Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 9:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ጻድቅ ብሆን አፌ ይወ​ቅ​ሰ​ኛል፤ ፍጹ​ምም ብሆን ጠማማ ያደ​ር​ገ​ኛል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ንጹሕ ብሆን እንኳ፣ አንደበቴ ይፈርድብኛል፤ እንከን የለሽ እንኳ ብሆን፣ በደለኛ ያደርገኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ጻድቅ ብሆን እንኳን አፌ ይወቅሰኛል፥ ፍጹምም ብሆን ጠማማ ያደርገኛል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እኔ ንጹሕና እውነተኛ ነኝ፤ ነገር ግን አነጋገሬ በደለኛ ያደርገኛል፤ የምናገራቸው ንግግሮች ሁሉ ይፈርዱብኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ጻድቅ ብሆን አፌ ይወቅሰኛል፥ ፍጹምም ብሆን ጠማማ ያደርገኛል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 9:20
24 Referencias Cruzadas  

አው​ስ​ጢድ በሚ​ባል ሀገር ስሙ ኢዮብ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ቅን፥ ንጹ​ሕና ጻድቅ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ነበር።


በደ​ለኛ ብሆን ወዮ​ልኝ፤ ጻድ​ቅም ብሆን ራሴን አላ​ነ​ሣም፤ ጕስ​ቍ​ል​ና​ንም ጠገ​ብ​ኋት።


መተ​ላ​ለ​ፌን በከ​ረ​ጢት ውስጥ አት​መ​ሃል፥ ኀጢ​አ​ቴ​ንም ለብ​ጠ​ህ​ባ​ታል።


ኢዮብ እንደ ጠቢብ በዕ​ው​ቀት አይ​ና​ገ​ርም፥ ቃሉም እንደ ምሁር አይ​ደ​ለም።


ኢዮብ ግን አፉን በከ​ንቱ ይከ​ፍ​ታል፥ ያለ ዕው​ቀ​ትም ቃሉን ያበ​ዛል።”


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ንጹሕ የሚ​ሆን ሟች ማን ነው? በሥ​ራ​ውስ የሚ​ጸ​ድቅ ሰው ማን ነው?


በጽ​ድቅ ብጠ​ራው፥ ባይ​ሰ​ማ​ኝም፥ የእ​ር​ሱን ፍርድ እለ​ም​ና​ለሁ።


“በእ​ው​ነት እን​ዲህ እንደ ሆነ ዐወ​ቅሁ፤ ሰውስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድቅ መሆን እን​ዴት ይች​ላል?


ሰው​ነ​ቶቼ ሁሉ ተነ​ዋ​ወጡ፤ እን​ግ​ዲህ ንጹሕ አድ​ር​ገህ እን​ደ​ማ​ት​ተ​ወኝ አው​ቃ​ለሁ፥


“ኃጢ​ኣ​ተኛ ሰው ከሆ​ንሁ፤ ስለ ምን አል​ሞ​ት​ሁም?


ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም እስ​ራ​ኤል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይታ​መ​ናል።


የሚ​ም​ረኝ፥ መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ፥ መጠ​ጊ​ያ​ዬና አዳኜ፤ መታ​መ​ኛ​ዬም፤ እር​ሱን ታመ​ንሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ከእኔ በታች የሚ​ያ​ስ​ገ​ዛ​ልኝ።


ኃጥእ ከነገር ብዛት የተነሣ ከኀጢአት አያመልጥም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።


ጠማማ ልብ ያለው መልካም ነገርን አያገኝም፥ አንደበቱን የሚለዋውጥም በክፉ ላይ ይወድቃል።


እኔም፥ “ከን​ፈ​ሮች የረ​ከ​ሱ​ብኝ ሰው በመ​ሆኔ፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው በረ​ከ​ሱ​ባ​ቸው ሕዝብ መካ​ከል በመ​ቀ​መጤ ዐይ​ኖች የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ ንጉ​ሡን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ አዩ ጠፍ​ቻ​ለ​ሁና ወዮ​ልኝ!” አልሁ።


ራሱን ሊያ​ከ​ብር ባል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም ሊንቅ ወድዶ፥ “ባል​ን​ጀ​ራዬ ማነው?” አለው።


እር​ሱም፥ “እና​ን​ተስ ለሰው ይም​ሰል ትመ​ጻ​ደ​ቃ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልቡ​ና​ች​ሁን ያው​ቃል፤ በሰው ዘንድ የከ​በረ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ናቀ ይሆ​ና​ልና።


ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos