በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አንድ የውስጥ አደባባይ ሠራ፤ በዚህም አደባባይ ዙሪያ በየሦስቱ ዙር የድንጋይ ረድፍ አንድ የሊባኖስ ዛፍ ሠረገላ ሳንቃ የተጋደመበት ግንብ አደረገ።
ዘፀአት 27:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የማደሪያውን አደባባይ ሥራ፤ በደቡብ በኩል ከጥሩ በፍታ የተሠሩ መጋረጃዎች ይሁኑ፥ የአንዱ ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ አብጅለት፤ በደቡብ በኩል ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ይሁን፤ ከቀጭን በፍታ የተፈተሉ መጋረጃዎች፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለድንኳኑ አደባባይ ክልል መጋረጃዎች ከቀጭን ሐር ሥራ፤ የመጋረጃዎቹም ርዝመት ከደቡብ በኩል አርባ አራት ሜትር ይሁን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለድንኳኑም አደባባይ ሥራ፤ ከጥሩ በፍታ የተሠሩ የአደባባዩ መጋረጃዎችም በደቡብ በኩል ይሁኑ። የአንዱም ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማደሪያውንም አደባባይ ሥራ፤ በደቡብ ወገን የጥሩ በፍታ መጋረጆች ይሁኑለት፥ የአንዱም ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፤ |
በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አንድ የውስጥ አደባባይ ሠራ፤ በዚህም አደባባይ ዙሪያ በየሦስቱ ዙር የድንጋይ ረድፍ አንድ የሊባኖስ ዛፍ ሠረገላ ሳንቃ የተጋደመበት ግንብ አደረገ።
እንዲሁም በዚያኑ ቀን ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን አደባባይ መካከለኛ ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረገ፤ ቀጥሎም በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህል ቁርባንና የኅብረት መሥዋዕት፥ የእንስሶች ስብ ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ይህን ሁሉ መሥዋዕት መያዝ ስለማይችል ነው።
ከተጋጠሙት መጋረጃዎች በአንደኛው መጋረጃ ጠርዝ ላይ አምሳ ቀለበቶች አደረገ፤ እንዲሁም በሁለተኛው መጋረጃ ጠርዝ በሚጋጠሙበት በኩል አምሳ ቀለበቶች አደረገ።
የአደባባዩን መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቹን፥ እግሮቹን፥ የአደባባዩን ደጃፍ መጋረጃ፥ አውታሮቹን፥ ካስማዎቹን፥ ለመገናኛው ድንኳን ለማደሪያው የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ፥
በምሥራቁ በር እንዳለው ዓይነት በሰሜኑ በር ትይዩ ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባ በር ነበር፤ ከአንዱ በር እስከ ሌላው በር አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።
በውስጠኛው መግቢያ በውጭው በኩል በውስጠኛው አደባባይ ለሚዘምሩ ዕቃ ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚመለከት በር አጠገብ ነበረ፥ ወደ ደቡብም ይመለከት ነበር፤ ሌላው ደግሞ ወደ ምሥራቅ በሚመለከተው በር አጠገብ ነበረ፥ ወደ ሰሜን ይመለከት ነበር።
የአደባባዩንም መጋረጆች፥ በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ ያለውን የአደባባዩን ደጃፍ መግብያ መጋረጃ፥ አውታሮቻቸውንም፥ የሚገለገሉባቸውንም ዕቃዎች ሁሉ ይሸከማሉ፤ እነርሱንም በሚመለከት ሊደረግ የሚገባውን ነገር ሁሉ ያድርጋሉ።
በዙሪያውም የሚቆሙትን የአደባባዩ ምሰሶች፥ እግሮቻቸውንም፥ ካስማዎቻቸውንም፥ አውታሮቻቸውንም፥ ዕቃዎቻቸውንና በተጓዳኝ የሚደረጉላቸውን አገልግሎቶች ሁሉ ነው፤ መሸከምም ያለባቸውን ዕቃዎች በየስሙ ትደለድላላችሁ።