Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 27:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “ለድንኳኑ አደባባይ ክልል መጋረጃዎች ከቀጭን ሐር ሥራ፤ የመጋረጃዎቹም ርዝመት ከደቡብ በኩል አርባ አራት ሜትር ይሁን፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ አብጅለት፤ በደቡብ በኩል ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ይሁን፤ ከቀጭን በፍታ የተፈተሉ መጋረጃዎች፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “የማደሪያውን አደባባይ ሥራ፤ በደቡብ በኩል ከጥሩ በፍታ የተሠሩ መጋረጃዎች ይሁኑ፥ የአንዱ ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “ለድ​ን​ኳ​ኑም አደ​ባ​ባይ ሥራ፤ ከጥሩ በፍታ የተ​ሠሩ የአ​ደ​ባ​ባዩ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችም በደ​ቡብ በኩል ይሁኑ። የአ​ን​ዱም ወገን ርዝ​መት መቶ ክንድ ይሁን፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የማደሪያውንም አደባባይ ሥራ፤ በደቡብ ወገን የጥሩ በፍታ መጋረጆች ይሁኑለት፥ የአንዱም ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 27:9
29 Referencias Cruzadas  

በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አንድ የውስጥ አደባባይ ሠራ፤ በዚህም አደባባይ ዙሪያ በየሦስቱ ዙር የድንጋይ ረድፍ አንድ የሊባኖስ ዛፍ ሠረገላ ሳንቃ የተጋደመበት ግንብ አደረገ።


እንዲሁም በዚያኑ ቀን ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን አደባባይ መካከለኛ ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረገ፤ ቀጥሎም በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህል ቊርባንና የኅብረት መሥዋዕት፥ የእንስሶች ስብ ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ይህን ሁሉ መሥዋዕት መያዝ ስለማይችል ነው።


በሁለቱም የቤተ መቅደሱ አደባባዮች የሰማይ ከዋክብት የሚመለኩባቸውን መሠዊያዎች ሠራ፤


ሰሎሞን ለካህናቱ አገልግሎት የሚውለውን ውስጠኛ አደባባይ፥ እንዲሁም ታላቁን አደባባይ አሠራ፤ እንዲሁም በሁለቱ አደባባዮች መካከል የሚገኙትን በሮች አሠርቶ በነሐስ እንዲለበጡ አደረገ።


እያመሰገናችሁ በመቅደሱ በሮች ግቡ፤ ምስጋናም በመስጠት ወደ አደባባዩ ሂዱ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም አወድሱ።


የማቀርበውም በኢየሩሳሌም መካከል በሚገኘው በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን!


በሌላ ስፍራ አንድ ሺህ ቀን ከመቈየት በመቅደስህ አንድ ቀን መዋል የተሻለ ነው፤ በክፉዎች ቤት ከምኖር ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት ዘበኛ ሆኜ መኖርን እመርጣለሁ።


በእግዚአብሔር ቤት ተተክለው በቤተ መቅደስ አደባባይ ውስጥ ተመችቶአቸው ይኖራሉ።


ለእርሱም መደገፊያ ኻያ የነሐስ እግሮች ያላቸው ኻያ ምሰሶዎች ሥራ፤ በእነርሱም ላይ ከብር የተሠሩ ዘንጎችና ኩላቦች ይኑሩ፤


ያደባባዩን መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቹንና እግሮቻቸውን፥ የአደባባዩን በር መጋረጃዎች፥


በአንደኛው ክፍል የመጨረሻ መጋረጃ ዘርፍ ላይ ኀምሳ ቀለበቶች፥ በሁለተኛው ክፍል የመጨረሻ መጋረጃ ዘርፍ ላይ ኀምሳ ቀለበቶች አስገቡ።


ለመገናኛው ድንኳን መግቢያ የሚሆኑት መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቹና የሚቆሙባቸው እግሮች፥ ለአደባባዩ መግቢያ የተሠራው መጋረጃና አውታሮቹ፥ ድንኳኑ የሚተከልባቸው ካስማዎች፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚገኙ የመገልገያ ዕቃዎች፥


ሙሴ በድንኳኑና በመሠዊያው ዙሪያ የሚሆነውን ድንኳኑ ሠራ፤ ወደ ድንኳኑ በሚያስገባው ደጃፍ መጋረጃ ሰቀለ፤ በዚህም ዐይነት ሥራውን ሁሉ ፈጸመ።


አደባባዩን በዙሪያው ትከል፤ መጋረጃውንም በድንኳኑ መግቢያ ደጃፍ ላይ ስቀለው።


በስተመጨረሻ ያለው ክፍል ወደ አደባባዩ ያመራ ነበር፤ እርሱም ሲለካ ኻያ ክንድ ሆኖ ተገኘ።


ከዚያ በኋላ ሰውዬው ወደ ውጪው አደባባይ አመጣኝ፤ በአደባባዩ ዙሪያ የድንጋይ ንጣፍና ክፍሎች ነበሩ ከንጣፉም ፊት ለፊት ሠላሳ ክፍሎች ነበሩ።


ያ ሰው በሰሜን በኩል ወደ ውጪው አደባባይ ትይዩ ያለውን የቅጽር በር ለካ፤


በምሥራቁ በር እንዳለው ዐይነት በሰሜኑ በር ትይዩ ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባ በር ነበር፤ ሰውዬው ከአንዱ በር እስከ ሌላው በር ሲለካ አንድ መቶ ክንድ ሆነ።


ያ ሰው በደቡቡ ቅጽር በር በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ ወሰደኝ፤ እርሱም የቅጽር በሩን ሲለካ ስፋቱ በውጪ ካሉት የቅጥር በሮች ጋር እኩል ሆኖ ተገኘ።


ያም ሰው በምሥራቁ ቅጽር በር በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ ወሰደኝ፤ እርሱም የቅጽሩን በር ሲለካው መጠኑ ልክ እንደ ሌሎቹ ሆኖ አገኘው።


ከዚህም በኋላ ያ ሰው እኔን ወደ ውስጠኛው አደባባይ አስገባኝ፤ እዚያም ሁለት ክፍሎች ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ በሰሜን የቅጽር በር አጠገብ ወደ ደቡብ የሚያመለክት ሲሆን፥ ሁለተኛው በደቡብ የቅጽር በር አጠገብ ወደ ሰሜን የሚያመለክት ነበር።


ኻያ ክንድ የሆነው የውስጥ አደባባይ ታልፎ በውጪው አደባባይ ንጣፍ ትይዩ የተሠሩት ክፍሎች ከፎቅ ወደ ፎቅ እያደጉ ወደ ሦስተኛ ፎቅ ደርሰዋል።


በቅጥር ግቢው መጋረጃዎች፥ በድንኳኑና በመሠዊያው ዙሪያ ባለው የቅጥር ግቢው በር መጋረጃ፥ በአውታሮቹ፥ እንዲሁም ለእነርሱ መጠቀሚያ በሚሆኑ ዕቃዎች ሁሉ ላይ ነው።


እንዲሁም በድንኳኑና በመሠዊያው ዙሪያ ለሚገኘው አደባባይ የተሠሩትን መጋረጃዎችና አውታሮች፥ ለአደባባዩ መግቢያ በር የሚሆኑትን መጋረጃዎችና ለእነዚህ መገልገያ የተመደቡትን ሌሎችንም ዕቃዎች ሁሉ ይሸከማሉ፤ ለእነዚህም ዕቃዎች የሚሆነውን ማንኛውንም አገልግሎት ይፈጽማሉ።


እንዲሁም በድንኳኑ ዙሪያ የሚገኘውን አደባባይ ምሰሶችን፥ እግሮቻቸውን፥ ካስማዎችን፥ አውታሮችንና ለእነዚህ ሁሉ መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች ነው፤ እያንዳንዱም መሸከም ያለበትን ዕቃ በየስሙ ትመድብለታለህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos