የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች

መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን


መጽሐፈ ሲራክ 49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
መጽሐፈ ሲራክ 49

ንጉሡ ኢዮ​ስ​ያስ

1 የኢ​ዮ​ስ​ያስ መታ​ሰ​ቢ​ያው በቀ​ማሚ ብል​ሃት እንደ ተቀ​መመ ሽቱ ነው፤ እንደ ማርም በአፍ ሁሉ ጣፋጭ ነው፤ በመ​ጠጥ ግብ​ዣም ጊዜ እንደ ዘፈን ነው።

2 እርሱ የቀና ነው፤ ሕዝ​ቡ​ንም መለ​ሳ​ቸው፤ የኀ​ጢ​አ​ት​ንም ርኵ​ሰት ሁሉ አስ​ወ​ገደ።

3 ልቡ​ና​ው​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀና፤ በኃ​ጥ​ኣ​ንም ዘመን ጽድ​ቅን አጸ​ናት።

4 ከዳ​ዊት፥ ከሕ​ዝ​ቅ​ያ​ስና ከኢ​ዮ​ስ​ያስ በቀር ሁሉም በድ​ለ​ዋል፤ የል​ዑ​ልን ሕግ ትተ​ዋ​ልና፤ የይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት አለቁ።

5 ኀይ​ላ​ቸ​ውን ለሌላ ሰጥ​ተ​ዋ​ልና፥ ክብ​ራ​ቸ​ው​ንም ለሌላ ሕዝብ ሰጥ​ተ​ዋ​ልና።

ነቢዩ ኤር​ም​ያስ

6 የተ​መ​ረ​ጠ​ች​ው​ንና የተ​ቀ​ደ​ሰ​ች​ውን ከተማ አቃ​ጠ​ሏት። መከራ አጽ​ን​ተ​ው​ባ​ታ​ልና እንደ ነቢዩ ኤር​ም​ያስ ትን​ቢት ጎዳ​ና​ዋን አጠፉ።

7 አሠ​ቃ​ይ​ተ​ው​ታ​ልና፤ እርሱ ግን ነቢይ ይሆን ዘንድ፥ ይነ​ቅል ዘንድ፥ ያጠ​ፋም ዘንድ፥ እን​ደ​ዚ​ሁም ይተ​ክል ዘንድ፥ ይሠ​ራም ዘንድ በእ​ናቱ ማኅ​ፀን ተመ​ረጠ።

ነቢዩ ሕዝ​ቅ​ኤል

8 ሕዝ​ቅ​ኤ​ልም የጌ​ት​ነ​ቱን ራእይ አየ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በኪ​ሩ​ቤል ሠረ​ገላ ላይ አየው።

9 ጠላ​ቶ​ቹ​ንም በመ​ዓት ዐሰ​ባ​ቸው፥ የጻ​ድ​ቃ​ን​ንም ጎዳ​ና​ቸ​ውን በመ​ል​ካም አቀና።

10 የዐ​ሥራ ሁለቱ ነቢ​ያ​ትም አጽ​ሞ​ቻ​ቸው በየ​ቦ​ታ​ቸው ለመ​ለሙ፤ ያዕ​ቆ​ብን አጽ​ና​ን​ተ​ው​ታ​ልና፥ በታ​መነ ተስ​ፋም አድ​ነ​ው​ታ​ልና።

11 ዘሩ​ባ​ቤ​ልን እን​ዴት እና​ገ​ን​ነው ይሆን! እር​ሱስ በቀኝ እጅ እን​ዳለ እንደ ሐቲም ቀለ​በት ነው።

12 የዮ​ሴ​ዴቅ ልጅ ዮሴ​ዕም እን​ዲሁ ነበረ፤ በዘ​መ​ና​ቸ​ውም ቤተ መቅ​ደ​ስን ሠሩ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ክብር የተ​ዘ​ጋጀ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕዝብ አከ​በ​ሩት።

13 የነ​ሕ​ም​ያም መታ​ሰ​ቢ​ያው ብዙ ነው፤ የወ​ደ​ቀ​ች​ውን ቅጽር አነ​ሣ​ልን፤ ደጃ​ፎ​ች​ንም አቆ​መ​ልን፤ ቍል​ፍ​ንም ሠራ​ልን፥ ቤታ​ች​ን​ንም ገነ​ባ​ልን።

14 እንደ ሄኖክ ያለ ሰው በም​ድር የተ​ፈ​ጠረ የለም፤ እርሱ ከዚህ ዓለም ተወ​ሰደ።

15 እንደ ዮሴ​ፍም ያለ ሰው አል​ተ​ወ​ለ​ደም፤ ለወ​ን​ድ​ሞቹ አለቃ ሆነ፤ ለሕ​ዝ​ቡም ኀይል ሆነ፥ ለአ​ጽ​ሞ​ቹም ይቅ​ር​ታን አገኘ።

16 ሴምና ሴት ከሰው ይልቅ ከበሩ፥ አዳ​ምም ከተ​ፈ​ጠ​ረው ሕያው ፍጥ​ረት ሁሉ ከበረ፤