ቲቶ 3:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስላደረግነው የጽድቅ ሥራ ሳይሆን፣ ከምሕረቱ የተነሣ አዳነን። ያዳነንም ዳግም ልደት በሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታደስ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ በጽድቅ በሠራናቸው ሥራዎች ሳይሆን እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ እኛን አዳነን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ በሠራነው የጽድቅ ሥራ ሳይሆን ራሱ በምሕረቱ አዳነን፤ ያዳነንም በአዲስ ልደት መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በተገኘው መታደስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ |
የሚምረኝ፥ መሸሸጊያዬ፥ መጠጊያዬና አዳኜ፤ መታመኛዬም፤ እርሱን ታመንሁ፤ ሕዝቡንም ከእኔ በታች የሚያስገዛልኝ።
ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፤ እናንተም ከርኵሰታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ፤ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አነጻችኋለሁ።
በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።
እኔስ “ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤
ይህን ዓለም አትምሰሉ፤ ልባችሁንም አድሱ፤ እግዚአብሔር የሚወደውን መልካሙንና እውነቱን፥ ፍጹሙንም መርምሩ።
እንግዲህ እናንተ እንዲህ ስትሆኑ እነማን ናችሁ? ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፤ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችኋልም።
ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ የኦሪትን ሥራ በመሥራት እንደማይጸድቅ እናውቃለንና፤ እኛም የኦሪትን ሥራ በመሥራት ሳይሆን በእርሱ በማመናችን እንጸድቅ ዘንድ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነናል፤ ሰው ሁሉ በኦሪት ሥራ አይጸድቅምና።
ምድራቸውን ትወርሳት ዘንድ የምትገባው ስለ ጽድቅህና ስለ ልብህ ቅንነት አይደለም፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ በሚያጠፋቸው በእነዚያ አሕዛብ ኀጢአት ምክንያትና ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው።
ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፤ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ፥ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፤
እንግዲህ ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን፥ ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ።
እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል፥ በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፥ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።
በኋላም የካዱትን እንደ ገና ለንስሓ እነርሱን ማደስ አይቻልም፤ ራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታልና፥ ያዋርዱትማልና።
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኀይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።
እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።
ይህም ውሃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፤ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤