Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 24:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ለዓመፀኛውም ቤት ምሳሌን ተናገር፥ እንዲህም በላቸው፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣደው፥ ድስቱን ጣደው፥ ውኃም ጨምርበት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ለዚህ ዐመፀኛ ቤት እንዲህ ብለህ ተምሳሌት ተናገር፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ብረት ድስት በእሳት ላይ ጣድ፤ ከጣድህም በኋላ ውሃ ጨምርበት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የመሰልኩትን ይህን ምሳሌ ዐመፀኞች ለሆኑት ሕዝቤ ንገራቸው፤ ‘ድስት በእሳት ላይ ጥደህ ውሃ አድርግበት፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ለዐ​መ​ፀ​ኛ​ውም ቤት ምሳ​ሌን ተና​ገር እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጣድ፥ ድስ​ቲ​ቱን ጣድ፥ ውኃም ጨም​ር​ባት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ለዓመፀኛውም ቤት ምሳሌን ተናገር እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣድ፥ ምንቸቲቱን ጣድ፥ ውኃም ጨምርባት።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 24:3
30 Referencias Cruzadas  

እኔም፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! እነርሱ ስለ እኔ፦ ይህ ምሳሌን የሚመስል አይደለምን? ብለዋል አልሁ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ እንቆቅልሽ ጠይቅ፥ ለእስራኤልም ቤት ምሳሌን መስል፥


እነርሱም፦ ቤቶች የሚሰሩበት ጊዜ ቅርብ አይደለምን? ይህች ከተማ ድስት ናት፥ እኛም ሥጋ ነን ብለዋል።


አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ኩርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም፥ አትፍራ፥ ቃላቸውንም አትፍራ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቃላቸውን አትፍራ፥ ፊታቸውንም አትፍራው።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ወደ እስራኤል ልጆች፥ ወደ ዓመፀኞች አገር፥ በእኔ ላይ ወደ ዐመፁት እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ቀን ድረስ በእኔ ላይ ዐመፁ።


ሰማያት ሆይ፤ ስሙ! ምድር ሆይ፤ አድምጪ! ጌታ እንዲህ ተናግሮአልና፤ “ልጆች ወለድሁ፤ አሳደግኋቸውም፤ እነርሱ ግን ዐመጹብኝ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዝገትዋ ላለባት ዝገትዋም ከእርሷ ላልወጣ ድስት፥ ለደም ከተማ ወዮላት! ቁራጭ ቁራጩን አውጣ፥ ዕጣ አልወደቀባትም።


አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ፥ የምነግርህን ስማ እንደ ዓመፀኛው ቤት ዓመፀኛ አትሁን፥ አፍህን ክፈት፥ የምሰጥህንም ብላ።


ዓመጸኛ ወገንና የጌታን ሕግ ለመስማት የማይወድዱ የሐሰት ልጆች ናቸውና፤


ለዓመፀኞች ልጆች ወዮላቸው! ይላል ጌታ፤ ከእኔ ዘንድ ያልሆነን ምክር ይመክራሉ፥ ኃጢአትንም በኃጢአት ላይ ለመጨመር ከመንፈሴ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ።


አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፥ ከቀድሞ ጀምሮ ያለውንም እንቆቅልሽ እናገራለሁ።


“እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፤ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ።


እርሱም “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለሌሎች ግን እያዩ እንዳያዩ እየሰሙም እንዳያስተውሉ በምሳሌዎች ይነገራቸዋል” አላቸው።


ምሳሌውን የተናገረው ስለ እነርሱ መሆኑን ስላወቁ፥ ሊይዙት ፈለጉ፤ ነገር ግን ሕዝቡን ስለ ፈሩ ትተውት ሄዱ።


በዚያ ቀን ምሳሌ ይመስልባችኋል፥ በኀዘን እንጉርጉሮ ያለቅስላችኋል፤ እርሱም፦ “ፈጽመን ጠፍተናል፤ የሕዝቤን ድርሻ ቀየረ፤ ከእኔ እንዴት ወሰደው፤ እርሻችንን ለከዳተኞች ይከፋፍላል” ይላል።


ለዓመፀኛ ቤት እንዲህ በል፦ እነዚህ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ አታውቁምን? በላቸው። ንገራቸው፦ እነሆ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ንጉሥዋንና ልዑሎችዋን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ባቢሎን አመጣቸው።


ነገር ግን እኔ ጌታ የምናገረውን ቃል እናገራለሁ፥ ይፈጸማልም፥ ደግሞም አይዘገይም፥ እናንተ ዓመፀኛ ቤት ሆይ፥ በዘመናችሁ ቃሌን እናገራለሁ እፈጽመዋለሁም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


የሰው ልጅ ሆይ፥ በዓመፀኛ ቤት መካከል ተቀምጠሃል፥ እንዲያዩ ዐይን አላቸው ነገር ግን አያዩም፥ እንዲሰሙም ጆሮ አላቸው ነገር ግን አይሰሙም፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።


ይህች ከተማ ድስት አትሆንላችሁም፥ እናንተም በመካከልዋ ሥጋ አትሆኑም፥ እኔም በእስራኤል ድንበር እፈርድባችኋለሁ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከልዋ ያኖራችኋቸው የተገደሉት እነርሱ ሥጋው ናቸው፥ ድስቱ ይህች ከተማ ናት፥ እናንተን ግን ከመካከልዋ አወጣችኋለሁ።


ግምባርህን ከባልጩት እንደሚጠነክር አልማዝ አድርጌዋለሁ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና አትፍራቸው፥ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ።


ሁለተኛም ጊዜ የጌታ ቃል “ምን ታያለህ?” ሲል ወደ እኔ መጣ። እኔም “የሚፈላ የሸክላ ድስት ከሰሜን ፊቱን አዘንብሎ አያለሁ” አልሁ።


እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አስመረሩ፤ ስለዚህ ጠላታቸው ሆነ፤ እርሱ ራሱ ተዋጋቸው።


በመላ አገሪቱ ራብ በነበረበት በአንድ ወቅት ኤልሳዕ ወደ ጌልጌላ ተመልሶ መጣ፤ በዚያም የነቢያትን ጉባኤ በማስተማር ላይ ሳለ አገልጋዩን “ትልቅ ድስት ጥደህ ወጥ ሥራላቸው” አለው።


ጌታም እንዲህ አለኝ “ከሰሜን በኩል የሚነሣ ጥፋት በምድሪቱ በተቀመጡ ሁሉ ላይ በድንገት ይመጣባቸዋል።


ግን አርኤልንም አስጨንቃለሁ፥ ልቅሶና ዋይታም ይሆንባታል፤ እሷም እንደ አርኤል ትሆንልኛለች።


ሲያናግረኝም መንፈስ ገባብኝ፥ በእግሬም አቆመኝ፥ የሚናገረኝንም ሰማሁ።


እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ በመካከላቸው ነቢይ እንደ ነበረ ያውቃሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios