Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ሲራክ 50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የኦ​ንያ ልጅ ስም​ዖን

1 የኦ​ንያ ልጅ ታላቁ ካህን ስም​ዖ​ንም በሕ​ይ​ወቱ ቤተ መቅ​ደ​ስን አደሰ፤ በዘ​መ​ኑም ቤተ መቅ​ደ​ስን አጸና።

2 እን​ዲ​ሁም የቅ​ጥ​ሩን መሠ​ረት ዕጥፍ አድ​ርጎ ሠራ ካህን የሚ​ለ​ብ​ሰ​ው​ንም ቀጭን ልብስ ሠራ።

3 በዘ​መ​ኑም የው​ኃ​ዎች ምን​ጮች አል​ጐ​ደ​ሉም፤ የጕ​ድ​ጓ​ዱም ውኃ ብዛቱ እንደ ባሕር ውኃ ነበር።

4 ሕዝ​ቡም እን​ዳ​ይ​ወ​ድቁ ይጠ​ነ​ቀ​ቅ​ላ​ቸው ነበር፤ ከተ​ማ​ዋ​ንም ከጠ​ላት ለመ​ከ​ላ​ከል መሸገ።

5 ከቤተ መቅ​ደስ መጋ​ረጃ በወጣ ጊዜም በሕ​ዝቡ መካ​ከል ተከ​በረ።

6 በደ​መና ውስጥ እንደ አጥ​ቢያ ኮከ​ብና በም​ል​ዐት ቀን እንደ ሙሉ ጨረቃ ነበረ።

7 በል​ዑል መቅ​ደ​ስም ላይ እን​ደ​ም​ታ​በራ ፀሐይ ነበረ። በብ​ሩህ ደመ​ናም ውስጥ ብር​ሃን እን​ደ​ሚ​ሰጥ ቀስተ ደመና ነበር።

8 እንደ መጸው ወራት ጽጌ​ረ​ዳም ነበር፤ በውኃ መፍ​ሰሻ አጠ​ገብ እን​ደ​ሚ​ያ​ፈራ አበ​ባም ነበር፤ በመ​ከ​ርም ወራት እንደ ሊባ​ኖስ ዛፍ ቅር​ን​ጫፍ ነበር።

9 በጥና እሳት ላይ እን​ዳለ ነጭ ዕጣ​ንም ነበር። ተመ​ትቶ እንደ ተሠራ የወ​ርቅ ዕቃም ነበር። በጌጥ ላይ እን​ዳለ የከ​በረ ዕን​ቍም ነበር፤

10 ፍሬዋ ብዙ እንደ ሆነ የዘ​ይት እን​ጨት፥ ከደ​መና በታች እን​ደ​ሚ​ያ​ድግ የዋ​ንዛ ዛፍ ነበር።

11 እር​ሱም የክ​ብር ልብ​ሱን በለ​በሰ ጊዜ፥ የመ​መ​ኪ​ያ​ው​ንም ጌጥ በለ​በሰ ጊዜ፥ ወደ ተቀ​ደ​ሰ​ውም መሠ​ዊያ በወጣ ጊዜ፥ በቅ​ድ​ስና ልብሱ ተከ​በረ።

12 ከካ​ህ​ና​ቱም እጅ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ሥጋ ክፍል በተ​ቀ​በለ ጊዜ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ይቆም ነበር፤ ወን​ድ​ሞ​ቹም በዙ​ሪ​ያው ቁመው ይጋ​ር​ዱት ነበር፤ እንደ ሊባ​ኖስ ለጋ ዝግ​ባና እንደ ዘን​ባ​ባም ዛፍ ይከ​ቡት ነበር።

13 እን​ዲ​ሁም የአ​ሮን ልጆች ሁሉ የክ​ብር ልብ​ሳ​ቸ​ውን ለብ​ሰው፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መባእ በእ​ጃ​ቸው ይዘው፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ፊት ይቆሙ ነበር።

14 በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ሥራ​ቸ​ውን ይፈ​ጽሙ ነበር፤ ሁሉን የሚ​ችል የል​ዑ​ል​ንም መሥ​ዋ​ዕት ያዘ​ጋጁ ነበር።

15 የወ​ይ​ኑን ጽዋዕ ይዞ እጁን አነሣ፤ የወ​ይ​ኑን ዘለላ ደምም አፈ​ሰሰ፤ ለን​ጉሠ ነገ​ሥት ለል​ዑል በጎ መዓዛ አድ​ርጎ በመ​ሠ​ዊ​ያው እግር ሥር ያፈ​ስ​ሰው ነበር።

16 የአ​ሮ​ንም ልጆች እየ​ጮሁ ምስ​ጋ​ና​ውን ይና​ገሩ ነበር፤ ተመ​ትቶ የተ​ሠራ የብር መለ​ከ​ት​ንም ይነፉ ነበር፤ በል​ዑ​ልም ፊት ማሰ​ባ​ሰ​ቢያ ሊሆን ቃላ​ቸ​ውን ያሰሙ ነበር።

17 ያን ጊዜም ሕዝቡ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ያርፉ ነበር፤ በም​ድር ላይም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ይሰ​ግዱ ነበር፤ ሁሉን ለሚ​ገዛ ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምስ​ጋና ያቀ​ርቡ ነበር።

18 መዘ​ም​ራ​ኑም በቃ​ላ​ቸው ያመ​ሰ​ግ​ኑት ነበር፥ የዜ​ማ​ቸ​ውም ድምፅ ቤቱን ያስ​ተ​ጋ​ባው ነበር።

19 ሕዝ​ቡም ወደ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልዩ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ጸን​ተው ሥር​ዐ​ቱን እስ​ኪ​ጨ​ርሱ ድረስ ይቅር በሚል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይለ​ምኑ ነበር፤ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ያከ​ና​ውኑ ነበር።

20 ከዚ​ህም በኋላ እርሱ ወርዶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በረ​ከት በአ​ን​ደ​በቱ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ፥ በስ​ሙም ይመኩ ዘንድ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ላይ እጁን አነሣ።

21 የል​ዑ​ል​ንም በረ​ከት ይቀ​በሉ ዘንድ ዳግ​መኛ ሰገዱ።

22 አሁ​ንም በሁ​ሉም ቦታ ብዙ ተአ​ም​ራት የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን፥ ከእ​ና​ታ​ችን ማኅ​ፀን ጀምሮ ዘመ​ና​ች​ን​ንም የሚ​ያ​ረ​ዝ​መ​ውን፥ እንደ ቸር​ነ​ቱም ይቅ​ር​ታ​ውን የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ል​ንን፥ የሁ​ሉን ፈጣሪ አመ​ስ​ግ​ኑት።

23 የል​ቡና ደስ​ታ​ንም ይሰ​ጠ​ናል፤ በዘ​መ​ና​ች​ንም ሰላ​ምን ያደ​ር​ጋል፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ለዘ​ለ​ዓ​ለም።

24 በቸ​ር​ነ​ቱም ከእኛ ጋር የታ​መነ ነው፤ በዘ​መ​ና​ች​ንም አዳ​ነን።

25 ሰው​ነቴ ሁለት ወገ​ኖ​ችን ጠላች፤ ሦስ​ተ​ኛው ግን ሕዝብ አይ​ደ​ለም።

26 እነ​ዚ​ህም በሰ​ማ​ር​ያና በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ተራራ የሚ​ኖሩ፥ በሰ​ቂማ የሚ​ኖሩ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ንም ሰዎች ናቸው።

27 ጥበ​ብን ከልቡ ያነ​ቃት የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሰው የሲ​ራክ አል​ዓ​ዛር ልጅ እኔ ኢያሱ የጥ​በ​ብ​ንና የም​ክ​ርን ትም​ህ​ርት በዚህ መጽ​ሐፍ ጻፍሁ።

28 ይህን እን​ደ​ዚህ የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በዚ​ያም የሚ​ራ​ቀቅ ብፁዕ ነው፤ ይህ​ንም በልቡ የሚ​ጠ​ብ​ቀው ጠቢብ ይሆ​ናል።

29 ይህ​ንም የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉን ይች​ላል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብር​ሃን ይመ​ራ​ዋ​ልና።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች