ሩት 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቦዔዝም ከከተማይቱ ሽማግሌዎች አሥር ሰዎች ጠርቶ፦ በዚህ ተቀመጡ አላቸው። እነርሱም ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቦዔዝ ከከተማዪቱ ሽማግሌዎች ዐሥሩን ጠርቶ፣ “እዚህ ተቀመጡ” አላቸው፤ እነርሱም ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቦዔዝም ከከተማይቱ ሽማግሌዎች ዐሥር ሰዎች ጠርቶ፦ “በዚህ ተቀመጡ” አላቸው። እነርሱም ተቀመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ቦዔዝ ከከተማው ሽማግሌዎች ዐሥሩን መርጦ “እዚህ ተቀመጡ” አላቸው፤ እነርሱም ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቦዔዝም ከከተማይቱ ሽማግሌዎች ዐሥር ሰዎች ጠርቶ “በዚህ ተቀመጡ፤” አላቸው። |
ለእርሱ ከታጨች በኋላ ጌታዋን ደስ ባታሰኘው በዎጆ ይስደዳት፤ ነገር ግን ለሌላ ወገን ይሸጣት ዘንድ አይገባውም። እርሱ አርክሶአታልና።
ያም ሰው የወንድሙን ሚስት ማግባት ባይወድድ፥ ዋርሳዪቱ በበሩ አደባባይ ወደሚቀመጡ ሽማግሌዎች ሄዳ፦ ‘ዋርሳዬ በእስራኤል ዘንድ ለወንድሙ ስም ማቆም እንቢ አለ፤ ከእኔም ጋር ሊኖር አልወደደም’ ትበላቸው።
ሁላችሁ፥ የነገዶቻችሁ አለቆች ሽማግሌዎቻችሁም፥ ሹሞቻችሁም፥ ጻፎቻችሁም፥ የእስራኤል ወንድ ሁሉ ዛሬ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ቆማችኋል።
ይህን ቃል በጆሮአቸው እነግር ዘንድ፥ ሰማይንና ምድርንም አስመሰክርባቸው ዘንድ የነገዶቻችሁን አለቆች፥ ሽማግሌዎቻችሁን ሁሉ፥ ሹሞቻችሁንም፥ ጻፎቻችሁንም ሰብስቡልኝ፤