ልብህን ስማ፤ መስጠት እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘው ተግባር ነው። በምታቀርበው ጊዜ፣ ከሁሉ የተመረጠውን፣ ከልብ የመነጨውን አቅርብ። እግዚአብሔር ብዙ ሰጥቶናልና፣ የማንገባውን ያህል ባርኮናልና በደስታ እናድርገው። የተረፈንን ብቻ ብንሰጥ፣ ሕይወትም እንዲሁ ለእኛ የምትሰጠን የተረፈውን ብቻ እንደሆነ እናውቃለን።
ለራሳችን እንደምንሰጥ አድርገን እንስጥ፤ በግዴታ ወይም ተመልሶ እንዲሰጠን በማሰብ አይደለም። ሌላው እንዲያየን ወይም እንዲያመሰግነን ሳንፈልግ፣ በትህትና እንስጥ። ግራ እጃችን የቀኝ እጃችን የሰጠችውን እንኳን አታውቅ። ጌታችን በደስታ የሚሰጠውን ይወዳል፤ ልባችንን ያውቃልና።
እያንዳንዳችን በልቡ እንዳሰበው ይስጥ፤ በኀዘን ወይም በግዴታ አይደለም፤ እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና። (2ኛ ቆሮንቶስ 9:7) መስጠት እግዚአብሔር ለእኛ ከሰጠን ውስጥ የምናቀርብለት የአምልኮ ምልክት ነው። እግዚአብሔር ሲሰጥ በልግስና እና ያለገደብ ነው። ስለዚህ ከልብ ስንሰጥ፣ እግዚአብሔር አብዝቶ እንዲባርከን በር እንከፍታለን። በሰጠህ መጠን ትቀበላለህ።
አመንዝሮች ሆይ፤ ከዓለም ጋራ ወዳጅነት ከእግዚአብሔር ጋራ ጠላትነት መሆኑን አታውቁምን? ስለዚህ የዓለም ወዳጅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኗል።
ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ፣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት፤ ሰላምም አትበሉት፤
የሚቀበለው ሰው፣ የክፉ ሥራው ተባባሪ ይሆናልና።
ነገር ግን አሁን የጻፍሁላችሁ፣ “ወንድም ነኝ” እያለ ከሚሴስን ወይም ከሚስገበገብ ወይም ጣዖትን ከሚያመልክ ወይም ከሚሳደብ ወይም ከሚሰክር ወይም ከሚቀማ ጋራ እንዳትተባበሩ ነው፤ ከእንደዚህ ዐይነቱ ሰው ጋራ ምግብ እንኳ አትብሉ።
በሌሊት አምርራ ታለቅሳለች፤ እንባዋ በጕንጮቿ ላይ ይወርዳል፤ ከወዳጆቿ ሁሉ መካከል፣ የሚያጽናናት ማንም የለም፤ ባልንጀሮቿ ሁሉ ከድተዋታል፤ ጠላቶቿም ሆነዋል።
ወንድሞች ሆይ፤ ያለ ሥርዐት ከሚመላለስ እና ከእኛ በተቀበላችሁት ትምህርት መሠረት ከማይኖር ወንድም እንድትርቁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዝዛችኋለን፤
መከፋፈል የሚያመጣን ሰው አንድ ጊዜ ምከረው፤ ለሁለተኛ ጊዜ አስጠንቅቀው፤ ከዚያ ካለፈ ከርሱ ጋራ አንዳች ነገር አይኑርህ።
እንዲህ ዐይነቱ ሰው የሳተና ኀጢአተኛ ነው፤ ራሱንም እንደሚኰንን ዕወቅ።
ባለራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሥ ኢዮሣፍጥንም እንዲህ አለው፣ “አንተ ክፉውን መርዳትህና እግዚአብሔርን የሚጠሉትን ማፍቀርህ ተገቢ ነውን? ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ ባንተ ላይ ነው፤
በዚህ መልእክት ላይ ላለው ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፣ እንደዚህ ያለውን ሰው በጥንቃቄ ተከታተሉት፤ በሥራውም እንዲያፍር ከርሱ ጋራ አትተባበሩ።
ሆኖም እንደ ወንድም ገሥጹት እንጂ እንደ ጠላት አትቍጠሩት።
ብፁዕ ነው፣ በክፉዎች ምክር የማይሄድ፣ በኀጢአተኞች መንገድ የማይቆም፣ በፌዘኞችም ወንበር የማይቀመጥ፤
ነገር ግን ደስ የሚሠኘው በእግዚአብሔር ሕግ ነው፤ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያሰላስለዋል።
እርሱም በወራጅ ውሃ ዳር እንደ ተተከለች፣ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣ ቅጠሏም እንደማይጠወልግ ዛፍ ነው፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
አምላክ ሆይ፤ ክፉዎችን ብትገድላቸው ምናለበት! ደም የተጠማችሁ ሰዎች ሆይ፤ ከእኔ ራቁ!
አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ፤ የልቤንም ሐሳብ ገና ከሩቁ ታስተውላለህ።
ስለ አንተ በክፉ ሐሳብ ይናገራሉና፤ ጠላቶችህም ስምህን በከንቱ ያነሣሉ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚጠሉህን አልጠላምን? በአንተ ላይ የሚነሡትንስ አልጸየፍምን?
በፍጹም ጥላቻ ጠልቻቸዋለሁ፤ ባላጋራዎቼም ሆነዋል።
ሩጫችሁ መልካም ነበር፤ ታዲያ ያሰናከላችሁ፣ ለእውነትስ እንዳትታዘዙ የከለከላችሁ ማን ነው?
እንዲህ ያለው ማባበል ከሚጠራችሁ የመጣ አይደለም፤
“ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ ያቦካል።”
ዓለምን ወይም በዓለም ያለውን ማንኛውንም ነገር አትውደዱ፤ ማንም ዓለምን ቢወድድ የአብ ፍቅር በርሱ ዘንድ የለም፤
ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፦ የሥጋ ምኞት፣ የዐይን አምሮትና የኑሮ ትምክሕት ከዓለም እንጂ ከአብ የሚመጣ አይደለም።
ዓለምና ምኞቱ ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ግን ለዘላለም ይኖራል።
ወንድሞች ሆይ፤ መለያየትን ከሚፈጥሩትና የተማራችሁትን ትምህርት በመቃወም በጕዟችሁ መሰናክል ከሚያደርጉት እንድትጠነቀቁ አሳስባችኋለሁ፤ ከእነርሱም ራቁ።
እንደ እነዚህ ያሉት ሰዎች የሚያገለግሉት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ሳይሆን የራሳቸውን ሆድ ነው። በለሰለሰ አንደበታቸውና በሽንገላ የዋሆችን ያታልላሉ።
የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ አንተ ግን ከዚህ ሁሉ ሽሽ፤ ጽድቅን፣ እውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ትዕግሥትንና ገርነትን ተከታተል።
መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤ በብዙ ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የመሰከርህለትንና የተጠራህበትን የዘላለም ሕይወት አጥብቀህ ያዝ።
ልጄ ሆይ፤ ኀጢአተኞች ቢያባብሉህ፣ ዕሺ አትበላቸው፤
“ከእኛ ጋራ ናና፣ ደም ለማፍሰስ እናድባ፤ በደል በሌለበት ሰው ላይ እንሸምቅ፤
እንደ መቃብር፣ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱ፣ ከነሕይወታቸው በሙሉ እንዋጣቸው፤
ውድ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ በየዐይነቱ እናገኛለን፤ ቤቶቻችንንም በዝርፊያ እንሞላለን፤
ከእኛ ጋራ ዕጣህን ጣል፤ የጋራ ቦርሳ ይኖረናል” ቢሉህ፣
ልጄ ሆይ፤ ዐብረሃቸው አትሂድ፤ በሚሄዱበትም መንገድ እግርህን አታንሣ፤
ወንድሞች ሆይ፤ አንድ ሰው በኀጢአት ውስጥ ገብቶ ቢገኝ፣ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ በገርነት ልትመልሱት ይገባል። ነገር ግን አንተም እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።
በሁሉም ዐይነት ዐመፃ፣ ክፋት፣ ስግብግብነትና ምግባረ ብልሹነት ተሞልተዋል፤ ቅናትን፣ ነፍስ ገዳይነትን፣ ጥልን፣ አታላይነትንና ተንኰልን የተሞሉ ናቸው፤ ሐሜተኞች፣
ወንጌሉም ስለ ልጁ፣ በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ሆነ፣
ስም አጥፊዎች፣ አምላክን የሚጠሉ፣ ተሳዳቢዎች፣ ትዕቢተኞችና ትምክሕተኞች ናቸው፤ ክፋትን የሚሠሩበትን መንገድ ያውጠነጥናሉ፤ ለወላጆቻቸው አይታዘዙም።
የማያስተውሉ፣ ውል የሚያፈርሱ፣ ርኅራኄ የሌላቸውና ጨካኞች ናቸው።
ይህን የሚያደርጉ ሁሉ ሞት ይገባቸዋል የሚለውን ትክክለኛ የሆነውን የእግዚአብሔርን ሕግ ቢያውቁም፣ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ እንዲህ የሚያደርጉትንም ያበረታታሉ።
ዓለምን ወይም በዓለም ያለውን ማንኛውንም ነገር አትውደዱ፤ ማንም ዓለምን ቢወድድ የአብ ፍቅር በርሱ ዘንድ የለም፤
ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፦ የሥጋ ምኞት፣ የዐይን አምሮትና የኑሮ ትምክሕት ከዓለም እንጂ ከአብ የሚመጣ አይደለም።