Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ነህምያ 9:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 አርባ ዓመት ሙሉ በበረሓ ረዳሃቸው፤ ከሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ምንም አላሳጣሃቸውም፤ ልብሳቸው አላለቀም፤ እግራቸው አላበጠም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በምድረ በዳ አርባ ዓመት መገብሃቸው፤ ምንም ያጡት አልነበረም፤ ልብሳቸው አላለቀም፤ እግራቸውም አላበጠም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አርባ ዓመትም በምድረ በዳ መገብካቸው፤ ምንም አላጡም፤ ልብሳቸው አላረጀም፥ እግራቸውም አላበጠም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አርባ ዓመ​ትም በም​ድረ በዳ መገ​ብ​ሃ​ቸው፤ ምንም አላ​ሳ​ጣ​ሃ​ቸ​ውም፤ ልብ​ሳ​ቸ​ውም አላ​ረ​ጀም፤ እግ​ራ​ቸ​ውም አላ​በ​ጠም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 አርባ ዓመትም በምድረ በዳ መገብሃቸው፥ ምንም አላጡም፥ ልብሳቸውም አላረጀም፥ እግራቸውም አላበጠም።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 9:21
9 Referencias Cruzadas  

የአንበሳ ደቦሎች ያጣሉ፤ ይራባሉም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ምንም አይጐድልባቸውም፤ መልካም ነገርም አያጡም።


እስራኤላውያንም ወደሚኖሩባት ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስኪደርሱ ድረስ ለአርባ ዓመት ሙሉ ይህን መና ተመገቡ።


“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በውኑ በአርባው ዓመት የምድረ በዳው ጒዞ ጊዜ መሥዋዕትና መባ አቅርባችሁልኛልን?


ለአርባ ዓመትም ያኽል በበረሓ ታገሣቸው


“በእርግጥ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሠራችሁት ሥራ ሁሉ ብዙ በረከት ሰጥቶአችኋል፤ በዚህ በሰፊው በረሓ በሄዳችሁበት ሁሉ ተንከባክቦአችኋል፤ በእነዚህ በአርባ ዓመቶች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ስለ ነበረ ምንም የጐደለባችሁ ነገር አልነበረም።


አርባ ዓመት ሙሉ በበረሓ ስመራችሁ ልብሳችሁ አላረጀም፤ ጫማችሁም አላለቀም።


አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዞች ስለ መጠበቅህ በልብህ ያለውን ሐሳብ ያውቅ ዘንድ አንተን ለመፈተን በዚህ በረሓ አርባ ዓመት ሙሉ በመከራ ውስጥ በማሳለፍ እንዴት እንደ መራህ አስታውስ።


በእነዚህም አርባ ዓመቶች ውስጥ ልብስህ አላለቀም፤ ከጒዞም የተነሣ እግርህ አላበጠም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos