ሕዝቅኤል 12:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ልጅ ሆይ፥ በዓመፀኛ ቤት መካከል ተቀምጠሃል፥ እንዲያዩ ዐይን አላቸው ነገር ግን አያዩም፥ እንዲሰሙም ጆሮ አላቸው ነገር ግን አይሰሙም፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰው ልጅ ሆይ፤ በዐመፀኛ ሕዝብ መካከል ተቀምጠሃል፤ የሚያዩበት ዐይን አላቸው፤ ነገር ግን አያዩም፤ የሚሰሙበትም ጆሮ አላቸው፤ ነገር ግን አይሰሙም፤ ዐመፀኛ ሕዝብ ናቸውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሰው ልጅ ሆይ! አንተ የምትኖረው ዐመፀኞች በሆኑ ሕዝብ መካከል ነው፤ እነርሱ ዐመፀኞች ከመሆናቸው የተነሣ ዐይን እያላቸው አያዩም፤ ጆሮም እያላቸው አይሰሙም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሰው ልጅ ሆይ! በዐመፀኛ ቤት መካከል ተቀምጠሃል፤ እነርሱ ያዩ ዘንድ ዐይን አላቸው ነገር ግን አያዩም፤ ይሰሙም ዘንድ ጆሮ አላቸው፤ ነገር ግን አይሰሙም፤ እነርሱ ዐመፀኛ ቤት ናቸውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ልጅ ሆይ፥ በዓመፀኛ ቤት መካከል ተቀምጠሃል፥ ያዩ ዘንድ ዓይን አላቸው እነርሱም አያዩም፥ ይሰሙም ዘንድ ጆሮ አላቸው እነርሱም አይሰሙም፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና። |
የሰጣቸውንም ድንጋጌ አልተቀበሉም፤ ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤ የሰጣቸውንም ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ ቸል አሉ፤ ለከንቱ ጣዖቶች በመስገድ ራሳቸውም ከንቱዎች ሆኑ፤ የእነርሱን መጥፎ ምሳሌነት እንዳይወርሱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዝ በመሻር በዙሪያቸው የሚኖሩ የአሕዛብን ልማድ ሁሉ ተከተሉ።
ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጉቦን ይወዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።
ለዓመፀኞች ልጆች ወዮላቸው! ይላል ጌታ፤ ከእኔ ዘንድ ያልሆነን ምክር ይመክራሉ፥ ኃጢአትንም በኃጢአት ላይ ለመጨመር ከመንፈሴ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ።
እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።
ነገር ግን እኔ ጌታ የምናገረውን ቃል እናገራለሁ፥ ይፈጸማልም፥ ደግሞም አይዘገይም፥ እናንተ ዓመፀኛ ቤት ሆይ፥ በዘመናችሁ ቃሌን እናገራለሁ እፈጽመዋለሁም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ለዓመፀኛ ቤት እንዲህ በል፦ እነዚህ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ አታውቁምን? በላቸው። ንገራቸው፦ እነሆ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ንጉሥዋንና ልዑሎችዋን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ባቢሎን አመጣቸው።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ወደ እስራኤል ልጆች፥ ወደ ዓመፀኞች አገር፥ በእኔ ላይ ወደ ዐመፁት እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ቀን ድረስ በእኔ ላይ ዐመፁ።
እርሱም “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለሌሎች ግን እያዩ እንዳያዩ እየሰሙም እንዳያስተውሉ በምሳሌዎች ይነገራቸዋል” አላቸው።
እኔ ዓመፃችሁንና የአንገታችሁን ድንዳኔ አውቃለሁና፥ እኔም ዛሬ ከእናንተ ጋር ገና በሕይወት ሳለሁ እናንተ በጌታ ላይ ዐምፃችኋል፥ ይልቁንስ ከሞትሁ በኋላ እንዴት ይሆናል?
“ጌታ አምላክህን በምድረ በዳ እንዴት እንዳስቆጣኸው፥ ከግብጽ ምድር ከወጣህበት ቀን ጀምሮ እዚህ ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በጌታ ላይ እንዳመፃችሁ አስታውስ፥ አትርሳም።