ዘዳግም 2:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእርግጥ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሠራችሁት ሥራ ሁሉ ብዙ በረከት ሰጥቶአችኋል፤ በዚህ በሰፊው በረሓ በሄዳችሁበት ሁሉ ተንከባክቦአችኋል፤ በእነዚህ በአርባ ዓመቶች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ስለ ነበረ ምንም የጐደለባችሁ ነገር አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችሁ እግዚአብሔር በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ባርኳችኋል፤ በዚህ ጭልጥ ባለው ምድረ በዳ ባደረጋችሁት ጕዞ ጠብቋችኋል። በእነዚህ አርባ ዓመታት አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ነበርና አንዳችም ነገር አላጣችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ አምላክህ የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፥ በዚህ በታላቅ ምድረ በዳ መሄድህን አውቆአል፥ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ ጌታ አምላክህ ከአንተ ጋር ነበረ፥ አንዳችም አላጣህም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔር የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፤ ይህን ታላቅና የሚያስፈራ ምድረ በዳ እንዴት እንደ ዞርኸው ዕወቅ፤ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነበረ፤ ከተናገርኸው ሁሉ አንዳችም አላሳጣህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፤ በዚህ በታላቅ ምድረ በዳ መሄድህን አውቆአል፤ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነበረ፥ አንዳችም አላጣህም። |
እግዚአብሔር ጌታዬን እጅግ ባርኮታል፤ ባለጸጋም አድርጎታል፤ ብዙ የበግ፥ የፍየልና የከብት መንጋ፥ ብርና ወርቅ፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮች ግመሎችና አህዮች ሰጥቶታል።
“ሂድና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘በመጀመሪያ በምድረ በዳ ምንም በማያበቅልበት ትከተሉኝ ነበር፤ በዚያን ጊዜ ሙሽራይቱ ለሙሽራው የምታሳየውን ፍቅርና ታማኝነት ለኔም ታሳይ እንደ ነበረ አስታውሳለሁ።
እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ዓመት፥ ሁለተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን በሲና በረሓ ሳሉ፥ እግዚአብሔር በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን እንዲህ ሲል አነጋገረው፦
ልጆቻችሁም በእናንተ አለማመን ምክንያት ከእናንተ የመጨረሻው በድን በምድረ በዳ እስኪወድቅ ድረስ አርባ ዓመት ሙሉ ጽኑ መከራ እየተቀበሉ በዚህ ምድረ በዳ ይንከራተታሉ፤
በኃጢአታችሁ ምክንያት አርባ ዓመት ሙሉ ትሠቃያላችሁ፤ ይህም ምድሪቱን ለማጥናት በቈያችሁበት አርባ ቀን ልክ አንዲቱ ዕለት አንድ ዓመት ትሆንባችኋለች፤ በዚያን ጊዜ እኔን መቃወም ምን እንደሚያመጣባችሁ ትገነዘባላችሁ።
እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ተቈጥቶ ስለ ነበር፥ እነዚያ ያሳዘኑት ትውልዶች በሙሉ እስከሚያልቁ ድረስ ለአርባ ዓመት በምድረ በዳ እንዲንከራተቱ አደረጋቸው፤
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፦ “የገንዘብ ቦርሳ፥ ከረጢት፥ ጫማም ሳትይዙ በላክኋችሁ ጊዜ የጐደለባችሁ ነገር ነበርን?” አላቸው። እነርሱም “ምንም የጐደለብን ነገር አልነበረም” ሲሉ መለሱለት።
“ከዚያም እግዚአብሔር አምላካችን እንዳዘዘን ከሲና ተነሥተን እናንተ ባያችሁት አስቸጋሪ በረሓ በተራራማው በአሞራውያን አገር በኩል አድርገን ወደ ቃዴስ በርኔ መጣን።
ይህም የሆነው ቃዴስ በርኔን ትተን ከሄድን ከሠላሳ ስምንት ዓመት በኋላ መሆኑ ነው፤ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ አስቀድሞ በመሐላ በተናገረው መሠረት ለጦርነት የደረሱ የዚያ ትውልድ ወንዶች ሁሉ አልቀው ነበር።
እግዚአብሔር ግን እስከ ዛሬይቱ ዕለት ድረስ ያለፋችሁበትን ሁኔታ የምታዩበት ዐይን፥ የምትሰሙበት ጆሮ፥ የምታስተውሉበት አእምሮ አልሰጣችሁም።
ከግብጽ ምድር የወጡት ለወታደርነት ብቃት የነበራቸው ወንዶች የእግዚአብሔርን ቃል ባለመስማታቸው ሁሉም እስኪያልቁ ድረስ እስራኤላውያን በበረሓ ለአርባ ዓመት ተጓዙ። ለልጅ ልጆቻቸው ሊሰጥ ለቀድሞ አባቶቻቸው ቃል ገብቶ የነበረውን በማርና በወተት የበለጸገውን ምድር በምድረ በዳ ያለቁት ልጆቻቸው እንደማያዩት አረጋግጦ ነበር።