ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ፤ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰማይም አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፤ እንዲህም አልሁ፦
ሮሜ 12:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደስ ከሚለው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሰው ጋርም አልቅሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደስ ከሚላቸው ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያዝኑም ጋራ ዕዘኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ። |
ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ፤ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰማይም አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፤ እንዲህም አልሁ፦
ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየሀገራቸው ወደ እርሱ መጡ፤ እነርሱም ቴማናዊው ንጉሥ ኤልፋዝ፥ አውኬናዊው መስፍን በልዳዶስ፥ አሜናዊው ንጉሥ ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊጐበኙትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ መጡ።
ኢትዮጵያዊውም አቤሜሌክ ኤርምያስን፥ “እነዚህን ጨርቆች በብብትህ ከገመዱ በታች አድርግ” አለው፤ ኤርምያስም እንዲሁ አደረገ።
በደረሰ ጊዜም የእግዚአብሔርን ጸጋ አየና ደስ አለው፤ በፍጹም ልባቸውም በእግዚአብሔር ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መከራቸው።
አንዱ የአካል ክፍል ቢታመም ከእርሱ ጋር የአካል ክፍሎች ሁሉ ይታመማሉ፤ አንዱ የአካል ክፍል ደስ ቢለውም የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።
የእኔ ደስታ የሁላችሁ እንደ ሆነ በሁላችሁ አምኛለሁና በመጣሁ ጊዜ ደስ ሊያሰኙኝ ከሚገባቸው ኀዘን እንዳያገኘኝ ይህን ጻፍሁላችሁ።
ከእነርሱ ጋር አብራችኋቸው እንደ ታሰራችሁ ሆናችሁ እስረኞችን ዐስቡ፤ መከራ የጸናባቸውንም በሥጋችሁ ከእነሱ ጋር እንዳላችሁ ሆናችሁ ዐስቡ።