፤ ዛፎች በሌሉባቸው ኰረብቶች ራስ ላይ ሙሾ አውጡ፤ እኔ እግዚአብሔር ተቈጥቻለሁ፤ ሕዝቤንም ከፊቴ አሽቀንጥሬ ጥያለሁ።
‘ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው አለኝ፤ የክብራችሁ ትምክሕት፥ የዐይናችሁ ተስፋና የልባችሁ ደስታ የሆነውን ቤተ መቅደሴን እንዲያረክሱ እተዋቸዋለሁ፤ በኢየሩሳሌም የቀሩት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በጦርነት ይገደላሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ገና በጌልገላ ሳሉ ክፉ ሥራቸው ተገለጠ፤ እኔም በዚያ የእነርሱን ሥራ መጥላት ጀመርኩ፤ ስለ ሠሩትም ክፉ ሥራ ከሰጠኋቸው ምድር አስወጣቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ለእነርሱ ፍቅር አላሳያቸውም፤ መሪዎቻቸው ሁሉ ዐመፀኞች ሆነዋል።
አሕዛብን ሁሉ ሰብስቤ፥ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤ የእኔ የሆኑትን ሕዝቤን እስራኤልን በሕዝቦች መካከል ስለ በታተኑና ምድሪቱን ስለ ተካፈሉ በኢዮሣፍጥ ሸለቆ ወደ ፍርድ አቀርባቸዋለሁ።
ከእነርሱም ብዙዎች በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሌሎችም ተማርከው ወደየአገሩ ይወሰዳሉ። የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።”
ስለ ብንያምም ነገድ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር የሚወደው ያለ ስጋት ይረፍ፤ ኀያሉ አምላክ ቀኑን ይጠብቀዋል። በእግዚአብሔር ጥበቃም ሥር ይኖራል።”