1 ነገሥት 8:64 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)64 እንዲሁም በዚያኑ ቀን ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን አደባባይ መካከለኛ ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረገ፤ ቀጥሎም በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህል ቁርባንና የኅብረት መሥዋዕት፥ የእንስሶች ስብ ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ይህን ሁሉ መሥዋዕት መያዝ ስለማይችል ነው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም64 በዚያ ዕለትም ንጉሡ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት ያለውን የአደባባዩን መካከለኛ ክፍል ቀደሰ፤ በዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባንና የኅብረት መሥዋዕቱን ሥብ አቀረበ፤ ይህን ያደረገውም በእግዚአብሔር ፊት የነበረው የናስ መሠዊያ በጣም ትንሽ ከመሆኑ የተነሣ፣ የሚቃጠለውን መሥዋዕት የእህሉን ቍርባንና የኅብረት መሥዋዕቱን ስብ መያዝ ባለመቻሉ ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም64 እንዲሁም በዚያኑ ቀን ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን አደባባይ መካከለኛ ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረገ፤ ቀጥሎም በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህል ቊርባንና የኅብረት መሥዋዕት፥ የእንስሶች ስብ ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ይህን ሁሉ መሥዋዕት መያዝ ስለማይችል ነው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)64 በእግዚአብሔር ፊት ያለው የናሱ መሠዊያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን የሰላሙንም መሥዋዕት ስብ ይይዝ ዘንድ ታናሽ ስለ ነበረ፥ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ የሰላሙንም መሥዋዕት ስብ አሳርጎአልና በእግዚአብሔር ቤት ፊት የነበረውን የአደባባዩን መካከል ንጉሡ በዚያ ቀን ቀደሰ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)64 በእግዚአብሔር ፊት ያለው የናሱ መሠዊያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን የደኅንነቱንም መሥዋዕት ስብ ይይዝ ዘንድ ታናሽ ስለ ነበረ፥ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን የደኅንነቱንም መሥዋዕት ስብ አሳርጎአልና በእግዚአብሔር ቤት ፊት የነበረውን የአደባባዩ መካከል ንጉሡ በዚያ ቀን ቀደሰ። Ver Capítulo |